Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሆሴዕ 11:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እስ​ራ​ኤል ሕፃን በነ​በረ ጊዜ ወደ​ድ​ሁት፤ ልጄ​ንም ከግ​ብፅ ጠራ​ሁት፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “እስራኤል ገና ሕፃን ሳለ ወደድሁት፤ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤን እስራኤልን ገና በሕፃንነቱ ወደድኩት፤ ልጄን ከግብጽ ጠራሁት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 11:1
18 Referencias Cruzadas  

አቤቱ፥ አን​ተን ከጥ​ልቅ ጠራ​ሁህ።


በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን፥ እንደ ንስር ክን​ፍም እንደ ተሸ​ከ​ም​ኋ​ችሁ፥ ወደ እኔም እን​ዳ​መ​ጣ​ኋ​ችሁ አይ​ታ​ች​ኋል።


አንተ ግን ፈር​ዖ​ንን እን​ዲህ ትለ​ዋ​ለህ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እስ​ራ​ኤል የበ​ኵር ልጄ ነው፤


ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ አል​ሁህ፤ አን​ተም ልት​ለ​ቅ​ቃ​ቸው ባት​ፈ​ቅድ፤ እኔ የበ​ኵር ልጅ​ህን እን​ደ​ም​ገ​ድል ዕወቅ።”


በፊቴ የከ​በ​ር​ህና የተ​መ​ሰ​ገ​ንህ ነህና፥ እኔም ወድ​ጄ​ሃ​ለ​ሁና ስለ​ዚህ ብዙ ሰዎ​ችን ለአ​ንተ ቤዛ፥ አለ​ቆ​ች​ንም ለራ​ስህ እሰ​ጣ​ለሁ።


ቤቴን ትች​አ​ለሁ፤ ርስ​ቴ​ንም ጥያ​ለሁ፤ ነፍሴ የም​ት​ወ​ድ​ዳ​ት​ንም በጠ​ላ​ቶ​ችዋ እጅ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቻ​ለሁ።


“ሂድ፤ እን​ዲህ ብለህ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጆሮ ተና​ገር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የብ​ላ​ቴ​ን​ነ​ት​ሽን ምሕ​ረት፥ የታ​ጨ​ሽ​በ​ት​ንም ፍቅር፥ በም​ድረ በዳ ዘር ባል​ተ​ዘ​ራ​በት ምድር እንደ ተከ​ተ​ል​ሽኝ አስ​ቤ​አ​ለሁ።


ከኀ​ጢ​አ​ት​ሽና ከዝ​ሙ​ትሽ ሁሉ ይህ ይከ​ፋል፤ አንቺ ዕራ​ቁ​ት​ሽን ሳለሽ፥ ኀፍ​ረ​ትም ሞል​ቶ​ብሽ ሳለሽ፥ በደ​ም​ሽም ተለ​ው​ሰሽ ሳለሽ፥ የሕ​ፃ​ን​ነ​ት​ሽን ወራት አላ​ሰ​ብ​ሽም።


“በአ​ን​ቺም ዘንድ ባለ​ፍሁ ጊዜ፤ በደ​ም​ሽም ተለ​ው​ሰሽ በአ​የ​ሁሽ ጊዜ፦ ከደ​ምሽ ዳኝ አል​ሁሽ፤


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ክፋት የተ​ነሣ እን​ዲሁ አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በነ​ጋም ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ ይጥ​ሉ​ታል።


ያዕ​ቆብ ወደ ሶርያ ሀገር ሸሸ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ስለ ሚስት አገ​ለ​ገለ፤ ስለ ሚስ​ትም ጠበቀ።


ኤፍ​ሬ​ምም፥ “ባለ​ጸጋ ሆኜ​አ​ለሁ፤ ሀብ​ት​ንም አግ​ኝ​ቻ​ለሁ፤ በድ​ካ​ሜም ሁሉ ኀጢ​አት የሚ​ሆን በደል አይ​ገ​ኝ​ብ​ኝም” አለ።


ሰማ​ይን ያጸ​ናሁ፥ ምድ​ር​ንም የፈ​ጠ​ርሁ፥ እጆ​ችም የሰ​ማይ ሠራ​ዊ​ትን ያቆሙ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ። እን​ዳ​ት​ከ​ተ​ላ​ቸ​ውም እነ​ር​ሱን አላ​ሳ​የ​ሁ​ህም። ከግ​ብፅ ምድ​ርም ያወ​ጣ​ሁህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌላ አም​ላክ አት​ወቅ፤ ከእኔ በቀር የሚ​ያ​ድ​ንህ የለ​ምና።


ከዚ​ያም የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘ​ብ​ዋን እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ምክ​ር​ዋ​ንም በአ​ኮር ሸለቆ እገ​ል​ጣ​ለሁ፤ እንደ ሕፃ​ን​ነ​ትዋ ወራት፥ ከግ​ብ​ፅም እንደ ወጣ​ች​በት ቀን ትዘ​ም​ራ​ለች።


ወድጃችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እናንተ ግን፦ በምን ወደድኸን? ብላችኋል። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል እግዚአብሔር ያዕቆብንም ወደድሁ፥ ዔሳውንም ጠላሁ።


ለሕ​ዝ​ቡም ራራ​ላ​ቸው፤ ቅዱ​ሳን ሁሉ ከእ​ጅህ በታች ናቸው፤ እነ​ር​ሱም የአ​ንተ ናቸው። ቃሎ​ች​ህ​ንም ይቀ​በ​ላሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የወ​ደ​ዳ​ች​ሁና የመ​ረ​ጣ​ችሁ፥ ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ስለ በዛ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ እና​ንት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ጥቂ​ቶች ነበ​ራ​ች​ሁና፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos