ከዚህም በኋላ ኀጢአቱን ያስባል። እንደ ጤዛ ትነት ይጠፋል። እንደ ሥራውም ይከፈለዋል። ዐመፀኛም ሁሉ እንደ በሰበሰ ዛፍ ይሰበራል።
ኢሳይያስ 49:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በውኑ ሴት፥ ልጅዋን ትረሳለችን? ከማኅፀንዋ ለተወለደውስ አትራራምን? ሴት ይህን ብትረሳ፥ እኔ አንቺን አልረሳሽም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለችን? ለወለደችውስ ልጅ አትራራለትምን? ምናልባት እርሷ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ የተወለደው ሕጻን ልጇን ትረሳለች? ርህራሄ አልባስ እስክመሆን ትደርሳለች? አዎን፥ እርሷ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልሳል፦ “እናት የምታጠባውን ልጅዋን ልትረሳ ትችላለችን? ወይስ ለወለደችው ልጅ አትራራምን? እርስዋ እንኳ ብትረሳ እኔ ግን እናንተን አልረሳም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም። |
ከዚህም በኋላ ኀጢአቱን ያስባል። እንደ ጤዛ ትነት ይጠፋል። እንደ ሥራውም ይከፈለዋል። ዐመፀኛም ሁሉ እንደ በሰበሰ ዛፍ ይሰበራል።
እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል፤ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፤ በሀገራቸውም ያርፋሉ፤ መጻተኞችም ከእነርሱ ጋር አንድ ይሆናሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጨመራሉ።
ያዕቆብ ሆይ፥ አንተም እስራኤል፥ አገልጋዬ ነህና ይህን ዐስብ፤ እኔ ፈጥሬሃለሁ፤ አንተም ባሪያዬ ነህ፤ እስራኤል ሆይ፥ አትርሳኝ።
ተራሮችን እንዳልቀሥፋቸው እንዳላፈልሳቸውም፥ ኮረብቶችም እንዳይነዋወጡ እንደ ማልሁ እንዲሁ ከእኔ ዘንድ ያለሽ ይቅርታ አያልቅም፤ የሰላምሽ ቃል ኪዳንም አይጠፋም፤ መሓሪሽ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአልና።
በእውነት ኤፍሬም ለእኔ የተወደደ ልጅ ነው፤ ደስ የሚያሰኝም ሕፃን ነው፤ በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር አስበዋለሁ፤ ስለዚህ አንጀቴ ታወከችለት፤ ርኅራኄም እራራለታለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
“ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ላይ በተሠራው በደል የተሞላች ብትሆንም፥ እስራኤል መበለት አልሆነችም፤ ይሁዳም ከአምላኩ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ አልራቀም።
ጋሜል። አራዊት እንኳ ጡታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ፤ የወገኔ ሴት ልጆች ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካኞች ሆኑ።
እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።
እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው!
እግዚአብሔር ለእርሱ ሕዝብ ያደርጋችሁ ዘንድ ተቀብሎአችኋልና፥ እግዚአብሔር ስለ ታላቅ ስሙ ሕዝቡን አይተውም።