Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 7:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ አታ​ገ​ኙ​ኝ​ምም፤ እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በ​ትም እና​ንተ መም​ጣት አት​ች​ሉም።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤ እኔ ወዳለሁበትም ልትመጡ አትችሉም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝም፤ እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤ እኔ ወዳለሁበት፥ እናንተ መምጣት አትችሉም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝም፤ እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም” አለ።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 7:34
12 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለመ​ሻት ከበ​ጎ​ቻ​ቸ​ውና ከላ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ይሄ​ዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእ​ነ​ርሱ ተለ​ይ​ቶ​አ​ልና አያ​ገ​ኙ​ትም።


እላችኋለሁና፥ ‘በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤’ እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።”


ከሄ​ድ​ሁና ቦታ ካዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላ​ች​ሁም ዳግ​መኛ እመ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተም እኔ በአ​ለ​ሁ​በት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወ​ስ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ው​ነ​ትና የሕ​ይ​ወት መን​ገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካል​ሆነ በቀር ወደ አብ የሚ​መጣ የለም።


አባት ሆይ፥ የሰ​ጠ​ኸኝ እነ​ዚህ እኔ ባለ​ሁ​በት አብ​ረ​ውኝ ይኖሩ ዘን​ድና የሰ​ጠ​ኸ​ኝን ክብ​ሬን ያዩ ዘንድ እወ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር ወድ​ደ​ኸ​ኛ​ልና።


‘ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ አታ​ገ​ኙ​ኝ​ምም፤ እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እና​ንተ መም​ጣት አት​ች​ሉም’ የሚ​ለን ይህ ነገር ምን​ድን ነው?”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos