ያዕቆብም እጅግ ባለጠጋ ሆነ፤ ሴቶችም ወንዶችም አገልጋዮች፥ ብዙ ከብትም፤ ላሞችም፥ በጎችም፥ ግመሎችና አህዮችም ሆኑለት።
ዘፍጥረት 31:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም የላባ ልጆች ያሉትን ነገር፥ “ያዕቆብ ለአባታችን የሆነውን ሁሉ ወሰደ፤ ይህንም ሁሉ ክብር ከአባታችን ከብት አገኘ” ሲሉ ሰማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የላባ ወንዶች ልጆች፣ “ያዕቆብ የአባታችንን ሀብት እንዳለ ወስዶታል፤ ይህ ሁሉ እርሱ ያካበተውም ሀብት ከአባታችን የተገኘ ነው” እያሉ ሲያወሩ ያዕቆብ ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም፥ የላባ ልጆች፦ “ያዕቆብ የአባታችን የሆነውን ሁሉ ወሰደ፥ የአባታችን ከነበረውም ይህንም ሁሉ ሀብት አገኘ” ሲሉ ሰማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የላባ ወንዶች ልጆች “ያዕቆብ የአባታችንን ሀብት ወሰደ፤ ይህን ሁሉ ሀብት ያገኘው ከአባታችን ነው” እያሉ መናገራቸውን ያዕቆብ ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም የላባ ልጆች ያሉትን ነገር፦ ያዕቆብ ለአባታችን የሆነውን ሁሉ ወሰደ ይህንም ሁሉ ክብር ከአባታችን ከብት አገኘ ሲሉ ሰማ። |
ያዕቆብም እጅግ ባለጠጋ ሆነ፤ ሴቶችም ወንዶችም አገልጋዮች፥ ብዙ ከብትም፤ ላሞችም፥ በጎችም፥ ግመሎችና አህዮችም ሆኑለት።
ላባም ለያዕቆብ እንዲህ ብሎ መለሰለት፥ “ሴቶቹ ልጆች ልጆች ናቸው፤ ወንዶቹም ልጆች ልጆች ናቸው፤ መንጎቹም ከብቶች ናቸው፤ ይህ የምታየው ሁሉ የእኔ ነው፤ የልጆችም ሀብት ነው፤ ዛሬም በእነዚህ በሴቶች ልጆችና በወለዱአቸው ልጆቻቸው ላይ ምን አደርጋለሁ?
ለአባቴ በግብፅ ምድር ያለኝን ክብሬን ሁሉ፥ በዐይኖቻችሁ ያያችሁትንም ሁሉ ንገሩት፤ አባቴንም ወደዚህ ፈጥናችሁ አምጡት።”
እኔ ድካምን ሁሉና የብልሃት ሥራውን ተመለከትሁ፥ ለሰውም በባልንጀራው ዘንድ ቅንአትን እንዲያስነሣ አየሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
ሲኦልም ሆድዋን አስፍታለች፤ አፍዋንም ያለ ልክ ከፍታለች፤ የተከበሩና ታላላቅ ሰዎች ባለጠጎቻቸውና ድሆቻቸውም ወደ እርስዋ ይወርዳሉ።
በትዕቢት ተነፍቶአል፤ አንዳችም አያውቅም፤ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፤ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ።
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።