Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 7:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከሰ​ባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በም​ድር ላይ ዝናብ አዘ​ን​ባ​ለ​ሁና፤ የፈ​ጠ​ር​ሁ​ት​ንም ፍጥ​ረት ሁሉ ከም​ድር ሁሉ ላይ አጠ​ፋ​ለ​ሁና።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ፤ የፈጠርሁትንም ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ገጽ አጠፋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ላይ ለማጥፋት ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የፈጠርኩትን ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ገጽ ላይ ለማጥፋት ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ዝናብ አዘንባለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከሰባት ቀን በኍላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁና፤ የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ላይ አጠፉለሁና።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 7:4
23 Referencias Cruzadas  

የሜዳ ቍጥ​ቋጦ ሁሉ በም​ድር ላይ ከመ​ኖሩ በፊት፥ የሜ​ዳ​ውም ቡቃያ ሁሉ ከመ​ብ​ቀሉ በፊት፥ አዳ​ምም ከመ​ፈ​ጠሩ በፊት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ በም​ድር ላይ አላ​ዘ​ነ​በም ነበር፤ ምድ​ር​ንም የሚ​ሠ​ራ​ባት ሰው አል​ነ​በ​ረም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ኖኅን አለው፥ “የሰው ሁሉ ጊዜው በፊቴ ደር​ሶ​አል፤ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ነሣ ምድር በግፍ ተመ​ል​ታ​ለ​ችና፤ እኔም እነሆ፥ ከም​ድር ጋር አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እኔም እነሆ፥ ከሰ​ማይ በታች የሕ​ይ​ወት ነፍስ ያለ​ውን ሥጋ ሁሉ ለማ​ጥ​ፋት በም​ድር ላይ የጥ​ፋት ውኃን አመ​ጣ​ለሁ፤ በም​ድር ያለው ሁሉ ይጠ​ፋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “መን​ፈሴ በሰው ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ኖ​ርም፤ እነ​ርሱ ሥጋ ናቸ​ውና፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም መቶ ሃያ ዓመት ይሆ​ናል” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የፈ​ጠ​ር​ሁ​ትን ሰው ከም​ድር ላይ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ከሰው እስከ እን​ስ​ሳና አራ​ዊት፥ እስከ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሽም፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠ​ር​ኋ​ቸው ተጸ​ጽ​ቻ​ለ​ሁና” አለ።


ከሰ​ባት ቀን በኋ​ላም የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ ሆነ።


ዝና​ቡም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በም​ድር ላይ ሆነ።


የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ነበረ፤ ውኃ​ውም በዛ፤ መር​ከ​ቢ​ቱ​ንም አነሣ፤ ከም​ድ​ርም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለች።


ከን​ጹሕ የሰ​ማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባ​ትና እን​ስት፥ ንጹሕ ካል​ሆነ የሰ​ማይ ወፍም ሁለት ሁለት ተባ​ትና እን​ስት እያ​ደ​ረ​ግህ በም​ድር ላይ ለም​ግ​ብና ለዘር ይቀር ዘንድ ለአ​ንተ ትወ​ስ​ዳ​ለህ።


ከዚ​ያም በኋላ ደግሞ ሰባት ቀን ቆይቶ፥ ርግ​ብን እን​ደ​ገና ከመ​ር​ከብ ላካት።


ደግሞ ሰባት ቀን ቆይቶ፥ ርግ​ብን ላካት፤ ዳግ​መ​ኛም ወደ እርሱ አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም።


የቀ​ላ​ዩም ምን​ጮች፥ የሰ​ማ​ይም መስ​ኮ​ቶች ተደ​ፈኑ፤ ዝና​ብም ከሰ​ማይ ተከ​ለ​ከለ፤


ጊዜ​ያ​ቸው ሳይ​ደ​ርስ ተነ​ጠቁ፤ መሠ​ረ​ታ​ቸ​ውም እንደ ፈሳሽ ውኃ ፈሰሰ።


ለነ​ፋስ ሚዛ​ንን ለው​ሆ​ችም መስ​ፈ​ሪ​ያን አደ​ረገ።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ከገጸ ምድር አስ​ወ​ግ​ድ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐመ​ፅን ተና​ግ​ረ​ሃ​ልና በዚህ ዓመት ትሞ​ታ​ለህ” አለው።


መከር ሳይ​ደ​ርስ ገና ከሦ​ስት ወር በፊት ዝና​ብን ከለ​ከ​ል​ኋ​ችሁ፤ በአ​ን​ድም ከተማ ላይ አዘ​ነ​ብሁ፤ በሌ​ላ​ውም ከተማ ላይ እን​ዳ​ይ​ዘ​ንብ አደ​ረ​ግሁ፤ በአ​ንድ ወገን ዘነበ፤ ያል​ዘ​ነ​በ​በ​ትም ወገን ደረቀ።


ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጐናጸፋል፤ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም፤ በአባቴና በመላእክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos