በሰሎሞንም ዘመን ሁሉ ይሁዳና እስራኤል ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ እያንዳንዳቸው ከወይኑና ከበለሱ በታች ተዘልለው ይቀመጡ ነበር።
ኤርምያስ 23:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዘመኑም ይሁዳ ይድናል፤ እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፤ ይህም ስም እግዚአብሔር በነቢያት ኢዮሴዴቅ ብሎ የጠራው ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርሱም ዘመን ይሁዳ ይድናል፤ እስራኤልም ያለ ሥጋት ይኖራል፤ የሚጠራበትም ስም፣ “እግዚአብሔር ጽድቃችን” የሚል ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም በደኅንነት ይቀመጣል፥ እርሱም፦ ‘ጌታ ጽድቃችን ነው’ በሚለው በዚህ ስም የሚጠራ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ በሚነግሥበት ጊዜ የይሁዳ ሕዝብ ደኅንነት ያገኛል፤ የእስራኤልም ሕዝብ በሰላም ይኖራል፤ እርሱም ‘እግዚአብሔር ጽድቃችን’ ተብሎ ይጠራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው። |
በሰሎሞንም ዘመን ሁሉ ይሁዳና እስራኤል ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ እያንዳንዳቸው ከወይኑና ከበለሱ በታች ተዘልለው ይቀመጡ ነበር።
በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፤ ብዙ አሕዛብንም ይዘልፋቸዋል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ፥ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍን አያነሣም፤ ሰልፍንም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም።
አምላካችን እግዚአብሔር ታላቅ ነውና ቸል አይለንም፤ እግዚአብሔር ፈራጃችን ነው፤ እግዚአብሔር አምላካችን ነው። እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤ እርሱ እግዚአብሔር ያድነናል።
“እኔ እግዚአብሔር አምላክ በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፤ በእጄም እይዝሃለሁ፤ አበረታሃለሁም፤ ለልጅ ልጅ ቃል ኪዳን፥ ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ።
ደሴቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እግዚአብሔር ግን እስራኤልን በዘለዓለማዊ መድኀኒት ያድነዋል፤ እናንተም ለዘለዓለም አታፍሩምና አቷረዱም።”
በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ እንዲከናወን አላደርግም፤ በአንቺ ላይ ለፍርድ የሚነሣውን ድምፅ ሁሉ ታጠፊያለሽ፤ ጠላቶችሽም ሁሉ ይፈረድባቸዋል፤ እግዚአብሔርንም ለሚያገለግሉ ርስት አላቸው፤ ጻድቃኔም ትሆኑኛላችሁ ይላል እግዚአብሔር።
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፤
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ ይላል እግዚአብሔር፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።
“እነሆ አንተን ከሩቅ፥ ዘርህንም ከምርኮ ሀገር አድናለሁና ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ! አትፍራ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ አንተም እስራኤል ሆይ! አትደንግጥ፤ ያዕቆብም ይመለሳል፤ ያርፍማል፤ ተዘልሎም ይቀመጣል፤ ማንም አያስፈራውም።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ምርኮአቸውን በመለስሁ ጊዜ በይሁዳ ሀገር በከተሞችዋ፦ የጽድቅ ማደሪያ ሆይ! የቅድስና ተራራ ሆይ! እግዚአብሔር ይባርክህ የሚል ነገርን እንደ ገና ይናገራሉ።
እነሆ በቍጣዬና በመዓቴ፥ በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት ሀገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ ተዘልለውም እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤
በዚያም ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት የጽድቅን ቍጥቋጥ አበቅልለታለሁ፤ እርሱም ፍርድንና ጽድቅን በምድር ያደርጋል።
በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል፤ ኢየሩሳሌምም ተዘልላ ትቀመጣለች፤ የምትጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው።
ተዘልለውም ይቀመጡባታል፤ ቤቶችንም ይሠራሉ፤ ወይኑንም ይተክላሉ፤ በዙሪያቸውም በአሉ በሚንቋቸው ሁሉ ላይ ፍርድን በአደረግሁ ጊዜ ተዘልለው ይቀመጣሉ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካቸው፥ የአባቶቻቸውም አምላክ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ ጎግንም እንዲህ በለው፥ “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን ሕዝቤ እስራኤል በሰላም በተቀመጠ ጊዜ አንተ የምትነሣ አይደለምን?
ዙሪያዋም ዐሥራ ስምንት ሺህ ክንድ ይሆናል፥ ከዚያም ቀን ጀምሮ የከተማዪቱ ስም፦ ‘እግዚአብሔር በዚያ አለ’ ተብሎ ይጠራል።”
የይሁዳ ልጆችና የእስራኤል ልጆች በአንድነት ይሰበሰባሉ፤ ለእነርሱም አንድ አለቃ ይሾማሉ፤ ከምድሪቱም ይወጣሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና።
ነገር ግን የይሁዳን ልጆች ይቅር እላቸዋለሁ፤ እኔ አምላካቸውም እግዚአብሔር አድናቸዋለሁ እንጂ በቀስት ወይም በሰይፍ፥ ወይም በጦር፥ ወይም በሠረገላ፥ ወይም በፈረሶች፥ ወይም በፈረሰኞች የማድናቸው አይደለም” አለው።
በዚያም ቀን ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች፥ ከመሬትም ተንቀሳቃሾች ጋር ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ። ቀስትንና ሰይፍን፥ ጦርንም ከምድሩ እሰብራለሁ፤ ተዘልለሽም ትቀመጫለሽ።
“ነገር ግን በጽዮን ተራራ ላይ መድኀኒት ይሆናል፤ እርሱም ቅዱስ ይሆናል፤ የያዕቆብም ቤት ሰዎች የወረሱአቸውን ይወርሳሉ።
የእስራኤል ቅሬታ ኃጢአትን አይሠሩም፥ ሐሰትንም አይናገሩም፥ በአፋቸውም ውስጥ ተንኰለኛ ምላስ አይገኝም፣ እነርሱም ይሰማራሉ፥ ይመሰጉማል፥ የሚያስፈራቸውም የለም።
ወድጃቸዋለሁና የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፣ አደላድላቸዋለሁም፣ እመልሳቸዋለሁ፣ እኔም አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁና እንዳልጣልኋቸው ይሆናሉ።
እናንተም በኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሱ ናችሁ፤ በእርሱም ከእግዚአብሔር ጥበብንና ጽድቅን፥ ቅድስናንና ቤዛነትን አገኘን።