ዕንባቆም 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከክፉ እንዲድን ጐጆውን በከፍታ ላይ ያደርግ ዘንድ ለቤቱ ክፉ ትርፍን ለሚሰበስብ ወዮለት! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በተጭበረበረ ትርፍ መኖሪያውን ለሚገነባ፣ ከጠላት እጅ ለማምለጥ፣ ቤቱን በከፍታ ላይ ለሚሠራ ወዮለት! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከክፉ ለመታደግ ጐጆውን በከፍታ ላይ በማድረግ፥ ለቤቱ ክፉ ትርፍን የሚሰበስብ ወዮለት! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አደጋ እንዳይደርስበት መኖሪያውን ከፍ ባለ አምባ ላይ የሚመሠርትና በሕገ ወጥ ገቢ ቤቱን ለሚሠራ ወዮለት! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከክፉ እንዲድን ጐጆውን በከፍታ ላይ ያደርግ ዘንድ ለቤቱ ክፉ ትርፍን ለሚሰበስብ ወዮለት! |
እናንተም “ከሲኦል ጋር ተማምለናል፤ ከሞትም ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፤ ሐሰትንም መሸሸጊያን አድርገናልና፥ በሐሰትም ተሰውረናልና፥ ዐውሎ ነፋስም ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም” ትላላችሁና፥
ከጎረቤቶቻቸው እርሻ ይወስዱ ዘንድ፥ ምድርንም ለብቻቸው ይይዟት ዘንድ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ፥ እርሻንም ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው!
ቆቅ ጮኸች፤ ያልወለደችውንም ዐቀፈች፤ በዐመፅ ባለጠግነትን የሚሰበስብ ሰውም እንደዚሁ ነው፤ በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፤ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።
አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፥ በዝግባ ዛፍም ውስጥ የምታለቅሺ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ትጨነቂያለሽ!
በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ድፍረትህና የልብህ ኵራት አነሣሥተውሃል። ቤትህንም ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
ባቢሎንም ወደ ሰማይ ብትወጣ፥ ቅፅሮችዋንም በኀይልዋ ብታጸና፥ ከእኔ ዘንድ አጥፊዎች ይመጡባታል፥ ይላል እግዚአብሔር።
በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ የስስትን ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈስሱ ዘንድ፥ ነፍሶችንም ያጠፉ ዘንድ እንደሚናጠቁ ተኵላዎች ናቸው።