አሁንም የእግዚአብሔር ጉባኤ እስራኤል ሁሉ እያዩ፥ አምላካችንም እየሰማ፥ ይህችን መልካሚቱን ምድር ትወርሱ ዘንድ፥ ለልጆቻችሁም ለዘለዓለም ታወርሱአት ዘንድ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤ ፈልጉም።
ኢሳይያስ 45:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስውር ወይም በጨለማ ስፍራ አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብ ዘር፦ በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም፤ ጽድቅን የምናገር፥ ቅን ነገርንም የምናገር እኔ እግዚአብሔር ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጨለማ ምድር፣ በምስጢር አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብም ዘር፣ ‘በከንቱ ፈልጉኝ’ አላልሁም። እኔ እግዚአብሔር ጽድቅን እናገራለሁ፤ ትክክለኛውንም ነገር ዐውጃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በስውር ወይም በጨለማ ምድር አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብ ዘር፦ በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም፤ እኔ ጌታ እውነትን እናገራለሁ ትክክለኛውንም አወራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጨለማ በሆነ አገር በድብቅ አልተናገርኩም፤ የያዕቆብን ልጆች፦ ‘ቅርጽ በሌለው ቦታ ፈልጉኝ’ አላልኳቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር እውነቱን እናገራለሁ፤ ትክክል የሆነውንም ነገር እገልጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስውር ወይም በጨለማ ምድር ሥፍራ አልተናገርሁም፥ ለያዕቆብ ዘር፦ በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም፥ እኔ እግዚአብሔር ጽድቅን እናገራለሁ ቅንንም አወራለሁ። |
አሁንም የእግዚአብሔር ጉባኤ እስራኤል ሁሉ እያዩ፥ አምላካችንም እየሰማ፥ ይህችን መልካሚቱን ምድር ትወርሱ ዘንድ፥ ለልጆቻችሁም ለዘለዓለም ታወርሱአት ዘንድ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤ ፈልጉም።
እርሱም ንጉሡን አሳን፥ የይሁዳንና የብንያምን ሕዝብ ሁሉ ሊገናኝ ወጣ፤ እንዲህም አለ፥ “አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ብትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል።
በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኀጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፤ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።
ንጉሡንም፥ “የአምላካችን እጅ በሚሹት ሁሉ ላይ ለመልካም ነው፤ ኀይሉና ቍጣው ግን እርሱን በሚተዉ ሁሉ ላይ ነው” ብለን ተናግረን ነበርና፤ በመንገድ ካለው ጠላት ያድኑን ዘንድ ጭፍራና ፈረሰኞች ከንጉሡ እለምን ዘንድ አፍሬ ነበርና።
እጃችሁን ወደ እኔ ብትዘረጉ፥ ዐይኖችን ከእናንተ እመልሳለሁ፤ ምህላንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደምን ተሞልተዋልና።
ተናግሬአለሁ፤ አድኜማለሁ፤ መክሬማለሁ፤ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምልኮ አልነበረም፤ ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር አምላክ እንደ ሆንሁ እናንተ ራሳችሁ ምስክሮች ናችሁ፤
ራሳችሁን አትደብቁ፤ ከጥንት ጀምሮ አልሰማችሁምን? አልነገርኋችሁምን? ከእኔ ሌላ አምላክ እንደ ሌለ ምስክሮች ናችሁ።”
ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፤ አትመለስምም፤ ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ምላስም ሁሉ በእግዚአብሔር ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።”
ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፤ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።
ከኤዶምያስ፥ ከባሶራ የሚመጣ፥ ልብሱም የቀላ፥ የሚመካ ኀይለኛ፥ አለባበሱም ያማረ፥ ይህ ማን ነው? ስለ ጽድቅ የምከራከር፥ ስለ ማዳንም የምፈርድ እኔ ነኝ።
የያዕቆብን ዘርና የይሁዳን ዘር አመጣለሁ፤ የተቀደሰው ተራራዬንም ይወርሳሉ፤ እኔ የመረጥኋቸውና ባሪያዎችም ይወርሱአታል፤ በዚያም ይኖራሉ።
እነርሱም፥ “ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ጠይቁ” ባሉአችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአምላኩ መጠየቅ አይገባውምን? ወይስ ለሕያዋን ሲሉ ሙታንን ይጠይቃሉን?
የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ ወይስ የጨለመች ምድር ሆንሁበትን? ሕዝቤስ ስለ ምን፦ እኛ አንገዛልህም፤ ከእንግዲህም ወዲህ ወደ አንተ አንመለስም ይላል?
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “እኔ ለዓለም በግልጥ ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብም፥ በቤተ መቅደስም ሁልጊዜ አስተማርሁ፤ በስውርም የተናገርሁት አንዳች ነገር የለም።
እነሆ፥ እርሱ በገሀድ ይናገራል፤ እነርሱ ግን ምንም የሚሉት የለም፤ ይህ በእውነት ክርስቶስ እንደ ሆነ ምናልባት አለቆች ዐውቀው ይሆን?
ጌታችን ኢየሱስም በመቅደስ ሲያስተምር ቃሉን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፥ “እኔን ታውቁኛላችሁ፤ ከወዴትም እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እኔ ራሴ የመጣሁ አይደለሁም፤ ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ አለ።
“ምስጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛና ለልጆቻችን ለዘለዓለም ነው።
እግዚአብሔር በሥራው እውነተኛ ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ እግዚአብሔር የታመነ ነው፤ ክፋትም የለበትም፤ እግዚአብሔር ጻድቅና ቸር ነው።