Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 61:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅግ ደስ ይላ​ቸ​ዋል። ነፍ​ሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች። ሽል​ማ​ትን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽል​ማ​ቷም እን​ዳ​ጌ​ጠች ሙሽራ፥ የማ​ዳ​ንን ልብስ አል​ብ​ሶ​ኛ​ልና፥ የደ​ስ​ታ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ደር​ቦ​ል​ኛ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፤ ነፍሴ በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች፤ ሙሽራ ራሱን እንደሚያሳምር፣ ሙሽራዪቱም በዕንቈቿ እንደምታጌጥ፣ የድነትን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 61:10
52 Referencias Cruzadas  

በእ​ር​ሱም እጸና ዘንድ፥ ዛሬ የኦ​ሪት ጽድቅ ሳይ​ኖ​ረኝ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገኝ ጽድቅ አለኝ እንጂ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ጽድ​ቅና ሰላም፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም የሆነ ደስታ ነው እንጂ መብ​ልና መጠጥ አይ​ደ​ለ​ምና።


በዚህ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ርሱ ይቅ​ር​ታ​ውን ባገ​ኘ​ን​በት በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እን​መ​ካ​ለን እንጂ።


ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።


ዐይ​ን​ሽን አን​ሥ​ተሽ በዙ​ሪ​ያሽ ተመ​ል​ከቺ፤ እነ​ዚህ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ። እኔ ሕያው ነኝና እነ​ዚ​ህን ሁሉ እንደ ጌጥ ትለ​ብ​ሻ​ቸ​ዋ​ለሽ፤ እንደ ሙሽ​ራም ትጐ​ና​ጸ​ፊ​አ​ቸ​ዋ​ለሽ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፤ ጽዮን ሆይ፥ ኀይ​ል​ሽን ልበሺ፤ አን​ቺም ቅድ​ስ​ቲቱ ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ያል​ተ​ገ​ረ​ዘና ርኩስ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ወደ አንቺ አያ​ል​ፍ​ምና ክብ​ር​ሽን ልበሺ።


በክ​ር​ስ​ቶስ የተ​ጠ​መ​ቃ​ችሁ እና​ን​ተማ ክር​ስ​ቶ​ስን ለብ​ሳ​ች​ኋል።


አባ​ቱም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን እን​ዲህ አላ​ቸው፦ ‘ያማሩ ልብ​ሶ​ችን ቶሎ አም​ጡና አል​ብ​ሱት፤ ለጣ​ቱም ቀለ​በት፥ ለእ​ግ​ሩም ጫማ አድ​ር​ጉ​ለት፤’


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለክ​ብሩ የተ​ከ​ላ​ቸው የጽ​ድቅ ዛፎች እን​ዲ​ባሉ ለጽ​ዮን አል​ቃ​ሾች አደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በአ​መ​ድም ፋንታ አክ​ሊ​ልን፥ በል​ቅ​ሶም ፋንታ የደ​ስ​ታን ዘይት፥ በኀ​ዘ​ንም መን​ፈስ ፋንታ የም​ስ​ጋ​ናን መጐ​ና​ጸ​ፊያ እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ልኮ​ኛል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቤ​ዣ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ ወደ ጽዮ​ንም በደ​ስ​ታና በሐ​ሤት ይመ​ጣሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ክብር በራ​ሳ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ ደስ​ታ​ንና ተድ​ላን ያገ​ኛሉ፤ ኀዘ​ንና ልቅ​ሶም ይወ​ገ​ዳሉ።


አሁ​ንም አቤቱ አም​ላክ ሆይ፥ ከኀ​ይ​ልህ ታቦት ጋር ወደ ዕረ​ፍ​ትህ ተነሣ፤ አቤቱ አም​ላክ ሆይ፥ ካህ​ና​ትህ ደኅ​ን​ነ​ትን ይል​በሱ፤ ቅዱ​ሳ​ን​ህም በደ​ስታ ደስ ይበ​ላ​ቸው።


እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።


ነገር ግን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ልበ​ሱት፤ የሥ​ጋ​ች​ሁ​ንም ምኞት አታ​ስቡ።


የሚ​ያ​ም​ኑ​በት ሁሉ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይጸ​ድ​ቃሉ።


እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፣ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።


ሐናም ጸለ​የች፤ እን​ዲ​ህም አለች፦ “ልቤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸና፤ ቀን​ዴም በአ​ም​ላኬ በመ​ድ​ኀ​ኒቴ ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ ተከ​ፈተ፤ በማ​ዳ​ን​ህም ደስ ብሎ​ኛል።


በዚ​ያም ቀን፥ “እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድ​ር​ገ​ነ​ዋል፤ ያድ​ና​ልም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ ነው፤ ጠብ​ቀ​ነ​ዋል፤ በመ​ዳ​ና​ች​ንም ደስ ይለ​ናል፤ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን” ይላሉ።


ዘወ​ትር በጌ​ታ​ችን ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ደግሜ እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡም ይመ​ለ​ሳሉ፤ በደ​ስ​ታም ተመ​ል​ሰው ወደ ጽዮን ይመ​ጣሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ​ታም በራ​ሳ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ ሐሤ​ት​ንና ደስ​ታ​ንም ያገ​ኛሉ፤ መከራ፥ ኀዘ​ንና ትካ​ዜም ይጠ​ፋሉ።


ሰባቱም ኋለኛዎች መቅሠፍቶች የሞሉባቸውን ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ “ወደዚህ ና፤ የበጉንም ሚስት ሙሽራይቱን አሳይሃለሁ፤” ብሎ ተናገረኝ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የእ​ሳ​ቱን ነበ​ል​ባል ይቈ​ር​ጣል።


የኤፍሬምም ሰዎች እንደ ኃያላን ይሆናሉ፥ ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ደስ ይለዋል፣ ልጆቻቸውም አይተው ደስ ይላቸዋል፥ ልባቸውም በእግዚአብሔር ሐሤት ያደርጋል።


በውኑ ሙሽራ ጌጥ​ዋን ወይስ ድን​ግል ዝር​ግፍ ጌጥ​ዋን ትረ​ሳ​ለ​ችን? ሕዝቤ ግን ለማ​ይ​ቈ​ጠር ወራት ረስ​ቶ​ኛል።


እር​ሱም፥ “ሂዱ፤ የሰ​ባ​ው​ንም ብሉ፤ ጣፋ​ጩ​ንም ጠጡ፤ ለእ​ነ​ዚ​ያም ምንም ለሌ​ላ​ቸው እድል ፈን​ታ​ቸ​ውን ላኩ፤ ዛሬ ለጌ​ታ​ችን የተ​ቀ​ደሰ ቀን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይ​ላ​ችን ነውና አት​ዘኑ” አላ​ቸው።


ሎሌ​ውም የብ​ርና የወ​ርቅ ጌጥ፥ ልብ​ስም አወጣ፤ ለር​ብ​ቃም ሰጣት፤ ዳግ​መ​ኛም ለአ​ባ​ቷና ለእ​ናቷ እጅ መንሻ ሰጣ​ቸው።


በዙፋኑ ዙሪያም ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።


ጽድ​ቅን ለበ​ስሁ፥ ቅን​ነ​ት​ንም እንደ መጎ​ና​ጸ​ፊያ ተሸ​ለ​ምሁ፤ ፍር​ድ​ንም እንደ ኩፋር ተቀ​ዳ​ጀ​ኋት


የሕ​ይ​ወት ምንጭ ከአ​ንተ ዘንድ ነውና፤ በብ​ር​ሃ​ንህ ብር​ሃ​ንን እና​ያ​ለን።


ጕን​ጮ​ችሽ እንደ ዋኖስ እጅግ ያማሩ ናቸው፥ አን​ገ​ት​ሽም በዕ​ንቍ ድሪ ያማረ ነው።


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ትላ​ለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈ​ጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ ቍጣ​ህ​ንም ከእኔ መል​ሰ​ሃ​ልና፥ ዳግ​መ​ኛም ይቅር ብለ​ኸ​ኛ​ልና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


እነሆ፥ አም​ላኬ መድ​ኀ​ኒቴ ነው፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ሬና ዝማ​ሬዬ ነው፤ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ሆኖ​አ​ልና በእ​ርሱ ታም​ኜ​አ​ለሁ፤ አል​ፈ​ራ​ምም።”


አዳ​ኝህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተ​ኸ​ዋ​ልና፥ ረዳ​ትህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አላ​ስ​ብ​ኸ​ውም፤ ስለ​ዚህ የሐ​ሰ​ትን ተክል ተክ​ለ​ሃል፤ የሐ​ሣ​ር​ንም ዘር ዘር​ተ​ሃል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ፥ ድንቅ ነገ​ርን የዱሮ እው​ነ​ተኛ ምክ​ርን አድ​ር​ገ​ሃ​ልና አከ​ብ​ር​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ።


ታበ​ጥ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ነፋ​ስም ይጠ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ ዐውሎ ነፋ​ስም ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል፤ አን​ተም በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ደስ ይል​ሃል።


ትእ​ዛ​ዜን ብት​ሰማ ኖሮ፥ ሰላ​ምህ እንደ ወንዝ ጽድ​ቅ​ህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር፤


እኔ ግን፥ “በከ​ንቱ ደከ​ምሁ፤ ምንም ጥቅም ለሌ​ለ​ውና ለከ​ንቱ ጕል​በ​ቴን ፈጀሁ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ል​ኛል፤ መከ​ራ​ዬም በአ​ም​ላኬ ፊት ነው” አልሁ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ደስ አሰ​ኝ​ሻ​ለሁ፤ ባድ​ማ​ሽ​ንም ሁሉ ደስ አሰ​ኛ​ለሁ፤ ምድረ በዳ​ሽ​ንም እንደ ዔድን፥ በረ​ሃ​ዎ​ች​ሽ​ንም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት አደ​ር​ጋ​ለሁ። ደስ​ታና ተድላ እም​ነ​ትና የዝ​ማሬ ድምፅ በው​ስጧ ይገ​ኝ​ባ​ታል።


ወደ ተቀ​ደሰ ተራ​ራዬ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በጸ​ሎ​ቴም ቤት ደስ አሰ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቤቴ ለአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የሚ​ሆን የጸ​ሎት ቤት ይባ​ላ​ልና፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውና ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም በመ​ሠ​ዊ​ያዬ ላይ የተ​መ​ረጠ ይሆ​ናል።


በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትታ​መ​ና​ለህ፤ በም​ድ​ርም በረ​ከት ላይ ያወ​ጣ​ሃል፤ የአ​ባ​ትህ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ርስት ይመ​ግ​ብ​ሃል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ እን​ደ​ዚህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


ነገር ግን በው​ስ​ጥዋ ደስ​ታ​ንና ሐሤ​ትን ያገ​ኛሉ፤ እኔም ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ደስ​ታን ለሕ​ዝ​ቤም ሐሤ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ካህ​ና​ቱም በገቡ ጊዜ ከመ​ቅ​ደሱ በው​ጭው አደ​ባ​ባይ አይ​ወ​ጡም፤ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ግን ቅዱስ ነውና በዚያ ያኖ​ሩ​ታል፤ ሌላም ልብስ ለብ​ሰው ወደ ሕዝብ ይወ​ጣሉ።”


ደግሞ፦ ንጹሕ ጥምጥም በራስ ላይ አድርጉ አለ። እነርሱም በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም አደረጉ፥ ልብስንም አለበሱት፣ የእግዚአብሔርም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios