እነዚህም በእነዚያ ትይዩ ሰባት ቀን ያህል ሰፈሩ፤ በሰባተኛውም ቀን ተጋጠሙ፤ የእስራኤልም ልጆች ከሶርያውያን በአንድ ቀን መቶ ሺህ እግረኛ ገደሉ።
ኢሳይያስ 66:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቃሉ የምትንቀጠቀጡ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ “የእግዚአብሔር ስም ይከብር ዘንድ፦ ደስታችሁም ይገለጥ ዘንድ፥ እነርሱም ያፍሩ ዘንድ የሚጠሏችሁንና የሚጸየፉአችሁን ወንድሞቻችን በሏቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ በቃሉ የምትንቀጠቀጡ፣ ይህን የእግዚአብሔር ቃል ስሙ፤ “እናንተ ወንድሞቻችሁ የጠሏችሁ፣ ስለ ስሜም አውጥተው የጣሏችሁ፣ ‘እስኪ እግዚአብሔር ይክበርና፣ የእናንተን ደስታ እንይ!’ አሏችሁ፤ ይሁን እንጂ ማፈራቸው አይቀርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንት በቃሉ ፊት የምትርዱ፥ የጌታን ቃል ስሙ፦ የጠሉአችሁ የናንተው ሕዝብ፥ ስለ ስሜም ያባረሩአችሁ፦ “ደስታችሁን እንድናይ ጌታ ይክበር” ብለዋል፤ ነገር ግን ያፍራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃሉን የምታከብሩ እናንተ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ “ስለ ስሜ የሚጠሉአችሁና የሚያገሉአችሁ እንዲህ ይሉአችኋል፦ ‘እናንተ ስትደሰቱ እናይ ዘንድ እስቲ እግዚአብሔር ክብሩን ይግለጥ፤’ ኀፍረት ላይ የሚወድቁት ግን እነርሱ ራሳቸው ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቃሉ የምትንቀጠቀጡ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ የጠሉአችሁ ስለ ስሜም ያባረሩአችሁ ወንድሞቻችሁ፦ ደስታችሁን እናይ ዘንድ እግዚአብሔር ይክበር ብለዋል፥ ነገር ግን ያፍራሉ። |
እነዚህም በእነዚያ ትይዩ ሰባት ቀን ያህል ሰፈሩ፤ በሰባተኛውም ቀን ተጋጠሙ፤ የእስራኤልም ልጆች ከሶርያውያን በአንድ ቀን መቶ ሺህ እግረኛ ገደሉ።
በፊቴም ራስህን አዋርደሃልና፥ በዚህም ስፍራ በሚኖሩበት ላይ ቃሌን በሰማህ ጊዜ ራስህን አዋርደሃልና፥ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ አልቅሰሃልና እኔ ደግሞ ሰምቼሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ስለ ምርኮኞቹም መተላለፍ የእስራኤልን አምላክ ቃል የሚፈሩ ሁሉ ወደ እኔ ተሰበሰቡ፤ እኔም እስከ ሠርክ መሥዋዕት ድረስ ዐዝኜ ተቀመጥሁ።
የእግዚአብሔርን ሥራ የሚያቃልለውን እርሱ ያቃልለዋል፥ ትእዛዙን የሚሰማ ግን በእርሱ በሕይወት ይኖራል። ለውሸተኛ ልጅ ምንም ደግነት የለም፥ ለብልህ አገልጋይ ግን ሥራው መልካም ይሆናል። መንገዱም ይቃናል።
ፀሓይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለ ሆንሁ አትዩኝ፤ የእናቴ ልጆች ስለ እኔ ተጣሉ፥ የወይን ቦታዎችንም ጠባቂ አደረጉኝ፤ ነገር ግን የእኔን የወይን ቦታ አልጠበቅሁም።
አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክንድህን አላወቁም፤ ካወቁ ግን ያፍራሉ። አላዋቆች ሰዎችን ቅንአት ያዛቸው፤ አሁንም እሳት ጠላቶችን ትበላለች።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ ባሪያዎች ይበላሉ፤ እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ እነሆ፥ ባሪያዎች ይጠጣሉ፤ እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ እነሆ፥ ባሪያዎች ደስ ይላቸዋል፤ እናንተ ግን ትጐሰቍላላችሁ፤
ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግዚአብሔር፤ “ወደ የዋሁና ወደ ጸጥተኛው፥ ከቃሌም የተነሣ ወደሚንቀጠቀጥ ሰው ከአልሆነ በቀር ወደ ማን እመለከታለሁ?
እንዲህም ሆነ፦ ቃሉን ሁሉ በሰሙ ጊዜ ፈርተው እርስ በርሳቸው ተመካከሩ፤ ባሮክንም፥ “ይህን ቃል ሁሉ በርግጥ ለንጉሡ እንናገራለን” አሉት።
ጌታ እግዚአብሔርን እከተለው ዘንድ እሄዳለሁ፤ እርሱ ያድነናልና፤ እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፤ የውኃ ልጆችም ይደነግጣሉ።
ይህንም ባለ ጊዜ በእርሱ ላይ በጠላትነት የተነሡበት ሁሉ አፈሩ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ሁሉ ከእርሱ ስለሚደረገው ድንቅ ነገር ሁሉ ደስ አላቸው።
ከምኵራባቸው ያስወጡአችኋል፤ ደግሞም እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።
እንዲሁ ክርስቶስም የብዙዎችን ኀጢአት ያስተሰርይ ዘንድ ራሱን አንድ ጊዜ ሠዋ፤ በኋላ ግን ያድናቸው ዘንድ ተስፋ ለሚያደርጉት ያለ ኀጢአት ይገለጥላቸዋል።