እርሱም በዘገየ ጊዜ እነዚያ መላእክት የእርሱን እጅ፥ የሚስቱንም እጅ፥ የሁለቱን ሴቶች ልጆቹንም እጅ ይዘው አወጡአቸው፤ እግዚአብሔር ራርቶላቸዋልና።
ዕብራውያን 8:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጃቸውን ይዤ ከምድረ ግብፅ ባወጣኋቸው ጊዜ ለአባቶቻቸው እንደ ገባሁት እንደዚያ ያለ ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልኖሩምና፤ እኔም ቸል ብያቸዋለሁና” ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከግብጽ አወጣቸው ዘንድ፣ እጃቸውን ይዤ በመራኋቸው ጊዜ፣ ከአባቶቻቸው ጋራ እንደገባሁት ኪዳን አይደለም፤ ምክንያቱም እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑም፤ እኔም ከእነርሱ ዘወር አልሁ፤ ይላል ጌታ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግብጽ ምድር ለማውጣት እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና እኔም ቸል አልኳቸው፤ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ቃል ኪዳን እጃቸውን ይዤ ከግብጽ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ቃል ኪዳን ያለ አይደለም፤ እነርሱ በቃል ኪዳኔ ስላልጸኑ እኔም ችላ አልኳቸው ይላል ጌታ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግብፅ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው ይላል ጌታ። |
እርሱም በዘገየ ጊዜ እነዚያ መላእክት የእርሱን እጅ፥ የሚስቱንም እጅ፥ የሁለቱን ሴቶች ልጆቹንም እጅ ይዘው አወጡአቸው፤ እግዚአብሔር ራርቶላቸዋልና።
እነሆ፥ እግዚአብሔር የዋሁን ሰው አይጥለውም፥ የኀጢኣተኞችንም እጅ አያበረታም። የዝንጉዎችንም መባ አይቀበልም።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ እኔ በሕዝብህ ፊት ሁሉ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ በምድር ሁሉ፥ በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እንደ እርሱ ያለ ከቶ ያልተደረገውን ታላቅ ተአምራትን አደርግልሃለሁ፤ እኔም የማደርግልህ ነገር ድንቅ ነውና አንተ በመካከሉ ያለህበት ይህ ሕዝብ ሁሉ የእግዚአብሔርን ሥራ ያያል።
በልጅ ወንድምዋ ላይ ተደግፋ እንደ ማለዳ ደምቃና አብርታ የምትወጣ ይህች ማን ናት? ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ ከእንኮይ በታች አስነሣሁህ፤ በዚያ እናትህ አማጠችህ፥ በዚያም ወላጅ እናትህ ወለደችህ።
በመልእክተኛም አይደለም፤ በመልአክም አይደለም፤ እርሱ ራሱ ያድናቸዋል እንጂ። እርሱ ይወዳቸዋልና፥ ይራራላቸዋልምና እርሱ ተቤዣቸው፤ ተቀበላቸውም፤ በዘመናቸውም ሁሉ ለዘለዓለም አከበራቸው።
ከግብፅ ሀገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር።
ዔ። የእግዚአብሔር ፊት ክፍላቸው ነበረ። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ አይመለከታቸውም፤ የካህናቱን ፊት አላፈሩም፤ ሽማግሌዎቹንም አላከበሩም።
“ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ አንቺ ቃል ኪዳንን በማፍረስ መሐላን የናቅሽ ሆይ! አንቺ እንዳደረግሽ እኔ ደግሞ አደርግብሻለሁ።
በአንቺ ዘንድ በአለፍሁና በአየሁሽ ጊዜ፥ እነሆ ጊዜሽ እንደ ደረሰ፥ በአንቺም የሚያድሩ ሰዎች ጊዜ እንደ ደረሰ አየሁ። እጆችን በላይሽ ዘረጋሁ፤ ኀፍረተ ሥጋሽንም ከደንሁ፤ ማልሁልሽም፤ ከአንቺም ጋራ ቃል ኪዳን ገባሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ አንቺም ለእኔ ሆንሽ።
የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁንና የእህሉን ቍርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ የድኅነት መሥዋዕታችሁንም አልመለከትም።
ይህንም ደግሞ አድርጋችኋል፣ እግዚአብሔር ቍርባኑን ዳግመኛ እንዳይመለከት፥ ከእጃችሁም በደስታ እንዳይቀበለው መሠዊያውን በእንባና በልቅሶ በኅዘንም ትከድናላችሁ።
እነሆ፥ አሁን የእግዚአብሔር እጅ በአንተ ላይ ነው፤ ዕውርም ትሆናለህ፤ እስከ ጊዜውም ፀሐይን አታይም፤” ወዲያውኑም ታወረ፤ ጨለማም ዋጠው፤ የሚመራውም ፈለገ።
ሳውልም ከምድር ተነሣ፤ ነገር ግን ዐይኖቹ ተገልጠው ሳሉ የሚያየው ነገር አልነበረም፤ እየመሩም ወደ ደማስቆ አገቡት።
እግዚአብሔር በኮሬብ ካደረገው ቃል ኪዳን ሌላ በሞዓብ ምድር ከእስራኤል ልጆች ጋር ያደርገው ዘንድ ሙሴን ያዘዘው የቃል ኪዳኑ ቃሎች እነዚህ ናቸው።
ይኸውም አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ዛሬ በሚያደርገው ቃል ኪዳንና አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር በተማማለው መሐላ ትገባ ዘንድ ነው።
ሰዎችም እንዲህ ይላሉ፦ የአባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ከግብፅ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከአባቶቻቸው ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን ስለተዉ፥