Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 9:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ይህን የሚ​ያ​ስ​ተ​ውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ያወ​ራስ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ለማን ተና​ገረ? ሰው እን​ዳ​ያ​ል​ፍ​ባት ምድ​ርስ ስለ ምን ጠፋች፤ እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተቃ​ጠ​ለች?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ይህን መረዳት የሚችል ጥበበኛ ሰው ማን ነው? እግዚአብሔር ገልጾለት ይህንስ ማስረዳት የሚችል ማን ነው? ምድሪቱስ ሰው እንደማያልፍበት በረሓ ለምን ጠፋች? ለምን ወና ሆነች?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? እንዲያውጅስ የጌታ አፍ ለማን ተናገረ? ሰው እንዳያልፍባት ምድርስ ስለምን ጠፋች፥ እንደ ምድረ በዳስ ስለምን ተቃጠለች?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ምድሪቱ ማንም ሊዘዋወርባት የማይችል ደረቅ በረሓና ጠፍ መሆንዋ ስለ ምንድን ነው? ይህንንስ የሚያስተውል ጥበበኛ ሰው ማን ነው? ለሌሎች ማስረዳት ይችል ዘንድ የገለጥክለትስ ማን ነው?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ያወራስ ዘንድ የእግዚአብሔር አፍ ለማን ተናገረ? ሰው እንዳያልፍባት ምድርስ ስለምን ጠፋች፥ እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተቃጠለች?

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 9:12
22 Referencias Cruzadas  

ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይህን የሚ​ያ​ደ​ምጥ፥ ለሚ​መ​ጣ​ውም ጊዜ የሚ​ሰማ ማን ነው?


ዝሙ​ታ​ቸው ምድ​ርን ሞል​ት​ዋ​ልና፥ ከመ​ር​ገም ፊት የተ​ነሣ ምድር አል​ቅ​ሳ​ለች፤ የም​ድረ በዳ ማሰ​ሪ​ያው ሁሉ ደር​ቆ​አል፤ ሥራ​ቸ​ውና ድካ​ማ​ቸው ከንቱ ሆነ።


ኀያል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ች​ሁን የነ​ቢ​ያ​ትን ቃል አት​ስሙ፤ ከን​ቱ​ነ​ትን ያስ​ተ​ም​ሩ​አ​ች​ኋል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ሳይ​ሆን ከገዛ ልባ​ቸው የወ​ጣ​ውን ራእይ ይና​ገ​ራሉ።


በቃሌ ቢቆ​ሙና ምክ​ሬን ቢሰሙ ኖሮ ግን ሕዝ​ቤን ከክፉ ሥራ​ቸው በመ​ለ​ሱ​አ​ቸው ነበር።


የሚ​ያ​ልም ነቢይ ሕል​ምን ይና​ገር፤ ቃሌም ያለ​በት ቃሌን በእ​ው​ነት ይና​ገር። ገለባ ከስ​ንዴ ጋር ምን አለው? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እና​ንተ ሴቶች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ ጆሮ​አ​ች​ሁም የአ​ፉን ቃል ትቀ​በል፤ ለሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም ልቅ​ሶ​ውን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ድ​ዋም ለባ​ል​ን​ጀ​ራዋ ዋይ​ታን ታስ​ተ​ምር።


መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንና ሥራ​ቸ​ውን በአ​ያ​ችሁ ጊዜ ያጽ​ና​ኗ​ች​ኋል፤ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ት​ንም ሁሉ በከ​ንቱ እን​ዳ​ላ​ደ​ረ​ግ​ሁ​ባት ታው​ቃ​ላ​ችሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤ​ፍ​ሬም ምን​ድን ነው? እኔ አደ​ከ​ም​ሁት፤ አጸ​ና​ሁ​ትም፤ እኔ እንደ ተወ​ደደ አበባ አፈ​ራ​ዋ​ለሁ፤ ፍሬ​ህም በእኔ ዘንድ ይገ​ኛል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መጠ​በቅ ትተ​ዋ​ልና ሲበሉ አይ​ጠ​ግ​ቡም፤ ሲያ​መ​ነ​ዝ​ሩም አይ​በ​ዙም።


መከሩ ከእ​ር​ሻ​ቸው ጠፍ​ቶ​አ​ልና ገበ​ሬ​ዎች ስለ ስን​ዴ​ውና ስለ ገብሱ ዐፈሩ፤ የወ​ይን አት​ክ​ል​ተ​ኞ​ችም ስለ ወይኑ አለ​ቀሱ።


አሕዛብን አጥፍቻለሁ፣ ግንቦቻቸው ሁሉ ፈርሰዋል፣ መንገዳቸውን ማንም እንዳያልፍባት ምድረ በዳ አድርጌአለሁ፥ ከተሞቻቸውም ማንም እንዳይኖርባቸው፥ አንድስ እንኳ እንዳይቀመጥባቸው ፈርሰዋል።


“እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፤


ይህ​ንም ያው​ቁት ዘንድ አላ​ሰ​ቡ​ትም፤ በሚ​መ​ጣ​ውም ዘመን አያ​ው​ቁ​ትም።


ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos