ዮአኪንንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ፤ የንጉሡንም እናት፥ የንጉሡንም ሚስቶች፥ ጃንደረቦቹንም፥ የሀገሩንም ታላላቆች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማረከ።
ኤርምያስ 22:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተንም፥ የወለደችህን እናትህንም ወዳልተወለዳችሁባት ወደ ሌላ ሀገር እጥላችኋለሁ፤ በዚያም ትሞታላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተንና የወለደችህን እናትህን ወዳልተወለዳችሁበት ወደ ሌላ አገር ወርውሬ እጥላችኋለሁ፤ በዚያም ትሞታላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተንም የወለደችህንም እናትህን ወዳልተወለዳችሁባት ወደ ሌላ አገር እጥላችኋለሁ፥ በዚያም ትሞታላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተንም፥ የወለደችህ እናትህንም እንድትሰደዱ አደርጋለሁ፤ ማንኛችሁም ወዳልተወለዳችሁበት አገር ሄዳችሁ ሁላችሁም እዚያ ትሞታላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተንም የወለደችህንም እናትህን ወዳልተወለዳችሁባት ወደ ሌላ አገር እጥላችኋለሁ፥ በዚያም ትሞታላችሁ። |
ዮአኪንንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ፤ የንጉሡንም እናት፥ የንጉሡንም ሚስቶች፥ ጃንደረቦቹንም፥ የሀገሩንም ታላላቆች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማረከ።
ዮአኪንም በነገሠ ጊዜ ዐሥራ ስምንት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ፤ እናቱም ኒስታ ትባል ነበር፤ እርስዋም የኢየሩሳሌም ሰው የኤልናታን ልጅ ነበረች።
እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ ሰባተኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ዮርማሮዴቅ በነገሠ በአንደኛው ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን ከፍ አደረገው፤ ከወህኒ ቤትም አወጣው፤
በወህኒም ውስጥ ለብሶት የነበረውን ልብስ ለወጠለት፤ ዮአኪንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ በፊቱ ሁልጊዜ እንጀራ ይበላ ነበር።
እነሆ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በኀይል ወርውሮ ይጥልሃል፤ ያጠፋሃልም፤ ልብስህንና የክብር አክሊልህንም ይገፍሃል፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ በምድሪቱ የሚኖሩትን በመከራ አሰናክላቸዋለሁ፤ መቅሠፍትሽም እንዲያገኛቸው አስጨንቃቸዋለሁ።
ለነገሥታቱና ለመኳንንቱ፦ የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ራሳችሁን አዋርዳችሁ ተቀመጡ በላቸው።
ስለዚህ ከዚች ምድር እናንተና አባቶቻችሁ ወደ አላወቃችኋት ምድር እጥላችኋለሁ፤ በዚያም ምሕረትን ለማያደርጉላችሁ ሌሎች አማልክት ቀንና ሌሊት ታገለግላላችሁ።”
ወደ ባቢሎንም የሄዱትን የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳን ምርኮ ሁሉ ወደዚች ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና።”
ይህም የሆነው ንጉሡ ኢኮንያንና እቴጌዪቱ፥ ጃንደረቦቹም፥ የይሁዳና የኢየሩሳሌምም አለቆች ነጻዎችና እሥረኞች፥ ብልሃተኞችና ብረት ሠራተኞችም ከኢየሩሳሌም ከወጡ በኋላ ነው።
በዚያ ለመቀመጥ በልባቸው ተስፋ ወደሚያደርጓት ወደ ይሁዳ ምድር ይመለሱ ዘንድ በግብፅ ለመኖር ከመጡ ከይሁዳ ቅሬታ ወገን የሚያመልጥና የሚቀር፥ ወደዚያም የሚመለስ አይኖርም፤ ከሚያመልጥም በቀር ማንም አይመለስም።”