Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 26:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እኔ ደግሞ አግ​ድሜ በቍጣ እሄ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እንደ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም ሰባት እጥፍ እቀ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 እኔም በቍጣዬ እመጣባችኋለሁ፤ ስለ ኀጢአታችሁም እኔው ራሴ ሰባት ዕጥፍ እቀጣችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 እኔ ደግሞ በቁጣ እናንተን በመቃወም እሄዳለሁ፤ እኔም ስለ ኃጢአታችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በእናንተ ላይ በቊጣ እነሣለሁ፤ በእናንተ ላይ የማመጣውንም ቅጣት ካለፈው ሰባት ጊዜ የበለጠ እንዲሆን አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እኔ ደግሞ በቍጣ እሄድባችኋለሁ፤ ስለ ኃጢአታችሁም ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 26:28
16 Referencias Cruzadas  

ጠላ​ቶ​ቹ​ንም ያዋ​ር​ዳ​ቸው ዘንድ የበ​ቀ​ልና የፍ​ዳን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ተጐ​ና​ጸፈ።


ስለ​ዚህ እኔ ደግሞ በመ​ዓት እሠ​ራ​ለሁ፤ ዐይኔ አይ​ራ​ራም፤ እኔም ይቅ​ርታ አላ​ደ​ር​ግም፤ ወደ ጆሮ​ዬም በታ​ላቅ ድምፅ ቢጮኹ አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም” አለኝ።


በቍ​ጣ​ዬና በመ​ቅ​ሠ​ፍቴ በተ​በ​ቀ​ል​ሁሽ ጊዜ በዙ​ሪ​ያሽ በአሉ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ትጨ​ነ​ቂ​ያ​ለሽ፤ ትደ​ነ​ግ​ጫ​ለ​ሽም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።


“ቍጣ​ዬ​ንና መዓ​ቴ​ንም በእ​ነ​ርሱ ላይ እጨ​ር​ሳ​ለሁ፤ መዓ​ቴ​ንም በፈ​ጸ​ም​ሁ​ባ​ቸው ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ን​ዓቴ እንደ ተና​ገ​ርሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ።


እኔም በተ​ዘ​ረ​ጋች እጅና በብ​ርቱ ክንድ፥ በቍ​ጣና በመ​ዓት፥ በታ​ላ​ቅም መቅ​ሠ​ፍት አወ​ጋ​ች​ኋ​ለሁ።


እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓ​ቱን በቍጣ፥ ዘለ​ፋ​ው​ንም በእ​ሳት ነበ​ል​ባል ይመ​ልስ ዘንድ እንደ እሳት ይመ​ጣል፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆ​ናሉ።


መጭ​መ​ቂ​ያ​ውን ብቻ​ዬን ረግ​ጫ​ለሁ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አል​ነ​በ​ረም፤ በቍ​ጣ​ዬም ረገ​ጥ​ኋ​ቸው፤ በመ​ዓ​ቴም ወደ መሬት ጣል​ጥ​ህ​ዋ​ቸው፤ ደማ​ቸ​ው​ንም በም​ድር ላይ አፈ​ሰ​ስሁ፤ ልብ​ሴም ሁሉ በደም ታለለ።


በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቆች ተሰነጠቁ።


እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፣ እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው፣ እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል።


ስለ ጠቡ በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለው ዘንድ ቀር​ቃ​ሃና ሣርን ማን በሰ​ጠኝ! አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ዛሬ አደ​ረገ፤ እነ​ርሱ ተቃ​ጥ​ለ​ዋ​ልና።


እኔ ደግሞ አግ​ድሜ በቍጣ እሄ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም ሰባት እጥፍ እበ​ቀ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


እስ​ከ​ዚ​ህም ድረስ ባት​ሰ​ሙኝ፥ አግ​ድ​ማ​ች​ሁም ብት​ሄ​ዱ​ብኝ፥


እኔም ደግሞ አግ​ድሜ ከእ​ነ​ርሱ ጋር በቍጣ ሄድሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድር አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ። ነገር ግን በዚ​ያን ጊዜ ያል​ተ​ገ​ረ​ዘው ልባ​ቸው ያፍ​ራል፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይና​ዘ​ዛሉ፤


አጥ​ር​ዋን ለምን አፈ​ረ​ስህ? መን​ገድ አላ​ፊም ሁሉ ይበ​ላ​ታል።


እን​ግ​ዲህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቍጣ​ዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎ​ችና በም​ድር ፍሬ ላይ ይፈ​ስ​ሳል፤ ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋ​ምም።”


ካፍ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓ​ቱን ፈጽ​ሞ​አል፤ ጽኑ ቍጣ​ው​ንም አፍ​ስ​ሶ​አል፤ እሳ​ትን በጽ​ዮን ውስጥ አቃ​ጠለ፤ መሠ​ረ​ቷ​ንም በላች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios