Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




አሞጽ 8:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከባ​ሕ​ርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰ​ሜ​ንም እስከ ምሥ​ራቅ ድረስ ይቅ​በ​ዘ​በ​ዛሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ለመ​ሻት ይር​ዋ​ር​ዋ​ጣሉ፤ አያ​ገ​ኙ​ት​ምም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል በመሻት፣ ከባሕር ወደ ባሕር፣ ከሰሜን ወደ ምሥራቅ ይንከራተታሉ፤ ነገር ግን አያገኙትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከባሕርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰሜንም እስከ ምሥራቅ ድረስ ይቅበዘበዛሉ፤ የጌታን ቃል ለመሻት ይሯሯጣሉ፥ ነገር ግን አያገኙትም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሕዝቡ ሁሉ ከሰሜን እስከ ደቡብ፥ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የእግዚአብሔርንም ቃል ለማግኘት በሁሉ ቦታ ይንከራተታሉ፤ ነገር ግን አያገኙም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከባሕርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰሜንም እስከ ምሥራቅ ድረስ ይቅበዘበዛሉ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ለመሻት ይርዋርዋጣሉ፥ አያገኙትምም።

Ver Capítulo Copiar




አሞጽ 8:12
14 Referencias Cruzadas  

ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፤ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል።


በክፉዎች ዘንድ ጥበብን ትፈልጋለህ፥ አታገኛትምም፤ ዕውቀት ግን በብልሆች ዘንድ በቀላሉ ይገኛል።


ቍር​ባ​ና​ች​ሁን በአ​ቀ​ረ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም በእ​ሳት ባሳ​ለ​ፋ​ችሁ ጊዜ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በዐ​ሳ​ባ​ችሁ ሁሉ ረከ​ሳ​ችሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እኔስ እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለ​ሁን? እኔ ሕያው ነኝ! አል​መ​ል​ስ​ላ​ች​ሁም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔን ትጠ​ይቁ ዘንድ መጥ​ታ​ች​ኋ​ልን? እኔ ሕያው ነኝ! አል​መ​ል​ስ​ላ​ች​ሁም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ብላ​ቴ​ናው ሳሙ​ኤ​ልም በዔሊ ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግል ነበር፤ በዚ​ያም ዘመን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ክቡር ነበረ፤ ራእ​ይም አይ​ገ​ለ​ጥም ነበር።


ግን በጠራችሁኝ ጊዜ እኔ አልሰማችሁም፤ ክፉዎች ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለመ​ሻት ከበ​ጎ​ቻ​ቸ​ውና ከላ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ይሄ​ዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእ​ነ​ርሱ ተለ​ይ​ቶ​አ​ልና አያ​ገ​ኙ​ትም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios