ኢሳይያስ 62:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእንግዲህ ወዲህ፥ “የተተወች” አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፥ “ውድማ” አትባልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፥ “ደስታዬ የሚኖርባት” ትባያለሽ፤ ምድርሽም፥ “ባል ያገባች” ትባላለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእንግዲህ፣ “የተተወች” ብለው አይጠሩሽም፤ ምድርሽም፣ “የተፈታች” አትባልም፤ ነገር ግን፣ “ደስታዬ በርሷ” ትባያለሽ፤ ምድርሽም፣ “ባለባል” ትባላለች፤ እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ይለዋል፤ ምድርሽም ባለባል ትሆናለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእንግዲህ ወዲህ፦ የተተወች አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፦ ውድማ አትባልም፤ ነገር ግን ጌታ ደስታዬ ባንቺ ነው ብሏታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፦ ደስታዬ የሚኖርባት ትባያለሽ ምድርሽም፦ ባል ያገባች ትባላለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእንግዲህ ወዲህ “የተተወች” ተብለሽ አትጠሪም፤ ምድርሽም “ባድማ” ተብላ አትጠራም። የምትጠሪበትም አዲስ ስም፥ “እግዚአብሔር በእርስዋ ደስ ይለዋል!” የሚል ይሆናል፤ ምድርሽም “ባለ ባል” ተብላ ትጠራለች፤ እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ይለዋል፤ ምድርሽም ባል እንዳላት ሴት ትሆናለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእንግዲህ ወዲህ፦ የተተወች አትባዪም፥ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፦ ውድማ አትባልም፥ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፦ ደስታዬ የሚኖርባት ትባያለሽ ምድርሽም፦ ባል ያገባች ትባላለች። |
አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፤ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል እግዚአብሔር።
እንግዲህ በምድርሽ ውስጥ ግፍ፥ በዳርቻሽም ውስጥ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ አይሰማም፤ ቅጥሮችሽ ድኅነት ይባላሉ፤ በሮችሽም በጥርብ ድንጋይ ይሠራሉ።
በእግዚአብሔርም እጅግ ደስ ይላቸዋል። ነፍሴም በእግዚአብሔር ሐሤት ታደርጋለች። ሽልማትን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማቷም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የደስታንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና።
እግዚአብሔር፥ “የተቤዣቸው፥ የተቀደሰ ሕዝብ” ብለው ይጠሩአቸዋል፤ አንቺም፥ “የተተወች ያይደለች የተወደደች ቅድስት ከተማ” ትባያለሽ።
አሕዛብ ጽድቅሽን፥ ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ፤ የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ።
ጐልማሳም ከድንግሊቱ ጋር እንደሚኖር፥ እንዲሁ ልጆችሽ ከአንቺ ጋር ይኖራሉ፤ ሙሽራም በሙሽራዪቱ ደስ እንደሚለው፥ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።
እኔም በኢየሩሳሌም ሐሤትን አደርጋለሁ፤ በሕዝቤም ደስ ይለኛል፤ ከዚያም ወዲያ የልቅሶ ድምፅና የዋይታ ድምፅ በውስጥዋ አይሰማም።
ከዳተኞች ልጆች ሆይ! እኔ እገዛችኋለሁና ተመለሱ፤ ይላል እግዚአብሔር። አንዱንም ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን እወስዳችኋለሁ፤ ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ፤
ለእነርሱም መልካምን በማድረግ ይቅር እላቸዋለሁ፤ በእውነትም በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።
ይህችም ከተማ እኔ የምሠራላቸውን በጎነት ሁሉ በሚሰሙ፥ እኔም ስላመጣሁላቸው በጎነትና ሰላም ሁሉ በሚፈሩና በሚደነግጡ አሕዛብ ሁሉ ፊት ለደስታ፥ ለክብርና ለገናንነት ትሆናለች።”
ሰዎችም ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆናለች፤ የፈረሱት፥ ባድማ የሆኑት፥ የጠፉትም ከተሞች ተመሽገዋል፤ ሰውም የሚኖርባቸው ሆነዋል ይላሉ።
አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፣ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል።
ሙሽራ ያለችው ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው የሙሽራው ሚዜ ግን በሙሽራው ቃል እጅግ ደስ ይለዋል፤ የእኔ ደስታ አሁን ተፈጸመች።
ለእግዚአብሔር የሚገባ ቅንዐት እቀናላችኋለሁና፤ ወደ እርሱ አቀርባችሁ ዘንድ ለአንዱ ንጹሕ ድንግል ሙሽራ ለክርስቶስ አጭቻችኋለሁና።
እግዚአብሔርም በአባቶችህ ደስ እንዳለው በመልካሙ ነገር ሁሉ እንደ ገና በአንተ ደስ ይለዋልና አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ፥ በሆድህም ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ፥ በከብትህም ብዛት እጅግ ይባርክሃል።
እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።