ሙሴም አለው፥ “እኛ ከታናናሾቻችንና ከሽማግሌዎቻችን፥ ከወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ጋር እንሄዳለን፤ በጎቻችንንና ላሞቻችንንም እንወስዳለን። የአምላካችን የእግዚአብሔር በዓል ነውና።”
ሆሴዕ 5:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርንም ለመሻት ከበጎቻቸውና ከላሞቻቸው ጋር ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተለይቶአልና አያገኙትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን ለመሻት፣ የበግና የፍየል መንጋ እንዲሁም የቀንድ ከብቶቻቸውን ነድተው ሲሄዱ፣ እርሱ ስለ ተለያቸው፣ ሊያገኙት አይችሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታንም ለመሻት በጎቻቸውንና በሬዎቻቸውን ነድተው ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተመልሶአልና አያገኙትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሥዋዕት አድርገው ለማቅረብ በጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን ነድተው እግዚአብሔርን ለመፈለግ ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ስለ ተለያቸው አያገኙትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርንም ለመሻት በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን ነድተው ይሄዳሉ፥ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተመልሶአልና አያገኙትም። |
ሙሴም አለው፥ “እኛ ከታናናሾቻችንና ከሽማግሌዎቻችን፥ ከወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ጋር እንሄዳለን፤ በጎቻችንንና ላሞቻችንንም እንወስዳለን። የአምላካችን የእግዚአብሔር በዓል ነውና።”
ለልጅ ወንድሜ ከፈትሁለት፥ ልጅ ወንድሜ ግን ሂዶ ነበር። ነፍሴ ከቃሉ የተነሣ ደነገጠች፤ ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፤ ጠራሁት፥ አልመለሰልኝም።
በሬን የሚሠዋልኝ ኃጥእ ውሻን እንደሚያርድልኝ ነው፤ የእህልን ቍርባን የሚያቀርብም የእሪያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፤ ዕጣንንም ለመታሰቢያ የሚያጥን አምላክን እንደሚፀርፍ ነው፤ እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ሊያመልጡት የማይችሉትን ክፉ ነገር በዚህ ሕዝብ ላይ አመጣለሁ፤ ወደ እኔም ይጮኻሉ፤ እኔ ግን አልሰማቸውም።
አንተም ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፤ በመከራቸው ቀን ወደ እኔ በጮኹ ጊዜ አልሰማቸውምና ስለ እነርሱ አትጸልይ፤ በምልጃና በጸሎት አትማልድ።
ቢጾሙ ጸሎታቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ቢያቀርቡም ደስ አልሰኝባቸውም፤ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ።”
ስለዚህ እኔ ደግሞ በመዓት እሠራለሁ፤ ዐይኔ አይራራም፤ እኔም ይቅርታ አላደርግም፤ ወደ ጆሮዬም በታላቅ ድምፅ ቢጮኹ አልሰማቸውም” አለኝ።
እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የሚያደርጉትን ከመቅደሴ ያርቁኝ ዘንድ የእስራኤል ቤት በዚህ የሚያደርጉትን፥ ታላቁን ርኵሰት ታያለህን? ደግሞም ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ታላቅ ርኵሰት ታያለህ” አለኝ።
መሥዋዕትንም ቢሠዉ፥ ሥጋንም ቢበሉ፤ እግዚአብሔር አይቀበላቸውም፤ አሁንም በደላቸውን ያስባል፤ በኀጢአታቸውም ይበቀላቸዋል፤ እነርሱም ወደ ግብፅ ይመለሳሉ፤ በአሦርም ርኩስ ነገርን ይበላሉ።
ከባሕርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰሜንም እስከ ምሥራቅ ድረስ ይቅበዘበዛሉ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል ለመሻት ይርዋርዋጣሉ፤ አያገኙትምም።
በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።