Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 43:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አድ​ኜ​ማ​ለሁ፤ መክ​ሬ​ማ​ለሁ፤ በእ​ና​ን​ተም ዘንድ ባዕድ አም​ልኮ አል​ነ​በ​ረም፤ ስለ​ዚህ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እንደ ሆንሁ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ገልጫለሁ፤ አድኛለሁ፤ ተናግሬአለሁ፤ በመካከላችሁ እኔ እንጂ ባዕድ አምላክ አልነበረም። እኔ አምላክ እንደ ሆንሁ፣ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ” ይላል እግዚአብሔር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ተናግሬአለሁ፥ አድኛለሁ፥ አሳይቻለሁ፥ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም፤ ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፥ ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እኔ ወደፊት የሚሆነውን ነገር አስቀድሜ ተናግሬአለሁ፤ እናንተን ያዳንኩ እኔ ነኝ፤ ከባዕዳን አማልክት አንድ እንኳ ይህን አላደረገም፤ ለዚህ ሁሉ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ተናግሬአለሁ አድኜማለሁ አሳይቼማለሁ፥ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም፥ ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እኔም አምላክ ነኝ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 43:12
13 Referencias Cruzadas  

ታው​ቁና ታም​ኑ​ብኝ ዘንድ እኔም እንደ ሆንሁ ታስ​ተ​ውሉ ዘንድ፥ እና​ንተ፥ የመ​ረ​ጥ​ሁ​ትም ባሪ​ያዬ ምስ​ክ​ሮች ሁኑ፤ እኔም ምስ​ክር እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ፤ ከእኔ በፊት አም​ላክ አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ኔም በኋላ አይ​ኖ​ርም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ​ውን መራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሌላ አም​ላክ አል​ነ​በ​ረም።


ራሳ​ች​ሁን አት​ደ​ብቁ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምን? አል​ነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁ​ምን? ከእኔ ሌላ አም​ላክ እንደ ሌለ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ።”


እን​ግ​ዲህ አም​ላ​ካ​ችን አቤቱ፥ የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ አንተ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከእጁ አድ​ነን።”


እነሆ፥ መን​ፈ​ስን በላዩ እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ወሬ​ንም ይሰ​ማል፤ ወደ ምድ​ሩም ይመ​ለ​ሳል፤ በም​ድ​ሩም በሰ​ይፍ እን​ዲ​ወ​ድቅ አደ​ር​ጋ​ለሁ በሉት” አላ​ቸው።


በዚህ በልዩ ጣዖት አነ​ሣ​ሡኝ፤ በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውም አስ​መ​ረ​ሩኝ።


በስ​ውር ወይም በጨ​ለማ ስፍራ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም፤ ለያ​ዕ​ቆብ ዘር፦ በከ​ንቱ ፈል​ጉኝ አላ​ል​ሁም፤ ጽድ​ቅን የም​ና​ገር፥ ቅን ነገ​ር​ንም የም​ና​ገር እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእ​ኔም በቀር አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ አድ​ን​ማ​ለሁ፤ እኔ እገ​ር​ፋ​ለሁ፤ ይቅ​ርም እላ​ለሁ፤ ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።


እነሆ፥ ለአ​ሕ​ዛብ ምስ​ክር፥ ለወ​ገ​ኖ​ችም አለ​ቃና አዛዥ እን​ዲ​ሆን አደ​ረ​ግ​ሁት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios