ኢሳይያስ 54:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥቂት ጊዜ ተውሁሽ፤ በታላቅ ምሕረትም ይቅር እልሻለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለጥቂት ጊዜ ተውሁሽ፤ ነገር ግን በታላቅ ርኅራኄ መልሼ እሰበስብሻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥቂት ጊዜ ተውሁሽ፥ በታላቅም ምሕረት እሰበስብሻለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለጥቂት ጊዜ ብቻ ትቼሽ ነበር፤ ነገር ግን በታላቅ ርኅራኄ እመልስሻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጥቂት ጊዜ ተውሁሽ፥ በታላቅም ምሕረት እሰበስብሻለሁ። |
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ከአሦርና ከግብፅ፥ ከባቢሎንና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላሜጤን፥ ከምሥራቅና ከምዕራብ ለቀሩት ለሕዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ገና እጁን ይገልጣል።
ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል፤ ከእስራኤልም የቀሩትን ይሰበስባል፤ ከይሁዳም የተበተኑትን ከአራቱ የምድር ማዕዘኖች ያከማቻል።
በዚያም ቀን እንዲህ ትላለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈጥተኸኛልና፥ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፥ ዳግመኛም ይቅር ብለኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል፤ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፤ በሀገራቸውም ያርፋሉ፤ መጻተኞችም ከእነርሱ ጋር አንድ ይሆናሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጨመራሉ።
በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከወንዝ ፈሳሽ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ዐጥር ያጥራል፤ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።
እግዚአብሔር ሕዝቡን ይቅር ብሎአልና፥ ከሕዝቡም ችግረኞቹን አጽንቶአልና። ሰማያት ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤ ተራሮችም እልል ይበሉ።
ዐይንሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፤ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ። እኔ ሕያው ነኝና እነዚህን ሁሉ እንደ ጌጥ ትለብሻቸዋለሽ፤ እንደ ሙሽራም ትጐናጸፊአቸዋለሽ ይላል እግዚአብሔር።
አንቺም በልብሽ፦ የወላድ መካን ሆኛለሁና፥ እኔም መበለት ነኝና እነዚህን ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ፥ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ እነዚህስ ከወዴት መጡ?” ትያለሽ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ደብዳቤ የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
ከእስራኤል የተበተኑትን የሚሰበስብ ጌታ እግዚአብሔር፦ ወደ ተሰበሰቡት ሌሎችን እሰበስብለታለሁ” ይላል።
ዐይኖችሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፤ ልጆችሽም እንደ ተሰበሰቡ እነሆ፥ እዪ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ ይመጣሉ፤ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃ ላይ ይሸከሙአቸዋል።
ከእንግዲህ ወዲህ፥ “የተተወች” አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፥ “ውድማ” አትባልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፥ “ደስታዬ የሚኖርባት” ትባያለሽ፤ ምድርሽም፥ “ባል ያገባች” ትባላለች።
በስጦታው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቸርነትና የእግዚአብሔርን ምስጋና ዐሰብሁ፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ወገኖች እውነተኛ ፈራጅ ነው፤ እንደ ቸርነቱና እንደ ጽድቁ ብዛትም ይቅርታውን ያመጣልናል።
“ሥራቸውንና አሳባቸውን ዐውቄአለሁ፤ እነሆም እኔ እመጣለሁ፤ አሕዛብንና ልሳናትንም ሁሉ እሰበስባለሁ፤ እነርሱም ይመጣሉ፤ ክብሬንም ያያሉ።
“ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ላይ በተሠራው በደል የተሞላች ብትሆንም፥ እስራኤል መበለት አልሆነችም፤ ይሁዳም ከአምላኩ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ አልራቀም።
ከአሕዛብም መካከል አወጣችኋለሁ፤ ከየሀገሩም ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፤ ወደ ገዛ ምድራችሁም እመልሳችኋለሁ።
“ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።
እግዚአብሔርም ኀጢአትህን ይቅር ይልሃል ይራራልህማል፤ እግዚአብሔርም አንተን ከበተነበት ከአሕዛብ ሁሉ መካከል መልሶ ይሰበስብሃል።
እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ! በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።