ኢሳይያስ 2:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፥ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን” ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙ አሕዛብ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ በጐዳናውም እንድንሄድ፤ መንገዱን ያስተምረናል።” ሕግ ከጽዮን፣ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ ጌታ ተራራ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ብዙ ሕዝቦች እንዲህ ይላሉ፦ “ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ስለሚገኝ ኑ ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤተ መቅደስም እንሂድ፤ እርሱ ፈቃዱን እንድናደርግ ያስተምረናል፤ እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፥ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ ወደ ጎዳናውም እንሄዳለን ይላሉ። |
ፈራጆችሽንም እንደ ቀድሞ፥ አማካሪዎችሽንም እንደ መጀመሪያ ጊዜ አስነሣለሁ፤ ከዚያም በኋላ የጽድቅ ከተማ፥ የታመነችም ጽዮን ርእሰ ከተማ ተብለሽ ትጠሪያለሽ።
በዚያም ቀን የእሴይ ሥር ይቆማል፤ የተሾመውም የአሕዛብ አለቃ ይሆናል፤ አሕዛብም በእርሱ ተስፋ ያደርጋሉ፤ ማረፊያውም የተከበረ ይሆናል።
በዚያም ወራት ከግብፅ ወደ አሦር መንገድ ይሆናል፤ አሦራዊውም ወደ ግብፅ፥ ግብፃዊውም ወደ አሦር ይገባል፤ ግብፃውያንም ለአሦራውያን ይገዛሉ።
ይህ፦ እኔ የእግዚአብሔር ነኝ ይላል፤ ያም በያዕቆብ ስም ይጠራል፤ ይህም፦ እኔ የእግዚአብሔር ነኝ ብሎ በእጁ ይጽፋል፤ በእስራኤልም ስም ይጠራል።”
በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ ስም የሚያስጠራ ቦታን እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋ የዘለዓለም ስምንም እሰጣቸዋለሁ።”
ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና፥ የሚቃጠለው መሥዋዕታቸውና ቍርባናቸውም በመሠዊያዬ ላይ የተመረጠ ይሆናል።
“እናንተ ግን እኔን ተዋችሁኝ፤ ቅዱሱንም ተራራዬን ረሳችሁ፥ ለአጋንንትም ማዕድ አዘጋጃችሁ፤ ዕድል ለተባለ ጣዖትም የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን ቀዳችሁ፤
የእስራኤል ልጆች ቍርባናቸውን በምስጋና ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደሚያመጡ፥ እንዲሁ ለእግዚአብሔር ቍርባን ይሆን ዘንድ ወንድሞቻችሁን ሁሉ፥ በፈረሶችና በሰረገሎች፥ በአልጋዎችና በበቅሎዎች፥ በጠያር ግመሎችም ላይ አድርገው፥ ከአሕዛብ ሁሉ ወደ ተቀደሰችው ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸዋል፥ ይላል እግዚአብሔር።
በበዓል ይምሉ ዘንድ ሕዝቤን እንዳስተማሩ በስሜ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ብለው ይምሉ ዘንድ የሕዝቤን መንገድ ፈጽመው ቢማሩ፥ በዚያ ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ።
“ሞሬታዊው ሚክያስ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ትንቢት ይናገር ነበር፤ ለይሁዳም ሕዝብ ሁሉ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌምም ምድረ በዳ ትሆናለች፤ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል ብሎ ተናገረ።
በኤፍሬም ተራሮች ላይ የሚከራከሩ፦ ተነሡ፤ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ ብለው የሚጠሩባት ቀን ትመጣለችና።”
በእግዚአብሔር ራእይ ወደ እስራኤል ምድር አመጣኝ፤ እጅግም በረዘመ ተራራ ላይ አኖረኝ፤ በዚያም ላይ እንደ ከተማ ሆኖ የተሠራ ነገር በፊቴ ነበረ።
ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመልሰው አምላካቸውን እግዚአብሔርንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በኋለኛውም ዘመን እግዚአብሔርንና ቸርነቱን ያስቡታል።
እንወቀው፤ እናውቀውም ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል፤ እንደ ወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን፤ በምድርም ላይ እንደ መጀመሪያውና እንደ ኋለኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።
ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የእግዚአብሔር ቃል ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፥ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በፍለጋውም እንሄዳለን ይላሉ።
ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድድ ግን ትምህርቴ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ሆነች፥ የምናገረውም ከራሴ እንዳይደለ እርሱ ያውቃል።
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፥ በሰማርያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮች ትሆኑኛላችሁ።”
ስለዚህም ወዲያውኑ ወደ አንተ ላክሁ፤ ወደ እኛ በመምጣትህም መልካም አደረግህ፤ አሁንም እግዚአብሔር ያዘዘህን ሁሉ ልንሰማ እነሆ፥ እኛ ሁላችን በእግዚአብሔር ፊት በዚህ አለን።”
ነገር ግን እንዲህ እላለሁ፤ በውኑ እስራኤል ብቻ አልሰሙምን? መጽሐፍ “ነገራቸው በምድር ሁሉ ተሰማ፤ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ” ብሎ የለምን?
አሕዛብን ያጠፉአቸዋል፤ በዚያም ይጠሩአቸዋል፤ የጽድቅ መሥዋዕትንም ይሠዋሉ፤ የባሕሩም ሀብት፥ በባሕሩ ዳር የሚኖሩ ሰዎችም ገንዘብ ይመግብሃልና፥
“ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር ታደርጉት ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንዳስተምራችሁ ያዘዘው ትእዛዝና ሥርዐት፥ ፍርድም ይህ ነው።