ኢሳይያስ 26:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በከፍታ የሚኖሩትን ሰዎች ዝቅ ታደርጋለህ፤ የተመሸጉትንም ከተሞች ትጥላለህ፤ እስከ ምድርም ድረስ ታወርዳቸዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በከፍታ የሚኖሩትን ዝቅ ዝቅ ያደርጋል፤ ከፍ ከፍ ያለችውን ከተማ ያዋርዳል፤ ወደ ምድር ይጥላታል፤ ከትቢያም ጋራ ይደባልቃታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከፍታ የሚኖሩትን ሰዎች ዝቅ ያደርጋል፤ ከፍ ያለችውን ከተማ ያዋርዳል፥ እስከ መሬትም ድረስ ያወርዳታል፥ እስከ ትቢያም ድረስ ይጥላታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከፍተኛ ቦታ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍ ያለችውን ከተማ ያፈራርሳታል። አፈራርሶም ከትቢያ ጋር ይቀላቅላታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በከፍታ የሚኖሩትን ሰዎች ዝቅ ያደርጋል፥ ከፍ ያለችውን ከተማ ያዋርዳል፥ እስከ መሬትም ድረስ ያወርዳታል፥ እስከ አፈርም ድረስ ይጥላታል። |
በዓለም ሁሉ ላይ ክፋትን አዝዛለሁ፤ የኀጢአተኞችንም ኀጢአት እጐበኛለሁ፤ የትዕቢተኞችንም ኵራት እሽራለሁ፤ የጨካኞቹንም ኵራት አዋርዳለሁ።
አንተም በልብህ፦ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፤ ዙፋኔንም ከሰማይ ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤ በሰሜንም ዳርቻ በረዣዥም ተራሮች ላይ እቀመጣለሁ፤
የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፤ እነርሱም ይዋረዳሉ፤
ከተሞችን ትቢያ አደረግህ፤ የተመሸጉ ከተሞችን፥ የኃጥኣንንም መሠረት አፈረስህ፤ ከተሞቻቸውም ለዘለዓለም አይሠሩም።
አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ፤ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ለስላሳና ቅምጥል አትባዪምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ።
አንተም፦ እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች፤ አትነሣምም በል።” የኤርምያስ ቃል እስከዚህ ድረስ ነው።
ቤት። እግዚአብሔር የያዕቆብን መልካም ነገር ሁሉ አሰጠመ፤ አልራራምም፤ በመዓቱ የይሁዳን ሴት ልጅ አንባዎች አፈረሰ፤ ወደ ምድርም አወረዳቸው፤ መንግሥቷንና ግዛቷንም አረከሰ።
ፈረሶቹ አደባባይሽን ይረግጣሉ፤ ሠራዊቶችሽንም በሾተል ይገድሏቸዋል፤ የጸና አርበኛሽንም በምድር ላይ ይጥለዋል።
በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ፤ ያዩህም፥ ይዘብቱብህም ዘንድ በነገሥታት ፊት አሳልፌ ሰጠሁህ።
በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤