Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 11:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ጥም​ዱ​ንም በሬ​ዎች ወስዶ በየ​ብ​ል​ታ​ቸው ቈራ​ረ​ጣ​ቸው፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ዳርቻ ሁሉ በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞቹ እጅ ላከና፥ “ሳኦ​ል​ንና ሳሙ​ኤ​ልን ተከ​ትሎ የማ​ይ​ወጣ ሁሉ፥ በበ​ሬ​ዎቹ እን​ዲሁ ይደ​ረ​ግ​በ​ታል” አለ። ድን​ጋ​ጤም በሕ​ዝቡ ላይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደቀ፤ እንደ አንድ ሰውም ሆነው ጮኹ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ጥንድ በሬዎች ወስዶ ቈራረጠ፤ ሥጋቸውንም በመልእክተኞች እጅ ልኮ፣ “ሳኦልንና ሳሙኤልን የማይከተል ሰው በሬው እንደዚህ ይቈራረጣል” ሲል በመላው እስራኤል አስነገረ። ታላቅ ፍርሀት ከእግዚአብሔር ዘንድ በሕዝቡ ላይ ወደቀ፤ ሕዝቡም እንደ አንድ ሰው ሆኖ ወጣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጥንድ በሬዎች ወስዶ ቆራረጠ፤ ሥጋቸውንም በመልእክተኞች እጅ ልኮ፥ “ሳኦልንና ሳሙኤልን የማይከተል ሰው በሬው እንደዚህ ይቆራረጣል!” ሲል በመላው እስራኤል አስነገረ። ታላቅ ፍርሀት ከጌታ ዘንድ በሕዝቡ ላይ ወደቀ፤ ሕዝቡም እንደ አንድ ሰው ሆኖ ወጣ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ጥንዱንም በሬዎች ወስዶ ቈራረጣቸው፤ የሥጋውንም ቊራጭ ሁሉ አስይዞ “ሳኦልንና ሳሙኤልን ተከትሎ ወደ ጦርነት የማይወጣ ሰው ቢኖር በሬዎቹ እንደዚህ ይቈራረጡበታል!” ከሚል ማስጠንቀቂያ ጋር መልእክተኞችን ወደ መላው የእስራኤል ምድር ላከ። በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈራ፤ አንድም ሰው ሳይቀር ሁሉም በአንድነት ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ጥምዱንም በሬዎች ወስዶ ቆራረጣቸው፥ ወደ እስራኤልም ዳርቻ ሁሉ በመልክተኞቹ እጅ ሰደደና፦ ሳኦልንና ሳሙኤልን ተከትሎ የማይወጣ ሁሉ፥ በበሬዎቹ እንዲሁ ይደረግ አለ። ድንጋጤም በሕዝቡ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደቀ፥ እንደ አንድ ሰውም ሆነው ወጡ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 11:7
8 Referencias Cruzadas  

ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ ካራ አነሣ፤ ዕቅ​ብ​ቱ​ንም ይዞ ከአ​ጥ​ን​ቶ​ችዋ መለ​ያያ ላይ ለዐ​ሥራ ሁለት ቈራ​ርጦ ወደ እስ​ራ​ኤል ሀገር ሁሉ ሰደደ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ፥ ከገ​ለ​ዓ​ድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ።


በይ​ሁ​ዳም ዙሪያ በነ​በሩ የም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ድን​ጋጤ ሆነ፤ ከኢ​ዮ​ሳ​ፍ​ጥም ጋር አል​ተ​ዋ​ጉም።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ታላቅ ድን​ጋጤ ስለ ወደ​ቀ​ባ​ቸው በጌ​ዶር ዙሪያ የነ​በ​ሩ​ትን ከተ​ሞች ሁሉ መቱ፤ በከ​ተ​ሞ​ቹም ውስጥ እጅግ ብዙ ምር​ኮና ብዝ​በዛ ነበ​ርና ከተ​ሞ​ቹን ሁሉ ማረኩ።


እስ​ራ​ኤ​ልም ከሴ​ቄም ሄደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መፍ​ራት በዙ​ሪ​ያ​ቸው ባሉት ከተ​ሞች ሁሉ ወደቀ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ለማ​ሳ​ደድ አል​ተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውም።


አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት በእ​ና​ንተ ላይ ይሁን፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በደ​ልና ለሰው ፊት ማድ​ላት፥ መማ​ለ​ጃም መው​ሰድ የለ​ምና ሁሉን ተጠ​ን​ቅ​ቃ​ችሁ አድ​ርጉ” አላ​ቸው።


ነገር ግን የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቀድ​ሱት፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ች​ሁና የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ች​ሁም እርሱ ይሁን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios