ዘፍጥረት 43:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም ዐይኑን አንሥቶ የእናቱን ልጅ ወንድሙ ብንያምን አየው፤ እርሱም አለ፥ “ወደ አንተ እናመጣዋለን ብላችሁ የነገራችሁኝ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነውን?” እነርሱም፥ “አዎን” አሉት። እንዲህም አለው፥ “ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍ በዐይኑ ሲቃኝ የእናቱን ልጅ ብንያምን አየና፣ “ያ የነገራችሁኝ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነው?” ብሎ ጠየቃቸው። ብንያምንም፣ “ልጄ፤ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍ በዐይኑ ሲቃኝ የእናቱን ልጅ ብንያምን አየና፥ “ያ የነገራችሁኝ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነው?” ብሎ ጠየቃቸው። ብንያምንም፥ “ልጄ፤ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍ የእናቱ ልጅ የሆነውን ወንድሙን ብንያምን ባየው ጊዜ “ ‘ታናሽ ወንድም አለን’ ብላችሁ ነግራችሁኝ ነበር፤ ይህ እርሱ ነውን?” አለና “ልጄ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይኑንም አንሥቶ የእናቱን ልጅ ብንያምን አያው እርሱም አለ፦ የነገራችህኝ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነውን? እንዲህም አለው፦ ልጄ ሆይ እግዚአብሔር ይባርክህ። |
እነርሱም አሉ፥ “ባሪያዎችህ በከነዓን ምድር የምንኖር ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ ታናሹም እነሆ ዛሬ ከአባታችን ጋር ነው፤ ሌላውም ሞቶአል።”
አሁንም እናንተ ወደዚህ የላካችሁኝ አይደላችሁም፤ እግዚአብሔር ላከኝ እንጂ፤ ለፈርዖንም እንደ አባት አደረገኝ፤ በቤቱም ሁሉ ላይ ጌታ፥ በግብፅ ምድርም ሁሉ ላይ አለቃ አደረገኝ።
አሁንም በፊቱ ትቆሙና ታገለግሉት ዘንድ፥ አገልጋዮቹም ትሆኑ ዘንድ፥ ታጥኑለትም ዘንድ እግዚአብሔር መርጦአችኋልና ቸል አትበሉ።”
ቅዱስ ሕዝብ በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን ይኖራል፤ ልቅሶን አልቅሺ፤ ይቅር በለኝም በዪ፤ ልቅሶሽን ባየ ጊዜ ይቅር ይልሻል፤ ሰምቶሻልና።
አሁንም ጸጋን ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔርን ለምኑ፣ ይህ ከእጃችሁ የተሰጠ ሲሆን ከቶ ፊታችሁን ይቀበላልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! አይዞህ፤ ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤” አለው።
ደቀ መዛሙርቱም እነዚህን ቃሎች አደነቁ። ኢየሱስም ደግሞ መልሶ “ልጆች ሆይ! በገንዘብ ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው።
ኢያሱም አካንን፥ “ልጄ ሆይ! ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ፤ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ አትሸሽገኝም” አለው።