ዮሴፍም የበኵር ልጁን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው፤ እንዲህ ሲል፥ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አደረገኝ፤”
ዘፍጥረት 48:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልም ቀኝ እጁን ዘርግቶ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረው፤ እርሱም ታናሽ ነበረ፤ ግራውንም በምናሴ ራስ ላይ አኖረ፤ እጆቹንም አስተላለፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤል ግን ቀኝ እጁን በታናሹ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረ፤ ግራ እጁንም በቀኝ እጁ ላይ አስተላልፎ በበኵሩ በምናሴ ራስ ላይ አኖረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም ቀኝ እጁን ዘርግቶ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረው፥ እርሱም ታናሽ ነበረ፥ ግራውንም በምናሴ ራስ ላይ አኖረ፥ እጆቹንም አስተላለፈ፥ ምናሴ በኩር ነበርና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ግን እጆቹን በማመሳቀል አስተላልፎ ቀኝ እጁን በታናሹ በኤፍሬም ራስ ላይ፥ ግራ እጁን በበኲሩ በምናሴ ራስ ላይ አኖረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም ቀኝ እጁን ዘርግቶ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረው እርሱም ታናሽ ነበረ ግራውንም በምናሴ ራስ ላይ አኖረ እጆቹንም አስተላለፈ፥ ምናሴ ራስ ላይ አኖረ፤ እጆቹንም አስተላለፈ ምናሴ በኵር ነበርና |
ዮሴፍም የበኵር ልጁን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው፤ እንዲህ ሲል፥ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አደረገኝ፤”
ለዮሴፍም በግብፅ ምድር ልጆች ተወለዱለት፤ እነርሱም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጴጤፌራ ልጅ አስኔት የወለደችለት ምናሴና ኤፍሬም ናቸው። ሶርያዊት ዕቅብቱ የወለደችለት የምናሴም ልጅ ማኪር ነው። ማኪርም ገለዓድን ወለደ፤ የምናሴም ወንድም የኤፍሬም ልጆች ሱታላና ጠኀን ናቸው። የሱታላ ልጅም ኤዴን ነው።
ዮሴፍም ሁለቱን ልጆቹን ወሰደ፤ ኤፍሬምንም በቀኙ በእስራኤል ግራ፥ ምናሴንም በግራው በእስራኤል ቀኝ አቆማቸው፤ ወደ አባቱም አቀረባቸው።
ዮሴፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ጭኖ በአየ ጊዜ ከባድ ነገር ሆነበት፤ ዮሴፍም የአባቱን እጅ በምናሴ ራስ ላይ ይጭነው ዘንድ ከኤፍሬም ራስ ላይ አነሣው።
“በባሕር በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የኤፍሬም ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የኤፍሬም ልጆች አለቃ የኤሜሁድ ልጅ ኤሌሳማ ነበረ።
ሌዋውያንንም በእግዚአብሔር ፊት አቅርባቸው፤ የእስራኤልም ልጆች በሌዋውያን ላይ እጃቸውን ይጫኑባቸው።
“ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።
ፀሐይም በገባ ጊዜ ልዩ ልዩ ደዌ ያለባቸውን ድውያን ሁሉ አመጡለት፤ ከእነርሱም በእያንዳንዱ ላይ እጁን ጭኖ ፈወሳቸው።
ሙሴም እጆቹን ስለ ጫነበት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥበብን መንፈስ ተሞላ፤ የእስራኤልም ልጆች ታዘዙለት፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።