እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ፈጠረው፤ በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
ዘፍጥረት 6:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም እነሆ፥ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፤ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለባቸውን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ለማጥፋት እነሆ፤ በምድር ላይ የጥፋት ውሃ አወርዳለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሁሉ ይጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ እኔ ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት፥ በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፥ በምድር ያለ ሁሉ ይጠፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ ከሰማይ በታች ሕይወት ያለውን ነገር ሁሉ ከምድር ላይ ለማጥፋት የጥፋት ውሃ አመጣለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ይጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም እነሆ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኂን አመጣለሁ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል። |
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ፈጠረው፤ በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
እግዚአብሔር አምላክም ኖኅን አለው፥ “የሰው ሁሉ ጊዜው በፊቴ ደርሶአል፤ ከእነርሱ የተነሣ ምድር በግፍ ተመልታለችና፤ እኔም እነሆ፥ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ።
ለመርከቢቱም መስኮትን ታደርጋለህ፤ ከቁመቷም ክንድ ሙሉ ትተህ ጨርሳት፤ የመርከቢቱንም በር በጎንዋ አድርግ፤ ታችኛውንም፥ ሁለተኛውንም፥ ሦስተኛውንም ደርብ ታደርግላታለህ።
እግዚአብሔርም፥ “የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፤ ከሰው እስከ እንስሳና አራዊት፥ እስከ ተንቀሳቃሽም፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና” አለ።
የጥፋት ውኃ በምድር ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ነበረ፤ ውኃውም በዛ፤ መርከቢቱንም አነሣ፤ ከምድርም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለች።
ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁና፤ የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ሁሉ ላይ አጠፋለሁና።”
እነሆም፥ እኔ የፈርዖንንና የግብፃውያንን ልብ አጸናለሁ፤ በኋላቸውም ይገባሉ፤ በፈርዖንና በሠራዊቱም ሁሉ፥ በሰረገሎቹም፥ በፈረሰኞቹም ላይ እከብራለሁ።
እኔ ነኝ፤ የማጽናናሽ እኔ ነኝ፤ አንቺ እንግዲህ ዕወቂ፤ ማንን ፈራሽ? የሚሞተውን ሰው እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ ነውን?
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ራሴ በአንቺ ላይ ነኝ፤ በአሕዛብም ፊት ፍርድን በመካከልሽ አደርጋለሁ።
ለእስራኤል ተራሮች የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ በላቸው፤ ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኮረብቶች፥ ለምንጮችና ለሸለቆዎች እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ሰይፍን አመጣባችኋለሁ፤ የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አጠፋለሁ።
እኔም ለኤፍሬም እንደ ነብር፥ ለይሁዳም ቤት እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁና፤ እኔም ነጥቄ እሄዳለሁ፤ እወስድማለሁ፤ የሚያድናቸውም የለም።
አዳራሹን በሰማይ የሠራ፥ ትእዛዙንም በምድር ላይ የመሠረተ፥ የባሕርንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት የሚያፈስሰው እርሱ ነው፤ ስሙም ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር ነው።
ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ ሲበሉና ሲጠጡ፥ ሲያገቡና ሲጋቡ ነበረ፤ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን አንድ አድርጎ አጠፋ።
ኀጢአትም ሞትን እንደ አነገሠችው እንዲሁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ጸጋ ጽድቅን ለዘለዓለም ሕይወት ታነግሠዋለች።
እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገድላለሁ፤ አድንማለሁ፤ እኔ እገርፋለሁ፤ ይቅርም እላለሁ፤ ከእጄም የሚያመልጥ የለም።
ኖኅም ስለማይታየው ነገር የነገሩትን ባመነ ጊዜ ፈራ፤ ቤተ ሰቡንም ያድን ዘንድ ክፍል ያላት መርከብን ሠራ፤ በዚህም ዓለምን አስፈረደበት፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።