በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ ይቅርም በል፤ አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ሁሉ ልብ ታውቃለህና ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለውና ስጠው።
ኤርምያስ 17:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱና፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ፤ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፣ እንደ ሥራው ፍሬ ለመስጠት፣ ልብን እመረምራለሁ፤ የአእምሮንም ሐሳብ እፈትናለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እኔ ጌታ ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ ለመስጠት ልብን እመረምራለሁ ኩላሊትንም እፈትናለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እግዚአብሔር ግን የሰውን አእምሮና የሰውን ልብ እመረምራለሁ፤ እያንዳንዱንም ሰው በአካሄዱና በሥራው መጠን ዋጋውን እሰጠዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ ኵላሊትንም እፈትናለሁ። |
በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ ይቅርም በል፤ አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ሁሉ ልብ ታውቃለህና ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለውና ስጠው።
“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
አምላኬ ሆይ፥ ልብን እንደምትመረምር፥ ጽድቅንም እንደምትወድድ አውቃለሁ፤ እኔም በልቤ ቅንነትና በፈቃዴ ይህን ሁሉ አቅርቤአለሁ፤ አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በፈቃዱ እንዳቀረበልህ በደስታ አይቻለሁ።
አንተ በተዘጋጀው በማደሪያህ በሰማይ ስማው፤ ይቅርም በለው፤ ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለው፤ አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ልብ ታውቃለህና።
ከፀሓይ በታች የተደረገው ክፉ ሁሉ ለሁሉ ነው፤ የሁሉ ድርሻ አንድ ነውና። ደግሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋትን ትሞላለች፥ በሕይወታቸው ሳሉ ሁከት በልባቸው አለ፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ።
ኵላሊትንና ልብን የምትፈትን፥ በቅንም የምትፈርድ እግዚአብሔር ሆይ! ክርክሬን ገልጬልሃለሁና ከእነርሱ ፍረድልኝ።
ስንዴን ትዘራላችሁ፤ እሾህንም ታጭዳላችሁ፤ ዕጣችሁም ምንም አይጠቅማችሁም፤ ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ በአዝመራችሁ ታፍራላችሁ።
አቤቱ! ጽድቅን የምትፈትን ኵላሊትንና ልብን የምትመረምር የሠራዊት ጌታ ሆይ! ክርክሬን ገልጬልሃለሁና ፍረድልኝ።
እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፤ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።”
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፥ “በጎችን በትናችኋል፤ አባርራችኋቸውማል፥ አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ! እንደ ሥራችሁ ክፋት እጐበኛችኋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር በምክር ታላቅ በሥራም ብርቱ ነህ፤ ስምህ ታላቅ የሆነ፥ ኀያል፥ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ለሁሉም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ፍሬ ትሰጥ ዘንድ ዐይኖችህ በሰው ልጆች መንገድ ሁሉ ተገልጠዋል።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዬ መጣ፤ እንዲህም አለኝ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ተናገር፦ የእስራኤል ቤት ሆይ! ይህን ነገር ተናግራችኋል፤ እኔም የሰውነታችሁን በደል አውቃለሁ።
ይህም የእስራኤልን ወገኖች በዐሳባቸው ከእኔ እንደ ተለዩበት እንደ ልባቸውና እንደ ርኵሰታቸው ያስታቸው ዘንድ ነው።”
እርሱም ልባችንን ይመረምራል፤ ልብ የሚያስበውንም እርሱ ያውቃል፤ ስለ ቅዱሳንም በእግዚአብሔር ዘንድ ይፈርዳል።
ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።
ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።
እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፥ “ፊቱን፥ የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንደሚያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።