La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 10:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ንተ ላይ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ስሙ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእስራኤል ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔር የሚላችሁን ስሙ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ! ጌታ በእናንተ ላይ የተናገረውን ቃል ስሙ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እነሆ እግዚአብሔር የሚነግራችሁን ቃል ስሙ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ የተናገረውን ቃል ስሙ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 10:1
16 Referencias Cruzadas  

ሚክ​ያ​ስም አለ፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የሰ​ማ​ሁት እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋኑ ተቀ​ምጦ፥ የሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ በቀ​ኙና በግ​ራው ቆመው አየሁ።


በሂ​ሶጵ እር​ጨኝ፥ እነ​ጻ​ማ​ለሁ፤ እጠ​በኝ፥ ከበ​ረ​ዶም ይልቅ ነጭ እሆ​ና​ለሁ።


እና​ንተ የሰ​ዶም አለ​ቆች ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ እና​ንተ የገ​ሞራ ሕዝብ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ አድ​ምጡ።


ስለ​ዚህ የተ​ጨ​ነ​ቃ​ችሁ ሰዎ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን ሕዝብ የም​ት​ገዙ አለ​ቆች ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በማን ትመ​ስ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስ​ተ​ያ​ዩ​ታ​ላ​ችሁ?


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ የሚ​ቤ​ዥም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ ፊተኛ ነኝ፤ እኔም ኋለኛ ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አም​ላክ የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የአ​ሕ​ዛ​ብን መን​ገድ አት​ማሩ፤ ከሰ​ማይ ምል​ክ​ትም አት​ፍሩ፤ አሕ​ዛብ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ነሣ ይፈ​ራ​ሉና።


የያ​ዕ​ቆብ ቤት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ወገ​ኖች ሁሉ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


በዳ​ዊት ዙፋን የም​ት​ቀ​መጥ የይ​ሁዳ ንጉሥ ሆይ! አን​ተና አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በእ​ነ​ዚ​ህም በሮች የሚ​ገባ ሕዝ​ብህ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


ስለ​ዚህ እና​ንተ የይ​ሁዳ ቅሬታ ሆይ! አሁን እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ግብ​ፅም ትገቡ ዘንድ በዚ​ያም ትቀ​መጡ ዘንድ ፊታ​ች​ሁን ብታ​ቀኑ፤


አሕ​ዛብ ሁሉ ያል​ተ​ገ​ረዙ ናቸ​ውና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ ልባ​ቸው ያል​ተ​ገ​ረዘ ነውና የተ​ገ​ረ​ዙ​ትን ሁሉ፥ ግብ​ጽ​ንና ይሁ​ዳን፥ ኤዶ​ም​ያ​ስ​ንም፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች፥ ሞዓ​ብ​ንም፥ በም​ድረ በዳም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ጠጕ​ራ​ቸ​ውን በዙ​ሪያ የተ​ላ​ጩ​ት​ንም ሁሉ የም​ጐ​በ​ኝ​በት ዘመን እነሆ ይመ​ጣል።”


እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! እው​ነ​ትና ምሕ​ረት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ማወቅ በም​ድር ስለ​ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ይወ​ቅ​ሳ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


አሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ አንተ፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትን​ቢት አት​ና​ገር፥ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ቤት አት​ዘ​ብ​ዝ​ባ​ቸው ብለ​ሃል።


ስለዚህም የመልእክትን ቃል እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ከእኛ በተቀበላችሁ ጊዜ፥ በእውነት እንዳለ በእናንተ በምታምኑ ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት፥ እኛ ደግሞ እግዚአብሔርን ሳናቋርጥ እናመሰግናለን።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።