ከካህናቱም ወገን ልጆች እንግዶቹን ሴቶች ያገቡ ሰዎች ተገኙ፤ ከኢዮሴዴቅ ልጅ ከኢያሱ ልጆችና ከወንድሞቹ ማዓሥያ፥ አልዓዛር፥ ኦሬም፥ ገዳልያ።
ኤርምያስ 23:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዝሙታቸው ምድርን ሞልትዋልና፥ ከመርገም ፊት የተነሣ ምድር አልቅሳለች፤ የምድረ በዳ ማሰሪያው ሁሉ ደርቆአል፤ ሥራቸውና ድካማቸው ከንቱ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድሪቱ በአመንዝሮች ተሞልታለች፤ ከርግማን የተነሣ ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ በምድረ በዳ ያሉት መሰማሪያዎች ደርቀዋል። ነቢያቱም ጠማማ መንገድ ተከትለዋል፤ ሥልጣናቸውን ያለ አግባብ ተጠቅመዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድር በአመንዝሮች ተሞልታለችና፥ ከመርገምም የተነሣ ምድር አልቅሳለች፤ የምድረ በዳውም ማሰማርዎች ደርቀዋል፤ አካሄዳቸውም ክፉ ነው፥ ብርታታቸውም ቅን አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድሪቱ እግዚአብሔርን በተዉ አመንዝሮች ተሞልታለች፤ ነቢያቱ ኀይላቸውን ያለ አግባቡ ይጠቀማሉ፤ የክፋትንም መንገድ ይከተላሉ፤ ከእግዚአብሔር ርግማን የተነሣ፥ ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ መስኮችም ደርቀዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድር ከአመንዝሮች ተሞልታለችና፥ ከመርገምም የተነሣ ምድር አልቅሳለች፥ የምድረ በዳ ማሰማርያ ደርቆአል፥ አካሄዳቸው ክፉ ነው፥ ብርታታቸውም ቅን አይደለም። |
ከካህናቱም ወገን ልጆች እንግዶቹን ሴቶች ያገቡ ሰዎች ተገኙ፤ ከኢዮሴዴቅ ልጅ ከኢያሱ ልጆችና ከወንድሞቹ ማዓሥያ፥ አልዓዛር፥ ኦሬም፥ ገዳልያ።
ስለዚህ ምድር ትውጣቸዋለች፤ በእርስዋ የተቀመጡ በድለዋልና፤ በምድር የሚኖሩ ሰዎችም ይቸገራሉ፤ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ።
ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ኀጢአትን አድርገዋልና፥ ከሐሳዊ ነቢይ ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ሐሰትን አደረጉ።
ብትገድሉም፥ ብታመነዝሩም፥ ብትሰርቁም፥ በሐሰትም ብትምሉ፥ ለበአልም ብታጥኑ፥ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ብትከተሉ ክፉ ያገኛችኋል።
በተራሮቹ ላይ አልቅሱ፤ በምድረ በዳም ጎዳና ላይ እዘኑ፤ ሰው ጠፍትዋልና፤ የሚመላለስም የለምና ሙሾውንም አሙሹ፤ የሰማይ ወፍ ድምፅንም እስከ ከብት ድምፅ ድረስ አይሰሙም፤ ደንግጠውም ተማርከው ሄዱ።
ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ያወራስ ዘንድ የእግዚአብሔር አፍ ለማን ተናገረ? ሰው እንዳያልፍባት ምድርስ ስለ ምን ጠፋች፤ እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተቃጠለች?
ሁሉም አመንዝሮች፥ የዐመጸኞች ጉባኤ ናቸውና ሕዝቤን እተዋቸው ዘንድ ከእነርሱም እለይ ዘንድ በምድረ በዳ ማደሪያን ማን በሰጠኝ?
ሁሉም አመንዝራዎች ናቸው፤ ጋጋሪ እንደሚያነድድበት እንደ ምድጃ ናቸው፤ ሁሉም እስኪቦካ ድረስ እሳትን መቈስቈስና እርሾን መለወስ ይቈያል።
“አንድ ሰው ቢበድል፥ የሚያምለውንም ቃል ቢሰማ፥ ምስክርም ሆኖ አንድ ነገር አይቶ እንደ ሆነ፥ ወይም ዐውቆ እንደ ሆነ ያነን ባይናገር በደሉን ይሸከማል፤
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመኝታቸውም ርኵሰት የለውም፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።
አመንዝሮች ሆይ! ዓለምን መውደድ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።