Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 29:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 አሕ​ዛብ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚ​ህች ምድር ስለ ምን እን​ደ​ዚህ አደ​ረገ? ይህስ የቍ​ጣው ታላቅ መቅ​ሠ​ፍት ምን​ድን ነው? ይላሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 አሕዛብም ሁሉ፣ “እግዚአብሔር በዚህች ምድር ላይ ይህን ለምን አደረገባት? ይህ አስፈሪና የሚነድድ ቍጣስ ለምን መጣባት?” ብለው ይጠይቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 አሕዛብም ሁሉ፥ ‘ጌታ በዚች ምድር ላይ ይህን ለምን አደረገባት? ይህ አስፈሪ ቁጣስ ንዴት ለምንድን ነው?’ ብለው ይጠይቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 በዚያን ጊዜ የመላው ዓለም ሕዝብ እንዲህ ሲል ይጠይቃል፤ ‘እግዚአብሔር በዚህች ምድር ላይ ይህን ሁሉ ስለምን አደረገ? ለብርቱ ቊጣውስ ምክንያት የሆነው ነገር ምንድን ነው?’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 አሕዛብ ሁሉ፦ እግዚአብሔር በዚህች ምድር ስለ ምን እንደዚህ አደረገ? ይህስ የቁጣው ታላቅ መቅሠፍት ምንድር ነው? ይላሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 29:24
16 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ልቡ​ና​ህን እንደ ማጽ​ና​ትህ፥ ንስ​ሓም እንደ አለ​መ​ግ​ባ​ትህ መጠን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ፍርድ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ቀን መቅ​ሠ​ፍ​ትን ለራ​ስህ ታከ​ማ​ቻ​ለህ።


መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንና ሥራ​ቸ​ውን በአ​ያ​ችሁ ጊዜ ያጽ​ና​ኗ​ች​ኋል፤ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ት​ንም ሁሉ በከ​ንቱ እን​ዳ​ላ​ደ​ረ​ግ​ሁ​ባት ታው​ቃ​ላ​ችሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ላሜድ። የም​ድር ነገ​ሥ​ታት፥ በዓ​ለ​ምም የሚ​ኖሩ ሁሉ፥ አስ​ጨ​ና​ቂና ጠላት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በር እን​ደ​ሚ​ገባ አላ​መ​ኑም።


“እና​ንተ ግን እኔን ተዋ​ች​ሁኝ፤ ቅዱ​ሱ​ንም ተራ​ራ​ዬን ረሳ​ችሁ፥ ለአ​ጋ​ን​ን​ትም ማዕድ አዘ​ጋ​ጃ​ችሁ፤ ዕድል ለተ​ባለ ጣዖ​ትም የወ​ይን ጠጅ ለመ​ጠጥ ቍር​ባን ቀዳ​ችሁ፤


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እና​ንተ፥ “አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለ ምን አደ​ረ​ገ​ብን?” ብትሉ፥ አንተ፥ “እንደ ተዋ​ች​ሁኝ፥ በሀ​ገ​ራ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት እን​ዳ​መ​ለ​ካ​ችሁ፥ እን​ዲሁ ለእ​ና​ንተ ባል​ሆነ ሀገር ለሌ​ሎች ሰዎች ትገ​ዛ​ላ​ችሁ” ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።


“ለዚ​ህም ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተ​ና​ገ​ርህ ጊዜ፦ ይህን ሁሉ ትልቅ የሆነ ክፉ ነገ​ርን ስለ ምን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገ​ረ​ብን? በደ​ላ​ች​ንስ ምን​ድን ነው? በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ግ​ነው ኀጢ​አት ምን​ድን ነው? ቢሉህ፥


የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ኤር​ም​ያ​ስን ወሰ​ደው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ ተና​ገረ።


ምድ​ሪ​ቱ​ንም የተ​ፈ​ታች አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ከእ​ር​ስዋ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ቃሉ።


የገ​ባ​ላ​ቸ​ው​ንም ቃል ኪዳን ሁሉ አል​ጠ​በ​ቁም። ከንቱ ነገ​ር​ንም ተከ​ተሉ፤ ከን​ቱም ሆኑ፤ እንደ እነ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሠሩ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያሉ​ትን አሕ​ዛብ ተከ​ተሉ።


የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ሙ​ምና፥ ቃል ኪዳ​ኑ​ንም አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባሪያ ሙሴ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አል​ሰ​ሙ​ምና፤ አላ​ደ​ረ​ጉ​ም​ምና።


ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ቸው ዘንድ እጃ​ቸ​ውን በያ​ዝ​ሁ​በት ቀን ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር እንደ ገባ​ሁት ያለ ቃል ኪዳን አይ​ደ​ለም፤ እነ​ርሱ በኪ​ዳኔ አል​ጸ​ኑ​ምና፥ እኔም ቸል አል​ኋ​ቸው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፦ አንቺ ቃል ኪዳ​ንን በማ​ፍ​ረስ መሐ​ላን የና​ቅሽ ሆይ! አንቺ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሽ እኔ ደግሞ አደ​ር​ግ​ብ​ሻ​ለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios