ሮቤልም አባቱን አለው፥ “ወደ አንተ መልሼ ያላመጣሁት እንደሆነ ሁለቱን ልጆችን ግደል፤ ልጅህን በእጄ ስጠኝ፤ እኔም ወደ አንተ እመልሰዋለሁ።”
ዘፍጥረት 42:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባታቸው ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፥ “ልጅ አልባ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ ብንያምንም ትወስዱብኛላችሁ፤ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባታቸው ያዕቆብም፣ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ ኧረ ምን ጕድ ነው የመጣብኝ!” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባታቸው ያዕቆብም፥ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ ኧረ ምን ጉድ ነው የመጣብኝ!” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ አባታቸው “ልጆቼን ሁሉ እንዳጣ ትፈልጋላችሁን? ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ለመውሰድ ትፈልጋላችሁ፤ በዚህ ሁሉ መከራ የምሠቃየው እኔ ነኝ!” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባታቸውን ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፦ ልጅ አልባ አስቀራችሁኝ ዮሴፍ የለም ስምዖንም የለም ብንያምንም ትወስዱብኛላችሁ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ፤ |
ሮቤልም አባቱን አለው፥ “ወደ አንተ መልሼ ያላመጣሁት እንደሆነ ሁለቱን ልጆችን ግደል፤ ልጅህን በእጄ ስጠኝ፤ እኔም ወደ አንተ እመልሰዋለሁ።”
አምላኬም በዚያ ሰው ፊት ሞገስን ይስጣችሁ፤ ያን ወንድማችሁንና ብንያምንም ይመልስላችሁ፤ እኔም ልጆችን እንዳጣሁ አጣሁ።”
ዮሴፍም ለአባቱና ለወንድሞቹ፥ ለአባቱም ቤተ ሰዎች ሁሉ ለእያንዳንዱ ሰው እየሰፈረ እህልን ለምግብ ይሰጣቸው ነበር።
ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፤ ይህም ኀጢአትን የማስወገድ ፍሬ ሁሉ ነው።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የኀዘን፥ የልቅሶና የጩኸት ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።
በሰው ላይ እንደሚደርሰው ያለ ፈተና ነው እንጂ ሌላ ፈተና አያገኛችሁም። በምትችሉት መከራ ነው እንጂ በማትችሉት መከራ ትፈተኑ ዘንድ ያልተዋችሁ እግዚአብሔር የተመሰገነ ነው፤ እርሱም ከፈተና ትድኑ ዘንድ በመከራ ጊዜ ይረዳችኋል።
ዳዊትም በልቡ፥ “አንድ ቀን በሳኦል እጅ እሞታለሁ፤ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ምድር ከመሸሸ በቀር የሚሻለኝ የለም፤ ሳኦልም በእስራኤል አውራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተዋል፤ እንዲሁም ከእጁ እድናለሁ” አለ።