Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 13:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የእግዚአብሔርን ሥራ የሚያቃልለውን እርሱ ያቃልለዋል፥ ትእዛዙን የሚሰማ ግን በእርሱ በሕይወት ይኖራል። ለውሸተኛ ልጅ ምንም ደግነት የለም፥ ለብልህ አገልጋይ ግን ሥራው መልካም ይሆናል። መንገዱም ይቃናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ምክርን የሚያቃልል በራሱ ላይ ጥፋት ያመጣል፤ ትእዛዝን የሚያከብር ግን ወሮታን ይቀበላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ትእዛዝን የሚያቃልል በትእዛዝ ተይዞ ይጠፋል፥ ትእዛዝን የሚፈራ ግን በደኅንነት ይኖራል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 መልካም ምክርን የሚንቅ ችግር ይደርስበታል፤ ትእዛዝን የሚያከብር ግን ዋጋ ያገኝበታል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 13:13
26 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ​ናቀ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ስለ ሰበረ፥ ያ ሰው ፈጽሞ ይጥፋ፤ ኀጢ​አቱ በራሱ ላይ ነው።”


ሙሉ ደመወዝን እንድትቀበሉ እንጂ የሠራችሁትን እንዳታጠፉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።


እነ​ርሱ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በሕ​ዝቡ ላይ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ፥ ፈው​ስም እስ​ከ​ማ​ይ​ገ​ኝ​ላ​ቸው ድረስ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​እ​ክ​ተ​ኞች ይሳ​ለቁ፥ ቃሉ​ንም ያቃ​ልሉ፥ በነ​ቢ​ያ​ቱም ላይ ያፌዙ ነበር።


ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት በም​ድረ በዳ በት​እ​ዛዜ ሂዱ አል​ኋ​ቸው፤ አል​ሄ​ዱ​ምም፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ት​ንም ሕጌን አፈ​ረሱ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ፈጽ​መው አረ​ከሱ። በዚ​ህም ጊዜ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ቍጣ​ዬን በም​ድረ በዳ አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።


ፍር​ዴ​ንም ጥሰ​ዋ​ልና፥ በሥ​ር​ዐ​ቴም አል​ሄ​ዱ​ምና፥ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋ​ልና በል​ባ​ቸው ዐሳብ ሄዱ።


ፍር​ዴን አላ​ደ​ረ​ጉ​ምና፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንም ጥሰ​ዋ​ልና፥ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋ​ልና፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ዐሳብ ተከ​ት​ለ​ዋ​ልና።


ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ወደ የዋ​ሁና ወደ ጸጥ​ተ​ኛው፥ ከቃ​ሌም የተ​ነሣ ወደ​ሚ​ን​ቀ​ጠ​ቀጥ ሰው ከአ​ል​ሆነ በቀር ወደ ማን እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ?


በደለኞችን ክፉ ነገር ይከተላቸዋል፤ ጻድቃንን ግን መልካም ነገር ያገኛቸዋል።


“ምክሬን ሁሉ ናቃችሁ፥ ዘለፋዬንም አልተመለከታችሁም፥


አብ​ር​ሃ​ምም፦ ‘ሙሴ​ንና ነቢ​ያ​ትን ካል​ሰ​ሙማ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ የተ​ነሣ ቢኖ​ርም እንኳ አይ​ሰ​ሙ​ትም፤ አያ​ም​ኑ​ት​ምም’ አለው።”


የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ፣ እግዚአብሔርም አደመጠ፥ ሰማም፥ እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ።


ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፤ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።”


የኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ ኣዛ​ር​ያስ፥ የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ ትዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችም ሰዎች ሁሉ ኤር​ም​ያ​ስን፥ “ሐሰት ተና​ግ​ረ​ሃል፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በዚያ ትቀ​መጡ ዘንድ ወደ ግብፅ አት​ግቡ ብሎ አል​ላ​ከ​ህም፤


አሁ​ንም እንደ ጌታ​ዬና የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ትእ​ዛዝ እን​ደ​ሚ​ፈ​ሩት ምክር፥ ሴቶ​ችን ሁሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ወ​ለ​ዱ​ትን እን​ሰ​ድድ ዘንድ ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ጋር ቃል ኪዳን እና​ድ​ርግ። ተነሥ እንደ አም​ላ​ካ​ች​ንም ትእ​ዛዝ ገሥ​ፃ​ቸው፤ እንደ ሕጉም ያድ​ርጉ፤


ከፈ​ር​ዖን ሹሞች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የፈራ ከብ​ቶ​ቹን ወደ ቤቶቹ ሰበ​ሰበ።


ከሚበለጽግና በተስፋ ከሚቈይ ሰውነቱን ሊረዳ የሚጀምር ይሻላል። መልካም ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ናት።


ትእዛዛትን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ መንገዶቹን የሚያቃልል ግን ይጠፋል።


በሥራ ዐዋቂ የሆነ መልካም ነገርን ያገኛል፤ በእግዚአብሔርም የታመነ ብፁዕ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios