Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 33:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በዚ​ያም ዘመን ይሁዳ ይድ​ናል፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተዘ​ልላ ትቀ​መ​ጣ​ለች፤ የም​ት​ጠ​ራ​በ​ትም ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቃ​ችን ተብሎ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በዚያ ዘመን ይሁዳ ይድናል፤ ኢየሩሳሌም ያለ ሥጋት ትኖራለች፤ የምትጠራበትም ስም፣ “እግዚአብሔር ጽድቃችን” የሚል ይሆናል።’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል ኢየሩሳሌምም በደኅንነት ትቀመጣለች፤ እርሷም፦ ‘ጌታ ጽድቃችን ነው’ በሚለው ስም ትጠራለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ከጠላት እጅ ድነው በሰላም ይኖራሉ። ከተማይቱም ‘እግዚአብሔር ጽድቃችን ነው’ ተብላ ትጠራለች፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል ኢየሩሳሌምም ተዘልላ ትቀመጣለች፥ የምትጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 33:16
20 Referencias Cruzadas  

በዘ​መ​ኑም ይሁዳ ይድ​ናል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ተዘ​ልሎ ይቀ​መ​ጣል፤ ይህም ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ቢ​ያት ኢዮ​ሴ​ዴቅ ብሎ የጠ​ራው ነው።


እና​ን​ተም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ርሱ ናችሁ፤ በእ​ር​ሱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ጽድ​ቅን፥ ቅድ​ስ​ና​ንና ቤዛ​ነ​ትን አገ​ኘን።


ደሴ​ቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እስ​ራ​ኤ​ልን በዘ​ለ​ዓ​ለ​ማዊ መድ​ኀ​ኒት ያድ​ነ​ዋል፤ እና​ን​ተም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አታ​ፍ​ሩ​ምና አቷ​ረ​ዱም።”


በእ​ር​ሱም እጸና ዘንድ፥ ዛሬ የኦ​ሪት ጽድቅ ሳይ​ኖ​ረኝ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገኝ ጽድቅ አለኝ እንጂ።


ኀጢ​አት የሌ​ለ​በት እርሱ እኛን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን እንደ ኃጥእ አድ​ር​ጓ​ልና።


ከዚህ በኋ​ላም መላው እስ​ራ​ኤል ይድ​ናሉ፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ እን​ዳለ፥ “አዳኝ ከጽ​ዮን ይወ​ጣል፤ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ኀጢ​አ​ትን ያስ​ወ​ግ​ዳል።


የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ፤


እና​ንተ በም​ድር ዳርቻ ያላ​ችሁ ሁሉ፥ እኔ አም​ላክ ነኝና፥ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለ​ምና ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ ትድ​ኑ​ማ​ላ​ችሁ።


ተዘ​ል​ለ​ውም ይቀ​መ​ጡ​ባ​ታል፤ ቤቶ​ች​ንም ይሠ​ራሉ፤ ወይ​ኑ​ንም ይተ​ክ​ላሉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም በአሉ በሚ​ን​ቋ​ቸው ሁሉ ላይ ፍር​ድን በአ​ደ​ረ​ግሁ ጊዜ ተዘ​ል​ለው ይቀ​መ​ጣሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አም​ላክ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


እነሆ በቍ​ጣ​ዬና በመ​ዓቴ፥ በታ​ላ​ቅም መቅ​ሠ​ፍቴ እነ​ር​ሱን ካሳ​ደ​ድ​ሁ​ባት ሀገር ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ​ዚ​ህም ስፍራ እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለ​ውም እን​ዲ​ኖሩ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤


እስ​ራ​ኤ​ልም ተማ​ምኖ፥ በያ​ዕ​ቆብ ምድር ብቻ​ውን፥ በስ​ን​ዴና በወ​ይን ምድር ይኖ​ራል፤ ሰማይ ከደ​መ​ናና ከጠል ጋር ለአ​ንተ ነው።


ስለ ብን​ያ​ምም እን​ዲህ አለ፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ወ​ደደ በእ​ርሱ ዘንድ ተማ​ምኖ ይኖ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዘ​መኑ ሁሉ ይጋ​ር​ደ​ዋል፤ በት​ከ​ሻ​ውም መካ​ከል ያድ​ራል።


ከብዙ ዘመ​ንም በኋላ ትፈ​ለ​ጋ​ለህ፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም ባድማ በነ​በሩ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ ከብዙ ሕዝብ ውስጥ ወደ ተሰ​በ​ሰ​በች፥ ከሰ​ይፍ ወደ ተመ​ለ​ሰች ምድር ትገ​ባ​ለህ፤ እር​ስ​ዋም ከሕ​ዝብ ውስጥ ወጥ​ታ​ለች፤ ሁሉም በሰ​ላም ይቀ​መ​ጡ​በ​ታል።


“እነሆ ለዳ​ዊት የጽ​ድቅ ቍጥ​ቋጥ የማ​ስ​ነ​ሣ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ንጉሥ ይነ​ግ​ሣል፤ ያስ​ባል፤ በም​ድ​ርም ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ያደ​ር​ጋል።


“እነሆ አን​ተን ከሩቅ፥ ዘር​ህ​ንም ከም​ርኮ ሀገር አድ​ና​ለ​ሁና ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ ሆይ! አት​ፍራ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተም እስ​ራ​ኤል ሆይ! አት​ደ​ን​ግጥ፤ ያዕ​ቆ​ብም ይመ​ለ​ሳል፤ ያር​ፍ​ማል፤ ተዘ​ል​ሎም ይቀ​መ​ጣል፤ ማንም አያ​ስ​ፈ​ራ​ውም።


ዙሪ​ያ​ዋም ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ክንድ ይሆ​ናል፥ ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ስም፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ አለ’ ተብሎ ይጠ​ራል።”


ያገ​ኙ​አ​ቸው ሁሉ በሉ​አ​ቸው፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፦ በጽ​ድቅ ማደ​ሪያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ተስፋ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት ስለ ሠሩ እኛ አና​ሳ​ር​ፋ​ቸ​ውም አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios