ከአንተም ከሚወጡት ከምትወልዳቸው ልጆችህ ማርከው ይወስዳሉ፤ በባቢሎንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃንደረቦች ይሆናሉ።”
ኤርምያስ 29:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም የሆነው ንጉሡ ኢኮንያንና እቴጌዪቱ፥ ጃንደረቦቹም፥ የይሁዳና የኢየሩሳሌምም አለቆች ነጻዎችና እሥረኞች፥ ብልሃተኞችና ብረት ሠራተኞችም ከኢየሩሳሌም ከወጡ በኋላ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የሆነው ንጉሡ ኢኮንያን እቴጌዪቱ እናቱ፣ የቤተ መንግሥቱ ባለሟሎች፣ የይሁዳና የኢየሩሳሌም መሪዎች፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችና ብረት ቀጥቃጮች ተማርከው ከኢየሩሳሌም ከተወሰዱ በኋላ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም የሆነው ንጉሡ ኢኮንያን እናቱም እቴጌይቱና ጃንደረቦቹም፥ የይሁዳና የኢየሩሳሌምም አለቆች፥ ጠራቢዎችና ብረት ሠራተኞችም ከኢየሩሳሌም ከወጡ በኋላ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደብዳቤውንም የጻፍኩት ንጉሡ ኢኮንያን፥ እቴጌይቱ እናቱና የቅርብ አገልጋዮቹ፥ የይሁዳና የኢየሩሳሌም መሪዎች፥ የእጅ ጥበብ ሠራተኞችና ሙያተኞች ሁሉ ተማርከው ከተወሰዱ በኋላ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም የሆነው ንጉሡ ኢኮንያን እናቱም እቴጌይቱ ጃንደረቦቹም የይሁዳና የኢየሩሳሌምም አለቆች ጠራቢዎችና ብረት ሠራተኞችም ከኢየሩሳሌም ከወው በኋላ ነው። |
ከአንተም ከሚወጡት ከምትወልዳቸው ልጆችህ ማርከው ይወስዳሉ፤ በባቢሎንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃንደረቦች ይሆናሉ።”
ፊቱንም አቅንቶ በመስኮቱ አያት። “አንቺ ማን ነሽ? ወደዚህ ወደ እኔ ውረጂ” አላት። ከዚህም በኋላ ሁለት ጃንደረቦች ወደ እርሱ ተመለከቱ።
ለነገሥታቱና ለመኳንንቱ፦ የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ራሳችሁን አዋርዳችሁ ተቀመጡ በላቸው።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፥ የይሁዳንም አለቆች፥ ብልሃተኞችንና እስረኞችን፥ ጓደኞቻቸውንም ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ከአፈለሳቸው በኋላ፥ እነሆ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር መቅደስ ፊት የተቀመጡ ሁለት የበለስ ቅርጫቶችን አሳየኝ።
“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን አለቆች ሁሉ ማርኮ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ባፈለሳቸው ጊዜ፥
ወደ ባቢሎንም የሄዱትን የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳን ምርኮ ሁሉ ወደዚች ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና።”
ፍልስጥኤማውያንም፥ “ዕብራውያን ሰይፍና ጦር እንዳይሠሩ” ብለው ነበርና በእስራኤል ምድር ሁሉ ብረት ሠሪ አልተገኘም።