Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 33:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መጥ ሰው ከዳ​ዊት ዘንድ አይ​ታ​ጣም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘ከዳዊት ዘር በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ፈጽሞ አይታጣም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ዳዊት በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ፈጽሞ አያጣም፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከዳዊት ዘር በእስራኤል ላይ የሚነግሥ ንጉሥ ከቶ እንደማይጠፋ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከዳዊት ዘንድ አይታጣም፥

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 33:17
15 Referencias Cruzadas  

ይኸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኔ፦ ‘ልጆ​ችህ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ቢጠ​ብቁ፥ በፊ​ቴም በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውና በፍ​ጹም ነፍ​ሳ​ቸው በእ​ው​ነት ቢሄዱ ከእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ሰው አይ​ጠ​ፋም’ ብሎ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው።


ለአ​ለ​ቆች ሰላ​ምን ለእ​ር​ሱም ሕይ​ወ​ትን አመ​ጣ​ለ​ሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ በፍ​ር​ድና በጽ​ድቅ ያጸ​ና​ውና ይደ​ግ​ፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆ​ናል፤ በዳ​ዊት ዙፋን መን​ግ​ሥቱ ትጸ​ና​ለች፤ ለሰ​ላ​ሙም ፍጻሜ የለ​ውም። የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​ዐት ይህን ያደ​ር​ጋል።


አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ፦ አንተ በፊቴ እንደ ሄድህ ልጆ​ችህ በፊቴ ይሄዱ ዘንድ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ቢጠ​ብቁ፥ በፊቴ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን የሚ​ቀ​መጥ ሰው ከአ​ንተ አይ​ጠ​ፋም ብለህ ለአ​ባ​ቴ ለ​ዳ​ዊት ተስፋ የሰ​ጠ​ኽ​ውን ጠብቅ።


ስለ​ዚህ በፊቴ የሚ​ቆም ሰው ከሬ​ካብ ልጅ ከኢ​ዮ​ና​ዳብ ወገን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ታ​ጣም፥” ይላል የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አሁ​ንም በፊ​ትህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖር ዘንድ የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቤት ትባ​ርክ ዘንድ ጀም​ረ​ሃል፤ አን​ተም አቤቱ፥ ባር​ከ​ኸ​ዋል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ቡሩክ ይሆ​ናል።”


በኢ​ዮ​አብ ራስ ላይና በአ​ባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይም​ጣ​በት፤ በኢ​ዮ​አ​ብም ቤት ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ወይም ለም​ጻም ወይም አን​ካሳ ወይም በሰ​ይፍ የሚ​ወ​ድቅ ወይም እን​ጀራ የሌ​ለው ሰው አይ​ታጣ።”


በዳ​ዊት ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መጡ ነገ​ሥ​ታ​ትና መሳ​ፍ​ንት በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና በፈ​ረ​ሶች ላይ እየ​ተ​ቀ​መጡ በዚ​ህች ከተማ በሮች ይገ​ባሉ፤ እነ​ር​ሱና አለ​ቆ​ቻ​ቸው የይ​ሁ​ዳም ሰዎች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ቀ​መጡ ይገ​ባሉ፤ ይህ​ችም ከተማ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሰው መኖ​ሪያ ትሆ​ና​ለች።


ዕድ​ሜ​ህም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፤ ከአ​ባ​ቶ​ች​ህም ጋር ባን​ቀ​ላ​ፋህ ጊዜ፥ ከወ​ገ​ብህ የሚ​ወ​ጣ​ውን ዘር​ህን ከአ​ንተ በኋላ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ ።


እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል፤ ዙፋ​ኑን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ለሁ።


የን​ጉሡ የኢ​ዮ​ራም ልጅ የአ​ካ​ዝ​ያስ እኅት ኢዮ​ሳ​ቡ​ሄም የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ልጅ ኢዮ​አ​ስን ከተ​ገ​ደ​ሉት ከን​ጉሡ ልጆች መካ​ከል ሰርቃ ወሰ​ደ​ችው፤ እር​ሱ​ንና ሞግ​ዚ​ቱ​ንም ወደ እል​ፍኝ ወሰ​ደች፤ ከጎ​ቶ​ል​ያም ሸሸ​ገ​ችው፤ አል​ገ​ደ​ሉ​ት​ምም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios