Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 108 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።

1 አቤቱ፥ ልመ​ና​ዬን ቸል አት​በል፥

2 የዐ​መ​ፀኛ አፍና የኀ​ጢ​አ​ተኛ አፍ በላዬ ተላ​ቅ​ቀ​ዋ​ልና። በሽ​ን​ገላ አን​ደ​በ​ትም በላዬ ተና​ገሩ፤

3 በጥል ከበ​ቡኝ፥ በከ​ን​ቱም ተዋ​ጉኝ።

4 በወ​ደ​ድ​ኋ​ቸው ፋንታ አጣ​ሉኝ፥ እኔ ግን እጸ​ል​ያ​ለሁ።

5 በመ​ል​ካም ፋንታ ክፉን ከፈ​ሉኝ። በወ​ደ​ድ​ኋ​ቸ​ውም ፋንታ ጠሉኝ።

6 በላዩ ኀጢ​አ​ተ​ኛን ሹም፤ ሰይ​ጣ​ንም በቀኙ ይቁም።

7 በሚ​ከ​ራ​ከ​ርም ጊዜ ተረ​ትቶ ይውጣ፤ ጸሎ​ቱም በደል ትሁ​ን​በት።

8 ዘመ​ኖ​ቹም ጥቂት ይሁኑ፤ ሹመ​ቱ​ንም ሌላ ይው​ሰድ።

9 ልጆ​ቹም ድሃ አደ​ጎች ይሁኑ፥ ሚስ​ቱም መበ​ለት ትሁን።

10 ልጆ​ቹም ታው​ከው ይሰ​ደዱ፥ ይለ​ም​ኑም፥ ከቤ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ያባ​ር​ሯ​ቸው።

11 ባለ ዕዳም ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ይበ​ር​ብ​ረው፥ የደ​ከ​መ​በ​ት​ንም ሁሉ ባዕድ ይበ​ዝ​ብ​ዘው።

12 የሚ​ረ​ዳ​ው​ንም አያ​ግኝ፤ ለድሃ አደግ ልጆ​ቹም የሚ​ራራ አይ​ኑር።

13 ልጆ​ቹም ይጥፉ፤ በአ​ን​ዲት ትው​ልድ ስሙ ትጥፋ።

14 የአ​ባቱ ኀጢ​አት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትታ​ሰብ፤ የእ​ና​ቱም ኀጢ​አት አይ​ደ​ም​ሰስ።

15 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ሁል​ጊዜ ይኑር፤ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውም ከም​ድር ይጥፋ።

16 ምጽ​ዋ​ትን ያደ​ርግ ዘንድ አላ​ሰ​በ​ምና ድሃ​ንና ምስ​ኪ​ን​ንም ሰው አሳ​ዷ​ልና ልቡም ሰውን ለመ​ግ​ደል የጨ​ከነ ነውና።

17 መር​ገ​ምን መረ​ጣት፥ ወደ እር​ሱም ትምጣ፤ በረ​ከ​ት​ንም አል​መ​ረ​ጣ​ትም ከእ​ር​ሱም ትራቅ።

18 መር​ገ​ምን እንደ ልብስ ለበ​ሳት፥ እንደ ውኃም ወደ አን​ጀቱ፥ እንደ ቅባ​ትም ወደ አጥ​ንቱ ገባች።

19 እን​ደ​ሚ​ለ​ብ​ሰው ልብስ፥ ሁል​ጊ​ዜም እን​ደ​ሚ​ታ​ጠ​ቀው ትጥቅ ትሁ​ነው።

20 ይህ ሥራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በሚ​ያ​ጣ​ሉኝ በነ​ፍ​ሴም ላይ ክፉን በሚ​ና​ገሩ ነው።

21 አንተ ግን አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ስለ ስምህ ምሕ​ረ​ት​ህን በእኔ ላይ አድ​ርግ፤ ምሕ​ረ​ትህ መል​ካም ናትና አድ​ነኝ።

22 እኔ ድሃና ምስ​ኪን ነኝና፥ ልቤም በው​ስጤ ደነ​ገ​ጠ​ብኝ።

23 እን​ዳ​ለፈ ጥላ አለ​ቅሁ፥ እንደ አን​በ​ጣም ረገ​ፍሁ።

24 ጕል​በ​ቶች በጾም ደከሙ፤ ሥጋ​ዬም ቅባት በማ​ጣት ከሳ።

25 እኔም በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ተሰ​ደ​ብሁ፤ ባዩኝ ጊዜም ራሳ​ቸ​ውን ነቀ​ነቁ።

26 አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ ርዳኝ፥ ስለ ምሕ​ረ​ት​ህም አድ​ነኝ።

27 አቤቱ፥ እጅህ ይህች እንደ ሆነች፥ አን​ተም ይህ​ችን እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ ይወቁ።

28 እነ​ርሱ ይራ​ገ​ማሉ፥ አንተ ግን ባርክ፤ በእኔ ላይ የሚ​ነ​ሡም ይፈሩ፥ ባሪ​ያህ ግን ደስ ይበ​ለው።

29 የሚ​ያ​ጣ​ሉኝ እፍ​ረ​ት​ንና ውር​ደ​ትን ይል​በሱ፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን እንደ መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይል​በ​ሱ​አት።

30 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በአፌ እጅግ አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ። በብ​ዙ​ዎ​ችም መካ​ከል አከ​ብ​ረ​ዋ​ለሁ።

31 ነፍ​ሴን ከሚ​ከ​ብ​ቡ​አት ያድን ዘንድ በእኔ በድ​ሃው ቀኝ ቆሞ​አ​ልና።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos