Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 63:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኛም አይ​ደ​ለም፤ በመ​ል​አ​ክም አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ራሱ ያድ​ና​ቸ​ዋል እንጂ። እርሱ ይወ​ዳ​ቸ​ዋ​ልና፥ ይራ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ል​ምና እርሱ ተቤ​ዣ​ቸው፤ ተቀ​በ​ላ​ቸ​ውም፤ በዘ​መ​ና​ቸ​ውም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አከ​በ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በጭንቃቸው ሁሉ ተጨነቀ፤ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በምሕረቱ ዋጃቸው፤ በቀደመው ዘመን ሁሉ አነሣቸው፤ ተሸከማቸውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በችግራቸው ጊዜ ሁሉ ያዳናቸው በመልእክተኛ ወይም በመልአክ አማካይነት ሳይሆን እርሱ በመካከላቸው በመገኘት ነው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ታደጋቸው፤ እርሱም በቀድሞ ዘመናት ሁሉ አንሥቶ ልጁን እንደሚሸከም ሰው ተንከባከባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፥ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 63:9
45 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እኔ በፊ​ትህ እሄ​ዳ​ለሁ፥ አሳ​ር​ፍ​ህ​ማ​ለሁ” አለው።


እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ያን​ጊ​ዜም የጴ​ጥ​ሮስ ልቡና ተመ​ለ​ሰ​ለ​ትና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ኩን ልኮ ከሄ​ሮ​ድስ እጅና የአ​ይ​ሁድ ሕዝብ ይጠ​ብ​ቁት ከነ​በ​ረው ሁሉ እንደ አዳ​ነኝ በእ​ው​ነት አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ።


ወደ​ዚ​ህም ስፍራ እስ​ክ​ት​መጡ ድረስ በሄ​ዳ​ች​ሁ​በት መን​ገድ ሁሉ፥ ሰው ልጁን እን​ዲ​መ​ግብ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድረ በዳ እን​ደ​መ​ገ​ባ​ችሁ እና​ንተ አይ​ታ​ች​ኋል።


በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን፥ እንደ ንስር ክን​ፍም እንደ ተሸ​ከ​ም​ኋ​ችሁ፥ ወደ እኔም እን​ዳ​መ​ጣ​ኋ​ችሁ አይ​ታ​ች​ኋል።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሠራ​ዊት ፊት ይሄድ የነ​በ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ፈቀቅ ብሎ በኋ​ላ​ቸው ሄደ፤ የደ​መ​ና​ውም ዐምድ ከፊ​ታ​ቸው ፈቀቅ ብሎ በኋ​ላ​ቸው ቆመ፤


ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አስ​ወ​ገዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ብቻ አመ​ለኩ፤ ደስም አሰ​ኙት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከሥ​ቃይ የተ​ነሣ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን አጥ​ተው ነበር።


ሊቀ ካህ​ና​ታ​ችን ለድ​ካ​ማ​ችን መከራ መቀ​በ​ልን የማ​ይ​ችል አይ​ደ​ለ​ምና፤ ነገር ግን ከብ​ቻዋ ከኀ​ጢ​አት በቀር እኛን በመ​ሰ​ለ​በት ሁሉ የተ​ፈ​ተነ ነው።


ከከፉ ነገር ሁሉ የአ​ዳ​ነኝ መል​አክ እርሱ እነ​ዚ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ይባ​ርክ፤ ስሜም፥ የአ​ባ​ቶች የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐ​ቅም ስም በእ​ነ​ርሱ ይጠራ፤ በም​ድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤”


“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።


እርሱ ራሱ ተፈ​ትኖ መከ​ራን ስለ ተቀ​በለ የሚ​ፈ​ተ​ኑ​ትን ሊረ​ዳ​ቸው ይች​ላ​ልና።


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ከክብሩ በኋላ ወደ በዘበዙአችሁ አሕዛብ ልኮኛል፣ የሚነካችሁ የዓይኑን ብሌን የሚነካ ነውና።


በም​ድረ በዳ በማ​ኅ​በሩ መካ​ከል የነ​በረ እርሱ ነው፤ በደ​ብረ ሲና ከአ​ነ​ጋ​ገ​ረው መል​አ​ክና፤ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ጋር ለእኛ ሊሰ​ጠን የሕ​ይ​ወ​ትን ቃል የተ​ቀ​በለ እርሱ ነው።


ነገር ግን የይ​ሁ​ዳን ልጆች ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ በቀ​ስት ወይም በሰ​ይፍ፥ ወይም በጦር፥ ወይም በሠ​ረ​ገላ፥ ወይም በፈ​ረ​ሶች፥ ወይም በፈ​ረ​ሰ​ኞች የማ​ድ​ና​ቸው አይ​ደ​ለም” አለው።


በአ​ገ​ኛ​ትም ጊዜ ደስ ብሎት በት​ከ​ሻው ላይ ይሸ​ከ​ማ​ታል።


ያን ጊዜ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም፤’ ብሎ ይመልስላቸዋል።


ንጉሡም መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት፤’ ይላቸዋል።


ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳ​ን​ዶቹ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ ተፈ​ታ​ተ​ኑት፥ ነዘር እባ​ብም እንደ አጠ​ፋ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አን​ፈ​ታ​ተን።


በም​ድር ላይም ወደቀ፤ ወዲ​ያ​ውም፥ “ሳውል፥ ሳውል፥ ለምን ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለህ?” የሚ​ለ​ውን ቃል ሰማ።


እር​ሱም፥ “አንተ ከእኛ ጋር ካል​ወ​ጣ​ህስ፥ ከዚህ አታ​ው​ጣን።


አባ​ቶ​ች​ህን ወድ​ዶ​አ​ልና ከእ​ነ​ርሱ በኋላ ዘራ​ቸ​ውን መረጠ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ሆኖ በታ​ላቅ ኀይሉ ከግ​ብፅ አወ​ጣህ፤


በኀ​ይል ከእ​ርሱ ጋር እኩል የሚ​ሆን፥ እው​ነ​ት​ንም የሚ​ፈ​ርድ ሌላ አና​ገ​ኝም። እርሱ እን​ደ​ማ​ይ​ሰማ ታስ​ባ​ለ​ህን?


አሁ​ንም ያዕ​ቆብ ሆይ፥ የፈ​ጠ​ረህ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሆይ፥ የሠ​ራህ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ተቤ​ዥ​ች​ሃ​ለ​ሁና አት​ፍራ፤ በስ​ም​ህም ጠር​ቼ​ሃ​ለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ።


በፊቴ የከ​በ​ር​ህና የተ​መ​ሰ​ገ​ንህ ነህና፥ እኔም ወድ​ጄ​ሃ​ለ​ሁና ስለ​ዚህ ብዙ ሰዎ​ችን ለአ​ንተ ቤዛ፥ አለ​ቆ​ች​ንም ለራ​ስህ እሰ​ጣ​ለሁ።


ከባ​ቢ​ሎን ውጡ፤ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ኰብ​ልሉ፤ በእ​ል​ልታ ድምፅ ተና​ገሩ፤ ይህም ይሰማ፤ እስከ ምድ​ርም ዳርቻ ድረስ አው​ሩና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባር​ያ​ውን ያዕ​ቆ​ብን ታድ​ጎ​ታል” በሉ።


ባሕ​ሩን ያደ​ረ​ቅሽ፥ ጥል​ቁ​ንም ውኃ ያደ​ረ​ቅ​ሽው፥ የዳ​ኑ​ትም ይሻ​ገሩ ዘንድ ጥል​ቁን ባሕር ጥር​ጊያ ጎዳና ያደ​ረ​ግሽ አይ​ደ​ለ​ሽ​ምን?


የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ፍር​ስ​ራ​ሾች ደስ ይበ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ብሎ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን አድ​ኖ​አ​ታ​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ምድሩ ቀና፤ ለሕ​ዝ​ቡም ራራ​ለት።


በቸ​ር​ነ​ትህ የተ​ቤ​ዠ​ሃ​ቸ​ውን ሕዝ​ብ​ህን መራህ፤ በኀ​ይ​ልህ ወደ ቅዱስ ማደ​ሪ​ያህ ጠራ​ሃ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios