Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 49:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እነሆ፥ እኔ በእጄ ግን​ቦ​ች​ሽን ሣልሁ፤ አን​ቺም ሁል​ጊዜ በፊቴ ነሽ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እነሆ፤ በእጄ መዳፍ ላይ ቀርጬሻለሁ፤ ቅጥሮችሽ ምን ጊዜም በፊቴ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እነሆ፥ እኔ በእጄ መጻፍ ቀርጬሻለሁ፥ ቅጥሮችሽም ሁልጊዜ በፊቴ አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ኢየሩሳሌም ሆይ! እነሆ፥ በእጄ መዳፍ ላይ ቀርጬሻለሁ፤ ቅጥሮችሽንም ዘወትር አስታውሳለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እነሆ፥ እኔ በእጄ መጻፍ ቀርጬሻለሁ፥ ቅጥሮችሽም ሁል ጊዜ በፊቴ አሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 49:16
12 Referencias Cruzadas  

ባሪያዬ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል ሆይ፥ በዚያ ቀን እወስድሃለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እኔ መርጬሃለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እንደ ቀለበት ማተሚያ አደርግሃለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ሽን በቅ​ጥ​ርሽ ላይ ቀንና ሌሊት አቁ​ሜ​አ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ስቡ ከቶ ዝም አይ​ሉም፤


እን​ግ​ዲህ በም​ድ​ርሽ ውስጥ ግፍ፥ በዳ​ር​ቻ​ሽም ውስጥ ጕስ​ቍ​ል​ናና ቅጥ​ቃጤ አይ​ሰ​ማም፤ ቅጥ​ሮ​ችሽ ድኅ​ነት ይባ​ላሉ፤ በሮ​ች​ሽም በጥ​ርብ ድን​ጋይ ይሠ​ራሉ።


እንደ ቀለ​በት በል​ብህ፥ እንደ ቀለ​በ​ትም ማኅ​ተም በክ​ን​ድህ አኑ​ረኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበ​ረ​ታች ናትና፥ ቅን​ዐ​ትም እንደ ሲኦል የጨ​ከ​ነች ናትና። ላን​ቃዋ እንደ እሳት ላንቃ እንደ ነበ​ል​ባል ነው።


በዚ​ያም ቀን ይህን ቅኔ በይ​ሁዳ ምድር ይዘ​ም​ራሉ፤ እነ​ሆም፥ የጸ​ና​ችና የም​ታ​ድን፥ ቅጥ​ር​ንና ምሽ​ግ​ንም የም​ታ​ደ​ርግ ከተማ አለ​ችን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በበ​ረ​ታች እጅ ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቶ​ሃ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ በአ​ፍህ ይሆን ዘንድ በእ​ጅህ እንደ ምል​ክት፥ በዐ​ይ​ኖ​ች​ህም መካ​ከል እንደ መታ​ሰ​ቢያ ይሁ​ን​ልህ።


ግን​ብ​ሽ​ንም በቀይ ዕንቍ፥ በሮ​ች​ሽ​ንም ቢረሌ በተ​ባለ ዕንቍ፥ ዳር​ቻ​ዎ​ች​ሽ​ንም በከ​በረ ዕንቍ እሠ​ራ​ለሁ።


“እኔ ሕያው ነኝ የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ቄም ልጅ ኢኮ​ን​ያን ሆይ፥ አን​ተን በሰ​ወ​ር​ሁ​በት ቀኝ እጄ እን​ዳለ ማሕ​ተም ነበ​ርህ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ግን እን​ደ​ማ​ት​ኖር እኔ ሕያው ነኝ፤” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እስ​ኪ​ያ​ጸና፥ በም​ድ​ርም ላይ ምስ​ጋና እስ​ኪ​ያ​ደ​ር​ጋት ድረስ ዝም አት​በሉ።


የይ​ሁዳ ኀጢ​አት በብ​ረት ብርዕ በደ​ን​ጊያ ሰሌዳ ተጽ​ፎ​አል፤ በል​ባ​ቸው ጽላ​ትና በመ​ሠ​ዊ​ያ​ቸው ቀን​ዶ​ችም ተቀ​ር​ጾ​አል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios