ሆሴዕ 11:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ጌታ እግዚአብሔርን እከተለው ዘንድ እሄዳለሁ፤ እርሱ ያድነናልና፤ እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፤ የውኃ ልጆችም ይደነግጣሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 እግዚአብሔርን ይከተላሉ፤ እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፤ እርሱ ሲያገሣ፣ ልጆቹ እየተንቀጠቀጡ ከምዕራብ ይመጣሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ጌታን ይከተላሉ፥ እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፤ ባገሣም ጊዜ ልጆቹ እየተንቀጠቀጡ ከምዕራብ ይመጣሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 “እኔ እግዚአብሔር እነርሱን ለማዳን እንደሚያገሣ አንበሳ ድምፄን ሳሰማ እነርሱ ይከተሉኛል፤ ልጆቼም እየተንቀጠቀጡ ከወደ ምዕራብ ይመጣሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 እግዚአብሔርን ይከተላሉ፥ እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፥ ባገሣም ጊዜ ልጆች እየተንቀጠቀጡ ከምዕራብ ይመጣሉ። Ver Capítulo |
እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛልና፥ “አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ እንደሚያገሣ፥ ድምፁም ተራሮችን እስኪሞላ በእርሱ ላይ እንደሚጮህ፥ እረኞችም ሁሉ ሲጮሁበት ከብዛታቸው የተነሣ እንደማይፈራ፥ ከድምፃቸውም የተነሣ እንደማይደነግጥ፥ እነርሱም ከቍጣው ብዛት የተነሣ ድል እንደሚሆኑና እንደሚደነግጡ፥ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።