ከንቱን የሚናገር ይግባና ይይ፤ ልቡ በላዩ ላይ ኀጢአትን ሰበሰበ፤ ወደ ሜዳ ይወጣል ይናገራልም፥ በእኔም ላይ ይተባበራል።
ኢሳይያስ 48:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አላወቅህም፤ አላስተዋልህም፤ ጆሮህን ከጥንት አልከፈትሁልህም፤ አንተ ፈጽሞ ወንጀለኛ እንደ ሆንህ፥ ከማኅፀንም ጀምረህ ተላላፊ ተብለህ እንደ ተጠራህ ዐውቄአለሁና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አልሰማህም ወይም አላወቅህም፤ ጆሮህ ከጥንት የተከፈተ አልነበረም፤ አንተ አታላይ እንደ ነበርህ፣ ከልጅነትህ ጀምሮ ዐመፀኛ መባልህን ዐውቄአለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አልሰማህም፥ አላወቅህም፥ ጆሮህ ከጥንት አልተከፈተችም፤ አንተ ፈጽሞ ወንጀለኛ እንደሆንህ ከማኅፀንም ጀምረህ ተላላፊ ተብለህ እንደ ተጠራህ አውቄአለሁና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የምናገረውን አትሰሙም፤ ለማወቅም አትፈልጉም፤ ከጥንት ጀምሮ ጆሮአችሁ የተደፈነ ነው፤ ይህም የሆነው እናንተ በጣም ከዳተኞች መሆናችሁንና ከተወለዳችሁ ጀምሮ ዐመፀኞች ተብላችሁ መጠራታችሁን ዐውቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አልሰማህም፥ አላወቅህም፥ ጆሮህ ከጥንት አልተከፈተችም፥ አንተ ፈጽሞ ወንጀለኛ እንደ ሆንህ ከማኅፀንም ጀምረህ ተላላፊ ተብለህ እንደ ተጠራህ አውቄአለሁና። |
ከንቱን የሚናገር ይግባና ይይ፤ ልቡ በላዩ ላይ ኀጢአትን ሰበሰበ፤ ወደ ሜዳ ይወጣል ይናገራልም፥ በእኔም ላይ ይተባበራል።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያፈርስሃል፤ ከቤትህም ይነቅልሃል፥ ያፈልስሃልም፥ ሥርህንም ከሕያዋን ምድር።
ከባድ ራእይ ተነገረኝ፤ ወንጀለኛው ይወነጅላል፤ በደለኛውም ይበድላል። የኤላም ሰዎችና የሜዶን መልእክተኛ በእኔ ላይ ይመጣሉ። ዛሬ ግን እጨነቃለሁ፤ እረጋጋለሁም።
አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክንድህን አላወቁም፤ ካወቁ ግን ያፍራሉ። አላዋቆች ሰዎችን ቅንአት ያዛቸው፤ አሁንም እሳት ጠላቶችን ትበላለች።
ለሚያዋርዱአችሁ ወዮላቸው! እናንተን ግን የሚያዋርዳችሁ የለም፤ የሚወነጅላችሁ እናንተን የሚወነጅል አይደለም፤ ወንጀለኞች ይጠመዳሉ፤ ይያዛሉም፤ ብል እንደበላው ልብስም ያልቃሉ።
ስለዚህ የቍጣውን መዓትና የሰልፉን ጽናት አመጣባቸው፤ በዙሪያቸው አቃጠላቸው፤ እነርሱ ግን አላወቁም፤ በልባቸውም አላስተዋሉም።
ስለዚህ ምክንያት ጥፋት ይመጣብሻል፤ ጥልቀቱን አታውቂም፤ በውስጡም ትወድቂያለሽ፤ ጕስቁልና ይመጣብሻል፤ ማምለጥም አይቻልሽም፤ ሞት ድንገት ይመጣብሻል፤ አታውቂምም።
እነርሱም አሁን እንጂ ከጥንት አልተፈጠሩም፤ አንተም፥ “እነሆ፥ ዐውቄአቸዋለሁ” እንዳትል ከዛሬ በፊት አልሰማሃቸውም።
ይሰሙኝስ ዘንድ ለማን እናገራለሁ? ለማንስ አዳኛለሁ? እነሆ፥ ጆሮአቸው ያልተገረዘች ናት፤ ለመስማትም አይችሉም፤ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቃል ለስድብ ሆኖባቸዋል፥ ይሰሙት ዘንድ አልፈቀዱምና።
ዲቃሎችን ልጆች ወልደዋልና እግዚአብሔርን ከድተዋል፤ አሁንም ኵብኵባ እነርሱንና ርስታቸውን ይበላቸዋል።
እግዚአብሔር የወደደውን መቅደስ ይሁዳ አርክሶአልና፥ የእንግዳውንም አምላክ ልጅ ሚስት አድርጎ አግብቶአልና ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኵሰት ተሠርቶአል።
እኛ ሁላችን ቀድሞ እንደ ሥጋችን ምኞት ኖርን፤ የሥጋችንንም ፈቃድና ያሰብነውን አደረግን፤ እንደ ሌሎች ኃጥአንም ሁሉ የጥፋት ልጆች ሆንን።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ ከአባቶችህ ጋር ታንቀላፋለህ፤ ይህም ሕዝብ ይነሣል፤ ይቀመጥባትም ዘንድ በሚሄድባት ምድር መካከል ያሉትን ሌሎችን አማልክት ተከትሎ ያመነዝራል፤ እኔንም ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳሉ።