አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።”
ሆሴዕ 6:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ነቢያቶቻችሁን አጨድኋቸው፤ በአፌም ቃል ገደልኋቸው፤ ፍርዴም እንደ ብርሃን ይወጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በነቢያቴ ቈራረጥኋችሁ፤ በአፌም ቃል ገደልኋችሁ፣ ፍርዴም እንደ መብረቅ በላያችሁ አበራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በነቢያት እጅ ቆረጥኋቸው፥ በአፌም ቃላት ገደልኋቸው፤ ፍርዴም እንደ ብርሃን ይወጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በነቢያቴ አማካይነት እንደማጠፋቸው በቃሌም አማካይነት እንደምገድላቸው አስጠነቀቅኋቸው፤ ስለዚህ ፍርዴ እንደ ንጋት ብርሃን ያንጸባርቃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በነቢያት እጅ ቈረጥኋቸው፥ በአፌም ቃል ገደልኋቸው፥ ፍርዴም እንደ ብርሃን ይወጣል። |
አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።”
እርስዋም በደጅ ስትገባ አኪያ የእግርዋን ኮቴ ሰማ፤ እንዲህም አላት፥ “የኢዮርብዓም ሚስት ሆይ፥ ግቢ! ስለምንስ ራስሽን ለወጥሽ? እኔም የሚያስጨንቅ ወሬ ይዤ ወደ አንቺ ተልኬአለሁ።
በገለዓድ ቴስባን የነበረው ቴስብያዊው ነቢዩ ኤልያስ አክዓብን፥ “በፊቱ የቆምሁት የኀያላን አምላክ የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! ከአፌ ቃል በቀር በእነዚህ ዓመታት ዝናብም ጠልም አይወርድም” አለው።
ከአዛሄልም ሰይፍ የሚያመልጠውን ሁሉ ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩም ሰይፍ የሚያመልጠውን ሁሉ ኤልሳዕ ይገድለዋል።
ኤልያስም፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቅ ዘንድ መልእክተኞችን ለምን ላክህ? በእስራኤል ዘንድ አምላክ ስለሌለ ነውን? እንደዚህ አይደለም፤ ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም” አለው።
ከነቢዩም ከኤልያስ እንዲህ የሚል ጽሕፈት መጣበት፥ “የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአባትህ በኢዮሣፍጥ መንገድ፥ በይሁዳም ንጉሥ በአሳ መንገድ አልሄድህምና፥
“ሰለዚህ እናንተ አእምሮ ያላቸሁ ሰዎች ስሙኝ፤ በእግዚአብሔርም ዘንድ ትበድሉ ዘንድ አትውደዱ። ሁሉን በሚችል አምላክ ፊትም ጻድቁን አታውኩት።
ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፤ በአፉም ቃል ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ኀጢአተኛውን ያጠፋዋል።
በኀይልህ ጩኽ፤ አትቈጥብ፤ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፤ ለሕዝቤ ኀጢአታቸውን፥ ለያዕቆብ ቤትም በደላቸውን ንገር።
እነሆ ትነቅልና ታፈርስ ዘንድ፥ ታጠፋና ትገለብጥ ዘንድ፥ ትሠራና ትተክል ዘንድ በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ዛሬ ሾሜሃለሁ።”
እነሆ በምድሪቱ ሁሉ ላይ፥ በይሁዳም ነገሥታት በአለቆችዋና በካህናቷ ላይ፥ በምድሪቱም ሕዝብ ላይ እንደ ተመሸገች ከተማ፥ እንደ ብረትም ዓምድ፥ እንደ ናስም ቅጥር ዛሬ አድርጌሃለሁ።
አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ፥ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡትን ነገሥታት፥ ካህናቱንም፥ ነቢያቱንም፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን ሁሉ በስካር እሞላቸዋለሁ።
ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እንደዚህ ያለ ቃል ተናግራችኋልና እነሆ በአፍህ ውስጥ ቃሌን እሳት፥ ይህንም ሕዝብ እንጨት አደርጋለሁ፤ ትበላቸውማለች።
“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ኀይል ዋይ በል፤ እርስዋንና የብርቱዎቹን አሕዛብ ሴቶች ልጆች ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ታችኛው ምድር ጣላቸው።
ያየሁትም ራእይ ከተማዪቱን ለማጥፋት በመጣሁ ጊዜ እንደ አየሁት ራእይ ነበረ፤ ራእዩም በኮቦር ወንዝ እንደአየሁት ራእይ ነበረ፤ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ።
እግዚአብሔር በውስጥዋ ጻድቅ ነው፣ ክፋትን አያደርግም፣ ፍርዱን በየማለዳው ወደ ብርሃን ያወጣል፥ ሳያወጣውም አይቀርም፣ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም።
ነገር ግን ልቡናህን እንደ ማጽናትህ፥ ንስሓም እንደ አለመግባትህ መጠን የእግዚአብሔር እውነተና ፍርድ በሚገለጥበት ቀን መቅሠፍትን ለራስህ ታከማቻለህ።
የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፤ የሚሠራም ሁለት ልሳን ካለው ሰይፍም ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፤ ነፍስንና መንፈስንም፥ ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፤ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “በድለኻል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዙን አልጠበቅህምና፤ ዛሬ እግዚአብሔር መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም አጽንቶልህ ነበር።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።
ሳሙኤልም፥ “የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ” አለ። አጋግም እየተንቀጠቀጠ ወደ እርሱ መጣ። አጋግም፥ “በውኑ ሞት እንደዚህ መራራ ነውን?” አለ።
ሳሙኤልም አጋግን፥ “ሰይፍህ ሴቶችን ልጆች አልባ እንዳደረገቻቸው እንዲሁ እናትህ በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች” አለ፥ ሳሙኤልም አጋግን በእግዚአብሔር ፊት በጌልጌላ ወጋው።