አንተም ወደ እኔ ብታልፍ የአብርሃም አምላክ የናኮርም አምላክ በእኛ መካከል ይፍረድ።” ያዕቆብም በአባቱ በይስሐቅ አምላክ ማለ።
ኢሳይያስ 8:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት፤ የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁም እርሱ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምትቀድሱት እርሱ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ የምትፈሩት እርሱ ይሁን፤ የምትንቀጠቀጡለትም እርሱ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልትቀድሱ የሚገባው የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ብቻ ነው፤ ልትፈሩት የሚገባው እርሱን ነው፤ ልትንቀጠቀጡለት የሚገባውም እርሱ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የሠራዊት አምላክ ቅዱስ እንደ ሆንኩ አስቡ፤ መፍራት የሚገባችሁም እኔን ብቻ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት፥ የሚያስፈራችሁና የሚያስደንግጣችሁም እርሱ ይሁን። |
አንተም ወደ እኔ ብታልፍ የአብርሃም አምላክ የናኮርም አምላክ በእኛ መካከል ይፍረድ።” ያዕቆብም በአባቱ በይስሐቅ አምላክ ማለ።
ሙሴም ለሕዝቡ፥ “እግዚአብሔር ሊፈትናችሁ፥ ኀጢአትንም እንዳትሠሩ እርሱን መፍራት በእናንተ ያድር ዘንድ መጥቶአልና አትፍሩ” አላቸው።
ነገር ግን ልጆቻቸው የእጄን ሥራ ባዩ ጊዜ ስለ እኔ ስሜን ይቀድሳሉ፤ የያዕቆብንም ቅዱስ ይቀድሳሉ፤ የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ።
ምድርንም ትሸፍን ዘንድ እንደ ደመና በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ትወጣለህ። በኋለኛው ዘመን ይሆናል፤ ጎግ ሆይ! በፊታቸው በተቀደስሁብህ ጊዜ፥ አሕዛብ ያውቁኝ ዘንድ በምድሬ ላይ አወጣሃለሁ።
ሙሴም አሮንን፥ “እግዚአብሔር፦ ወደ እኔ በሚቀርቡ እመሰገናለሁ፤ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ደነገጠ።
እናንተ በጺን ምድረ በዳ በማኅበሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አላከበራችሁኝምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የክርክር ውኃ ነው።”
ነገር ግን፤ የምትፈሩትን አሳያችኋለሁ፤ እናንተስ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ሊጥል ሥልጣን ያለውን ፍሩት፤ አዎ፥ እላችኋለሁ፤ እርሱን ፍሩ።
እግዚአብሔር ያናገረለትንም ተስፋ ይቀራል ብሎ አልተጠራጠረም፤ በእምነት ጸና እንጂ፤ ለእግዚአብሔርም ክብርን ሰጠ።
በዘመንህም ሁሉ አምላክህን እግዚአብሔርን መፍራትን ትማር ዘንድ፥ ስሙ እንዲጠራበት በመረጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት የእህልህን፥ የወይንህን፥ የዘይትህንም ዐሥራት፥ የላምህንና የበግህንም በኵራት ብላ።
ጥምዱንም በሬዎች ወስዶ በየብልታቸው ቈራረጣቸው፤ ወደ እስራኤልም ዳርቻ ሁሉ በመልእክተኞቹ እጅ ላከና፥ “ሳኦልንና ሳሙኤልን ተከትሎ የማይወጣ ሁሉ፥ በበሬዎቹ እንዲሁ ይደረግበታል” አለ። ድንጋጤም በሕዝቡ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደቀ፤ እንደ አንድ ሰውም ሆነው ጮኹ።