የይሁዳና የብንያም የአባቶች ቤቶች አለቆችም፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት ይወጡ ዘንድ እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው ሁሉ ተነሡ።
ኢሳይያስ 49:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአፈረሱሽ በኋላ ፈጥነሽ ትታነጺያለሽ፤ ያፈረሱሽ ከአንቺ ይወጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንዶች ልጆችሽ ፈጥነው ይመለሳሉ፤ ያፈራረሱሽም ከአንቺ ይሸሻሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆችሽ ይፈጥናሉ፥ ሊያፈረሱሽና ሊያወደሙሽ ከአንቺ ይወጣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንቺን የሚገነቡ ፈጣኖች ናቸው፤ ያወደሙሽ ግን ከአንቺ ርቀው ይሄዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆችሽ ይፈጥናሉ፥ ያፈረሱሽና ያወደሙሽ ከአንቺ ዘንድ ይወጣሉ። |
የይሁዳና የብንያም የአባቶች ቤቶች አለቆችም፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት ይወጡ ዘንድ እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው ሁሉ ተነሡ።
እኔም፥ “እኛ ያለንበትን ጕስቍልና፥ ኢየሩሳሌም እንደ ፈረሰች፥ በሮችዋም በእሳት እንደ ተቃጠሉ ታያላችሁ። አሁንም ከእንግዲህ ወዲህ መሳለቂያ እንዳንሆን ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንሥራ” አልኋቸው።
ቍጣዬን በኀጢአተኛ ሕዝብ ላይ እልካለሁ፤ ይማርኳቸውና ይበዘብዙአቸው ዘንድ፥ ከተሞችንም ይረግጡአቸውና እንደ ትቢያ ያደርጓቸው ዘንድ ሕዝቤን አዝዛለሁ።
ፈርሰሻልና፥ ፈጽመሽም ጠፍተሻልና በአንቺ ለሚኖሩ ሰዎች ዛሬ ጠባብ ትሆኚባቸዋለሽ፤ ያጠፉሽም ከአንቺ ይርቃሉ።
አንቺ ግን ሰማያትን የፈጠረውን፥ ምድርንም የመሠረታትን ፈጣሪሽን እግዚአብሔርን ረስተሻል፤ ያጠፋሽ ዘንድ ባዘጋጀ ጊዜ ከአስጨናቂው ቍጣ የተነሣ ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈርተሻል፤ ይቈጣሽ ዘንድ መክሮአልና፤ አሁን የሚያስጨንቅሽ ቍጣው የት አለ?
ዐይኖችሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፤ ልጆችሽም እንደ ተሰበሰቡ እነሆ፥ እዪ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ ይመጣሉ፤ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃ ላይ ይሸከሙአቸዋል።
ጐልማሳም ከድንግሊቱ ጋር እንደሚኖር፥ እንዲሁ ልጆችሽ ከአንቺ ጋር ይኖራሉ፤ ሙሽራም በሙሽራዪቱ ደስ እንደሚለው፥ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።
ከእንግዲህም ወዲያ ለእስራኤል ቤት የሚወጋ እሾህ፥ በዙሪያቸውም ከአሉ ከናቋቸው ሁሉ የሚያቈስል ኩርንችት አይሆንም፤ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
እኔም የእስራኤልን ቤት ሰዎች ሁሉ ሁሉንም አበዛባችኋለሁ፤ በከተሞችም ሰዎች ይኖሩባቸዋል፤ ባድማዎቹም ስፍራዎች ይሠራሉ።