Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 38:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እኔ እን​ዲህ አልሁ፥ “በሕ​ይ​ወት ዘመኔ መካ​ከል ወደ ሲኦል በሮች እገ​ባ​ለሁ፤ የቀ​ረ​ው​ንም ዘመ​ኔን ተውሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እኔ፣ “በዕድሜዬ እኩሌታ፣ በሲኦል ደጆች ማለፍ አለብኝን? የቀረውንስ ዘመኔን ልነጠቅ ይገባልን?” አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እኔ፦ በሕይወት ዘመኔ እኩሌታ ከሕይወት ልለይ ይገባልን? በቀረው ዘመኔስ ወደ ሲኦል በሮች መግባት አለብኝን? አልኩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እኔ ገና በመካከለኛ ዕድሜዬ ሳለሁ የመኖር ዕድል ተነፍጎኝ ወደ ሙታን ዓለም የምወርድ መስሎኝ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እኔ፦ በሕይወት ዘመኔ መካከል ወደ ሲኦል በሮች እገባለሁ፥ የቀረው ዘመኔ ጐደለብኝ አልሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 38:10
12 Referencias Cruzadas  

ሙታ​ንን በሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንጂ በራ​ሳ​ችን እን​ዳ​ን​ታ​መን በው​ስ​ጣ​ችን ለመ​ሞት ቈር​ጠን ነበር።


ሕይ​ወቴ እስ​ት​ን​ፋስ እንደ ሆነች አስብ፤ ዐይ​ኔም መል​ካም ነገ​ርን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ዳግ​መኛ አታ​ይም።


በዚ​ያም ወራት ሕዝ​ቅ​ያስ ለሞት እስ​ኪ​ደ​ርስ ታመመ። ነቢ​ዩም የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ ወደ እርሱ መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ በሕ​ይ​ወት አት​ኖ​ር​ምና ቤት​ህን አስ​ተ​ካ​ክል” አለው።


እታ​ገሥ ዘንድ ጕል​በቴ ምን​ድን ነው? ነፍ​ሴም ትጽ​ናና ዘንድ ዘመኔ ምን​ድን ነው?


አንተ በም​ት​ሄ​ድ​በት በሲ​ኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕው​ቀ​ትና ጥበብ አይ​ገ​ኙ​ምና እጅህ ለማ​ድ​ረግ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ እንደ ኀይ​ልህ አድ​ርግ።


የይ​ሁዳ ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያስ ታምሞ ከደ​ዌው በተ​ፈ​ወሰ ጊዜ የጸ​ለ​የው ጸሎት ይህ ነው፦


ውኃ እስከ ነፍሴ ድረስ ፈሰሰ፤ ጥልቁ ባሕር በዙ​ሪ​ያዬ ከበ​በኝ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios