ኢሳይያስም አላቸው፥ “ለጌታችሁ እንዲህ በሉት፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሦር ንጉሥ ብላቴኖች ስለ ተሳደቡት፥ ስለ ሰማኸው ቃል አትፍራ።
ኢሳይያስ 10:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በጽዮን የምትኖር ሕዝቤ ሆይ፥ ከአሦር የተነሣ አትፍራ፤ በበትር ይመቱሃልና፥ የግብፅንም መንገድ ታይ ዘንድ መቅሠፍቴን አመጣብሃለሁና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በጽዮን የምትኖሩ ሕዝቤ ሆይ፤ ግብጽ እንዳደረገብህ ሁሉ በትር ያነሡብህን፣ በሽመል የደበደቡህን አሦራውያንን አትፍራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጌታ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በጽዮን የምትኖሩ ሕዝቤ ሆይ፤ ግብጽ እንዳደረገብህ ሁሉ በትር ያነሡብህን፤ በሽመል የደበደቡህን አሦራውያንን አትፍራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር በጽዮን ለሚኖሩ ሕዝቦቹ እንዲህ ይላል፦ “ምንም እንኳ ከዚያ በፊት ግብጻውያን ጨቊነው እንደ ገዙአችሁ እነርሱም የጨቈኑአችሁ ቢሆንም አሦራውያንን አትፍሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በጽዮን የምትኖር ሕዝቤ ሆይ፥ አሦር በበትር ቢመታህ፥ ግብፅም እንዳደረገህ ዘንጉን ቢያነሣብህ አትፍራው። |
ኢሳይያስም አላቸው፥ “ለጌታችሁ እንዲህ በሉት፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሦር ንጉሥ ብላቴኖች ስለ ተሳደቡት፥ ስለ ሰማኸው ቃል አትፍራ።
ግብፃውያንም፥ የፈርዖን ፈረሶች፥ ሰረገሎቹም፥ ፈረሰኞቹም፥ ሠራዊቱም ሁሉ አሳደዱአቸው፤ በባሕሩ ዳር በብኤልሴፎን ፊት ለፊት ባለው ገላጣ መንደር አንጻርም ሰፍረው አገኙአቸው።
የፈርዖንም ሹሞች፥ “ቀድሞ ታደርጉት እንደ ነበራችሁ እንደ ትናንትናውና እንደ ትናንትና በስቲያው የተቈጠረውን ጡብ ዛሬስ ስለምን አትጨርሱም?” እያሉ በእስራኤል ልጆች ላይ የተሾሙትን አለቆች ይገርፉ ነበር።
እነሆ፥ አምላኬ መድኀኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ክብሬና ዝማሬዬ ነው፤ መድኀኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜአለሁ፤ አልፈራምም።”
ፍልስጥኤም ሆይ፥ ከእባቡ ዘር እፉኝት ይወጣልና፥ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና፥ የኀይላችሁ ቀንበር ተሰብሮአልና ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ።
ቅዱስ ሕዝብ በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን ይኖራል፤ ልቅሶን አልቅሺ፤ ይቅር በለኝም በዪ፤ ልቅሶሽን ባየ ጊዜ ይቅር ይልሻል፤ ሰምቶሻልና።
እግዚአብሔር በላዩ የሚያወርድበት የታዘዘበቱ የበትር ድብደባ ሁሉ በከበሮና በመሰንቆ ይሆናል፤ በጦርነትም ክንዱን አንሥቶ ይዋጋቸዋል።
እናንተ አእምሮ የሌላችሁ፥ ልቡናችሁን አረጋጉ፤ ጽኑ፤ አትፍሩ፤ እነሆ፥ አምላካችን ፍርድን ይመልሳል፤ ይበቀላልም፤ እርሱም መጥቶ ያድነናል።
እግዚአብሔር ስለ እርሱ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ቀላል አድርጋሃለች፤ በንቀትም ሥቃብሃለች፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ራስዋን ነቅንቃብሃለች።
ኢሳይያስ፥ “ለጌታችሁ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሦር ንጉሥ ባሪያዎች ስለ ሰደቡኝ፥ ስለ ሰማኸው ቃል አትፍራ።
ጽድቄን አመጣኋት፤ ከእኔ ዘንድ የምትገኝ መድኀኒትንም አላዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኀኒትን ለእስራኤል ሰጥቻለሁ።
አንቺ ግን ሰማያትን የፈጠረውን፥ ምድርንም የመሠረታትን ፈጣሪሽን እግዚአብሔርን ረስተሻል፤ ያጠፋሽ ዘንድ ባዘጋጀ ጊዜ ከአስጨናቂው ቍጣ የተነሣ ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈርተሻል፤ ይቈጣሽ ዘንድ መክሮአልና፤ አሁን የሚያስጨንቅሽ ቍጣው የት አለ?
እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድም ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።
እንዲህም በለው፥ “ተጠበቅ፥ ዝምም በል፤ አትፍራ፤ ከእነዚህ ከሚጤሱ ሁለት የእንጨት ጠለሸቶች፥ የተነሣ ልብህ አይደንግጥ፤ ከተቈጣሁ በኋላ ይቅር እላለሁና።
በምድያም ጊዜ እንደ ሆነ በላያቸው የነበረው ቀንበር ተነሥቶአልና፥ በጫንቃቸው የነበረውንም፥ የአስጨናቂዎችንም በትር መልሶአልና።