Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 5:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 “እናይ ዘንድ፥ ሥራ​ውን ያፋ​ጥን፤ እና​ው​ቃ​ትም ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ምክር፥ ትምጣ” ለሚሉ ወዮ​ላ​ቸው!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 “በዐይናችን እንድናይ እግዚአብሔር ይቸኵል፤ ሥራውንም ያፋጥን፤ የእስራኤልን ቅዱስ፣ የርሱን ዕቅድ እንድናውቃት ትቅረብ፤ ትምጣም” ለሚሉ ወዮላቸው!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በዐይናችን እንድናይ እግዚአብሔር ይቸኩል፤ ሥራውንም ያፋጥን፤ የእስራኤልን ቅዱስ፤ የእርሱን ዕቅድ እንድናውቃት ትቅረብ፤ ትምጣም ለሚሉ ወዮላቸው!”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “እኛ በዐይናችን እናያት ዘንድ እግዚአብሔር ሊያደርግ ያቀደውን በፍጥነት ያድርግ፤ እናውቃትም ዘንድ የእስራኤል ቅዱስ ያቀዳት ምክር ትፈጸም” ለሚሉ ሁሉ ወዮላቸው!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ሥራውንም ያፋጥን፥ እናውቃትም ዘንድ የእስራኤል ቅዱስ ምክር ትቅረብ፥ ትምጣ ለሚሉ ወዮላቸው!

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 5:19
13 Referencias Cruzadas  

“የሰው ልጅ ሆይ! በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር፦ ዘመኑ ረዝ​ሞ​አል፤ ራእ​ዩም ሁሉ ጠፍ​ቶ​አል የም​ት​ሉት ምሳ​ሌው ምን​ድን ነው?


እነሆ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወዴት አለ? አሁን ይምጣ ይሉ​ኛል።


ለሰው ሁሉ ቃሉ ሸክም ይሆ​ን​በ​ታ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም ብላ​ችሁ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አት​ጥሩ፤ የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕ​ያ​ውን አም​ላክ ቃል ለው​ጣ​ች​ኋ​ልና።


“የሰው ልጅ ሆይ! ዐመ​ፀ​ኛው የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት፦ ይህቺ የሚ​ያ​ያት ራእይ ለብዙ ዘመን ናት፤ እር​ሱም ለሩቅ ወራት ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ራል” ይላሉ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክር የሚ​ቆም፥ ቃሉን የሚ​ያ​ይና የሚ​ሰማ ማን ነው? ቃሉ​ንስ ያዳ​መጠ፥ የሰ​ማስ ማን​ነው?


በቃሉ የም​ት​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ይከ​ብር ዘንድ፦ ደስ​ታ​ች​ሁም ይገ​ለጥ ዘንድ፥ እነ​ር​ሱም ያፍሩ ዘንድ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁ​ንና የሚ​ጸ​የ​ፉ​አ​ች​ሁን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በሏ​ቸው።


“ከዚህ መን​ገድ መል​ሱን፤ ከዚ​ህም ፈቀቅ አድ​ር​ጉን በሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቅዱስ ትም​ህ​ርት ከእኛ ዘንድ አስ​ወ​ግዱ” ይሏ​ቸ​ዋል።


ይሁ​ዳም ሦስ​ትና አራት ዐምድ ያህል በአ​ነ​በበ ቍጥር፥ ንጉሡ በብ​ርዕ መቍ​ረጫ ቀደ​ደው፤ ክር​ታ​ሱ​ንም በም​ድጃ ውስጥ በአ​ለው እሳት ፈጽሞ እስ​ኪ​ቃ​ጠል ድረስ በም​ድጃ ውስጥ ወደ አለው እሳት ጣለው።


አሁ​ንም፥ “ንጉሥ የለ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ራ​ን​ምና፤ ንጉ​ሥስ ምን ያደ​ር​ግ​ል​ናል?” ይላሉ።


እግዚአብሔርን በቃላችሁ አታክታችኋል። እናንተም፦ ያታከትነው በምንድር ነው? ብላችኋል። ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል፣ ወይስ፦ የፍርድ አምላክ ወዴት አለ? በማለታችሁ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios