ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውም ይህ ቤት ባድማ ይሆናል፤ በዚያም የሚያልፍ ሁሉ እያፍዋጨ፦ እግዚአብሔር በዚህ ሀገርና በዚህ ቤት ስለ ምን እንዲህ አደረገ? ብሎ ይደነቃል።
ኤርምያስ 22:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፦ የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ትተው ለሌሎች አማልክት ስለ ሰገዱ፥ ስለ አመለኳቸውም ነው ብለው ይመልሳሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም፣ ‘የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ኪዳን ትተው ሌሎችን አማልክት ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው’ ይላሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፦ “የአምላካቸውን የጌታን ቃል ኪዳን ትተው ለሌሎች አማልክት ስለ ሰገዱ ስላገለገሉአቸውም ነዋ ብለው ይመልሳሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ከእኔ ከአምላካችሁ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን አፍርሳችሁ ባዕዳን አማልክትን በማምለካችሁና በማገልገላችሁ ምክንያት መሆኑንም ይረዳሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ትተው ለሌሎች አማልክት ስለ ሰገዱ ስላመለኩአቸውም ነዋ ብለው ይመልሳሉ። |
ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውም ይህ ቤት ባድማ ይሆናል፤ በዚያም የሚያልፍ ሁሉ እያፍዋጨ፦ እግዚአብሔር በዚህ ሀገርና በዚህ ቤት ስለ ምን እንዲህ አደረገ? ብሎ ይደነቃል።
በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ታስቈጡኝ ዘንድ ትታችሁኛልና፥ ለሌሎች አማልክትም ዐጥናችኋልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።
በእጃቸው ሥራ ሁሉ ሊያስቈጡኝ ትተውኛልና፥ ለሌሎችም አማልክት አጥነዋልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።
ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ ወደ አሉ ወደ አባቶቻቸው ኀጢአት ተመለሱ፥ ያመልኩአቸውም ዘንድ እንግዶችን አማልክት ተከተሉ፤ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት ከአባቶቻቸው ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አፈረሱ።
እንደዚህም በሏቸው፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የዚህን ቃል ኪዳን ቃል የማይሰማ ሰው ርጉም ይሁን፤
አንተ እንዲህ ትላቸዋለህ፦ አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተዉ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ፤ አመለኩአቸውም፤ ሰገዱላቸውም፤ እነርሱም ትተውኛል፤ ሕጌንም አልጠበቁም፤
ያገኙአቸው ሁሉ በሉአቸው፤ ጠላቶቻቸውም፦ በጽድቅ ማደሪያ በእግዚአብሔር ላይ፥ በአባቶቻቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ስለ ሠሩ እኛ አናሳርፋቸውም አሉ።
በሚሄዱባቸውም አሕዛብ መካከል ርኵሰታቸውን ሁሉ ይናገሩ ዘንድ ከሰይፍና ከራብ፥ ከቸነፈርም ጥቂቶች ሰዎችን ከእነርሱ አስቀራለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
መንገዳቸውንና ሥራቸውን በአያችሁ ጊዜ ያጽናኗችኋል፤ ያደረግሁባትንም ሁሉ በከንቱ እንዳላደረግሁባት ታውቃላችሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
አሕዛብም የእስራኤል ቤት በኀጢአታቸው ምክንያት እንደ ተማረኩ ያውቃሉ፤ ስለ ከዱኝ እኔም ፊቴን ከእነርሱ ስለ መለስሁ፥ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ ሰጠኋቸው፥ እነርሱም ሁሉ በሰይፍ ወደቁ።
በቍጣዬና በመቅሠፍቴ በተበቀልሁሽ ጊዜ በዙሪያሽ በአሉ በአሕዛብ ዘንድ ትጨነቂያለሽ፤ ትደነግጫለሽም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
አሕዛብ ሁሉ እግዚአብሔር በዚህች ምድር ስለ ምን እንደዚህ አደረገ? ይህስ የቍጣው ታላቅ መቅሠፍት ምንድን ነው? ይላሉ።