ያዕቆብ 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእርሱ ጌታንና አብን እናመሰግናለን፤ በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምላሳችን ጌታንና አብን እንባርካለን፤ በርሷም በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምላሳችን ጌታንና አብን እንባርካለን፥ በእርሷም በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርስዋ አባታችንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፤ እንዲሁም በእርስዋ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን፤ በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን፤ |
ንጉሡ ዳዊትም ወደ በውሪም መጣ፤ እነሆም፥ ሳሚ የሚባል የጌራ ልጅ ከሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፤ እየሄደም ይረግመው ነበር።
የሶርህያ ልጅ አቢሳ ግን፥ “ሳሚ እግዚአብሔር የቀባውን ሰድቦአልና እንግዲህ ሞት የተገባው አይደለምን?” ብሎ መለሰ።
ንጉሡ ዳዊትም በጉባኤው ሁሉ ፊት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ እንዲህም አለ፥ “አቤቱ፥ የእስራኤል አምላክ አባታችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ቡሩክ ነህ።
ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፥ “አምላካችን እግዚአብሔርን አመስግኑ” አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፥ በጕልበታቸውም ተንበርክከው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ ደግሞም ለንጉሡ።
ጌታም አለ፥ “ይህ ሕዝብ በከንፈሮቹ ያከብረኛልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በከንቱ ያመልኩኛል፤ ሰው ሠራሽ ትምህርትም ያስተምራሉ፤
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
ወንድ በሚጸልይበት ጊዜ ሊከናነብ አይገባውም፤ የእግዚአብሔር አርአያውና አምሳሉ ነውና፤ ሴትም ለባልዋ ክብር ናት።
በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን።
ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኀይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።
ወደ እርሻውም ወጡ፤ ወይናቸውንም ለቀሙ፤ ጠመቁትም፤ የደስታም በዓል አደረጉ፤ ወደ አምላካቸውም ቤት ገቡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ አቤሜሌክንም ረገሙት።