Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ጢሞቴዎስ 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4-5 በትዕቢት ተነፍቶአል፤ አንዳችም አያውቅም፤ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፤ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ያ ሰው በትዕቢት ተወጥሯል፤ አንዳችም አያስተውልም። ስለ ቃላት ለመከራከርና ለመጣላት ክፉ ጕጕት አለው፤ እነዚህም ቅናትን፣ ጥልን፣ ስድብን፣ መጥፎ ጥርጣሬን ያስከትላሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በትዕቢት የተወጠረና ምንም የማያውቅ ነው፤ ነገር ግን የንትርክና በቃላት የመከራከር ለየት ያለ ክፉ ምኞት አለበት፤ እነዚህም ነገሮች የሚያመጡት ቅንዓትን፥ መከፋፈልን፥ ስድብን፥ ክፉ ጥርጣሬን፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በትዕቢት የተወጠረና ምንም የማያውቅ ነው፤ ነገር ግን ስለ ቃላት የመከራከርና የመጨቃጨቅ ክፉ ምኞት አድሮበታል፤ ይህም የሚያስከትለው ቅንአትን፥ ጠብን፥ ስድብን፥ መጥፎ ጥርጣሬን፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4-5 በትዕቢት ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም፥ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፥ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ።

Ver Capítulo Copiar




1 ጢሞቴዎስ 6:4
44 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ጠብን እንዲያመጣ አውቀህ ከሰነፎችና ካልተማሩ ምርመራ ራቅ፤


ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤


በትዕቢት ተነፍቶ በዲያቢሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን።


እነዚህ ግን የማያውቁትን ሁሉ ይሳደባሉ፤ አእምሮም እንደሌላቸው እንስሶች በፍጥረታቸው በሚያውቁት ሁሉ በእርሱ ይጠፋሉ።


እነዚህ ግን ለመጠመድና ለመጥፋት በፍጥረታቸው እንደ ተወለዱ አእምሮ እንደ ሌላቸው እንስሶች ሆነው፥ በማያውቁት ነገር እየተሳደቡ በጥፋታቸው ይጠፋሉ፤


ይህን አሳስባቸው፤ በቃልም እንዳይጣሉ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፤ ይህ ምንም የማይረባ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና።


እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፤ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል።


ከንቱና ከመጠን ይልቅ ታላቅ የሆነውን ቃል ይናገራሉና፤ በስሕተትም ከሚኖሩት አሁን የሚያመልጡትን በሥጋ ሴሰኛ ምኞት ያታልላሉ።


ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤


ነገር ግን ሞኝነት ካለው ምርመራና ከትውልዶች ታሪክ ከክርክርም ስለ ሕግም ከሚሆን ጠብ ራቅ፤ የማይጠቅሙና ከንቱዎች ናቸውና፤


ሕዝ​ቡም እጅግ ታወኩ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስ​ንም ተከ​ራ​ከ​ሩ​አ​ቸው፤ ስለ​ዚህ ነገ​ርም ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስን፥ ጓደ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አሉት ወደ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት ሊል​ኳ​ቸው ተማ​ከሩ።


‘ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ፤ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም፤’ የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥


“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤” ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።


በመ​ታ​ለ​ልና ራስን ዝቅ በማ​ድ​ረግ ለመ​ላ​እ​ክት አም​ልኮ ትታ​ዘዙ ዘንድ ወድዶ፥ በአ​ላ​የ​ውም በከ​ንቱ የሥ​ጋው ምክር እየ​ተ​መካ የሚ​ያ​ሰ​ን​ፋ​ችሁ አይ​ኑር።


የም​ት​ሠ​ሩ​ትን ሁሉ ያለ ማን​ጐ​ራ​ጐ​ርና ያለ መጠ​ራ​ጠር በፍ​ቅ​ርና በስ​ም​ም​ነት ሥሩ።


በክ​ር​ክ​ርና ከንቱ ውዳ​ሴን በመ​ው​ደድ አት​ሥሩ፤ ትሕ​ት​ናን በያዘ ልቡና ከራ​ሳ​ችሁ ይልቅ ባል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁን አክ​ብሩ እንጂ አት​ታ​በዩ።


ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ን​ዶች በቅ​ና​ታ​ቸ​ውና በክ​ር​ክ​ራ​ቸው፥ ሌሎ​ችም በበጎ ፈቃድ ስለ ክር​ስ​ቶስ ሊሰ​ብ​ኩና ሊያ​ስ​ተ​ምሩ የወ​ደዱ አሉ።


አን​ዱም ምንም ሳይ​ሆን ምንም የሆነ ቢመ​ስ​ለው ራሱን ያታ​ል​ላ​ልና።


ኩሩ​ዎች አን​ሁን፤ እርስ በር​ሳ​ችን አን​ተ​ማማ፤ እርስ በር​ሳ​ች​ንም አን​ቀ​ናና።


እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​በ​ላ​ሉና የም​ት​ነ​ካ​ከሱ ከሆነ ግን፥ እርስ በር​ሳ​ችሁ እን​ዳ​ት​ተ​ላ​ለቁ ተጠ​ን​ቀቁ።


የሚ​ገ​ዙ​አ​ች​ሁ​ንና የሚ​ቀ​ሙ​አ​ች​ሁን፥ መባያ የሚ​ያ​ደ​ር​ጓ​ች​ሁ​ንና የሚ​ታ​በ​ዩ​ባ​ች​ሁን፥ ፊታ​ች​ሁ​ንም በጥፊ የሚ​መ​ት​ዋ​ች​ሁን ትታ​ገ​ሡ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ች​ሁና።


ከሁሉ አስ​ቀ​ድሞ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በም​ት​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ እን​ደ​ም​ት​ጣ​ሉና እን​ደ​ም​ት​ከ​ራ​ከሩ ሰም​ቻ​ለሁ፤ የማ​ም​ነ​ውም አለኝ።


ነገር ግን የሚ​ጠ​ራ​ጠር ቢኖር እኛ ወይም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን እን​ዲህ ያለ ልማድ የለ​ንም።


ራሳ​ች​ሁን አታ​ስቱ፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ በዚህ ዓለም ጥበ​በኛ እንደ ሆነ የሚ​ያ​ስብ ሰው ጥበ​በኛ ይሆን ዘንድ ራሱን ዐላ​ዋቂ ያድ​ርግ።


በሥ​ጋዊ ሕግም ትኖ​ራ​ላ​ች​ሁና እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​ቃ​ኑና የም​ት​ከ​ራ​ከሩ ከሆነ ግን ሥጋ​ው​ያን መሆ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምን? እንደ ሰው ልማ​ድስ የም​ት​ኖሩ መሆ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምን?


እም​ነቱ ደካማ የሆ​ነ​ውን ሰው ታገ​ሡት፤ በዐ​ሳ​ቡም አት​ፍ​ረዱ።


በቀን እን​ደ​ሚ​ሆን በጽ​ድቅ ሥራ እን​መ​ላ​ለስ፤ በዘ​ፈ​ንና በስ​ካር፥ በዝ​ሙ​ትና በመ​ዳ​ራ​ትም አይ​ሁን፤ በክ​ር​ክ​ርና በቅ​ና​ትም አይ​ሁን።


እርስ በር​ሳ​ች​ሁም በአ​ንድ ዐሳብ ተስ​ማሙ፤ ትዕ​ቢ​ትን ግን አታ​ስቡ፤ ራሱን የሚ​ያ​ዋ​ር​ደ​ው​ንም ሰው ምሰሉ፤ እና ዐዋ​ቆች ነን አት​በሉ።


ለሚ​ክ​ዱና እው​ነ​ትን ለሚ​ለ​ውጡ፥ ዐመ​ፅ​ንም ለሚ​ወ​ድዱ ሰዎች ዋጋ​ቸው ቍጣና መቅ​ሠ​ፍት ነው።


ስለ ትም​ህ​ር​ትና ስለ ስሞች፥ ስለ ሕጋ​ች​ሁም የም​ት​ከ​ራ​ከሩ ከሆነ ግን ለራ​ሳ​ችሁ ዕወቁ፤ እኔ እን​ዲህ ያለ ነገር ልሰማ አል​ፈ​ቅ​ድም።”


በዚ​ያ​ችም ከተማ ሲሞን የሚ​ባል አንድ ሰው ነበር፤ የሰ​ማ​ርያ ሰዎ​ች​ንም ያስት ነበር፤ ሰው​የዉ ሥራ​የኛ ነበር፤ ራሱ​ንም ታላቅ ያደ​ርግ ነበር።


እነሆ፥ ለጠ​ብና ለክ​ር​ክር ትጾ​ማ​ላ​ችሁ፤ ድሃ​ው​ንም በጡጫ ትማ​ታ​ላ​ችሁ፤ በም​ት​ጮ​ኹ​በት ጊዜ ድም​ፃ​ችሁ እን​ዲ​ሰማ ለእኔ ትጾ​ማ​ላ​ች​ሁን? ድም​ፃ​ች​ሁ​ንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እን​ደ​ም​ት​ጾ​ሙት አት​ጾ​ሙም።


ምንም ሳይኖራቸው ራሳቸውን ባለጠጎች የሚያደርጉ አሉ፥ ባለጠግነታቸው ብዙ ሲሆን ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉም አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios