ኤርምያስ 17:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታትና መሳፍንት በሰረገሎችና በፈረሶች ላይ እየተቀመጡ በዚህች ከተማ በሮች ይገባሉ፤ እነርሱና አለቆቻቸው የይሁዳም ሰዎች፥ በኢየሩሳሌምም የሚቀመጡ ይገባሉ፤ ይህችም ከተማ ለዘለዓለም የሰው መኖሪያ ትሆናለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታትና መኳንንታቸው በዚህች ከተማ በሮች ይገባሉ፤ በፈረሶችና በሠረገሎች ተቀምጠው በይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ታጅበው ይመጣሉ፤ ይህችም ከተማ ለዘላለም የሰው መኖሪያ ትሆናለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታትና መሳፍንት፥ በሰረገሎችና በፈረሶች ላይ እየተቀመጡ በዚህች ከተማ በሮች ይገባሉ፤ እነርሱና መሳፍንቶቻቸው የይሁዳም ሰዎች በኢየሩሳሌምም የሚቀመጡ ይገባሉ፥ ይህችም ከተማ ለዘለዓለም የሰው መኖሪያ ትሆናለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዳዊት ዙፋን ላይ የተቀመጡ ነገሥታት ከባለ ሥልጣኖቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በሮች ይገባሉ፤ እነርሱም ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ሕዝብ ጋር በአንድነት ሆነው በፈረሶችና በሠረገሎች ላይ ይቀመጣሉ፤ የኢየሩሳሌም ከተማ ሁልጊዜ በሕዝብ የተሞላች ትሆናለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታትና መሳፍንት በሰረገሎችና በፈረሶች ላይ እየተቀመጡ በዚህች ከተማ በሮች ይገባሉ፥ እነርሱና መሳፍንቶቻቸው የይሁዳም ሰዎች በኢየሩሳሌምም የሚቀመጡ ይገባሉ፥ ይህችም ከተማ ለዘላለም የሰው መኖሪያ ትሆናለች። |
ዳዊትም ከእርሱ ሺህ ሰረገላዎችን፥ ሰባት ሺህ ፈረሰኞችን፥ ሃያ ሺህም እግረኞችን ያዘ፤ ዳዊትም የሰረገለኛውን ፈረስ ሁሉ ቋንጃ ቈረጠ፤ ለራሱም መቶ ሰረገላዎችን ብቻ አስቀረ።
ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፤ ለእግዚአብሔርም በዓል ታደርጉታላችሁ፤ ለልጅ ልጃችሁም ሥርዐት ሆኖ ለዘለዓለም ታደርጉታላችሁ።
ለአለቆች ሰላምን ለእርሱም ሕይወትን አመጣለሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆናል፤ በዳዊት ዙፋን መንግሥቱ ትጸናለች፤ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዐት ይህን ያደርጋል።
አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ፥ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡትን ነገሥታት፥ ካህናቱንም፥ ነቢያቱንም፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን ሁሉ በስካር እሞላቸዋለሁ።
በዳዊት ዙፋን የምትቀመጥ የይሁዳ ንጉሥ ሆይ! አንተና አገልጋዮችህ በእነዚህም በሮች የሚገባ ሕዝብህ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በዘመኑ አይከናወንምና፥ ከዘሩም በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ አይነሣምና፥ እንግዲህ ወዲህም ለይሁዳ ገዢ አይሾምምና ይህን ሰው እንደ ሞተ ቍጠሪው” አለ።
ይህንም ነገር ብታደርጉ፥ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡ ነገሥታት በሰረገሎችና በፈረሶች ላይ ተቀምጠው፥ በዚህ ቤት በሮች ይገባሉ፤ እነርሱም፥ አገልጋዮቻቸውም፥ ሕዝቡም እንዲሁ ይገባሉ።
እርሱም፥ “ሁላችሁ እናንተ ከክፉ መንገዳችሁና ከሥራችሁ ክፋት ተመለሱ፤ እግዚአብሔርም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣችሁ ምድር ትቀመጣላችሁ አለ።
በዚያም ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት የጽድቅን ቍጥቋጥ አበቅልለታለሁ፤ እርሱም ፍርድንና ጽድቅን በምድር ያደርጋል።
በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ልጅ እንዳይሆንለት ከባሪያዬ ከዳዊት ጋር፥ ከአገልጋዮችም ከሌዋውያን ካህናት ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ደግሞ ይፈርሳል።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ መንገዳችሁንና ሥራችሁን አቅኑ፤ በዚህም ስፍራ አሳድራችኋለሁ።
ለእርሱ ፈረሶችን እንዳያበዛ፥ ሕዝቡንም ወደ ግብፅ እንዳይመልስ፤ እግዚአብሔር፦ በዚያች መንገድ መመለስን አትድገም ብሎአልና።
እናንተ ግን፥ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ ወደምትሆን ወደ ጽዮን ተራራ፥ በሰማያት ወደ አለችው ኢየሩሳሌም፥ ደስ ብሎአቸው ወደሚኖሩ አእላፍ መላእክትም ደርሳችኋል።
እንዲህም አለ፥ “በእናንተ ላይ የሚነግሠው የንጉሡ ሥርዐት ይህ ነው፤ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሰረገላ ነጂዎችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ በሰረገሎችም ፊት ይሮጣሉ፤