ፈርዖንም አብራምን ጠርቶ አለው፥ “ይህ ያደረግህብኝ ምንድን ነው? እርስዋ ሚስትህ እንደ ሆነች ለምን አልገለጥህልኝም?
ዘፍጥረት 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፥ “ይህን ለምን አደረግሽ?” አላት። ሴቲቱም አለች፥ “እባብ አሳተኝና በላሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አምላክ ሴቲቱን፣ “ይህ ያደረግሽው ምንድን ነው?” አላት። እርሷም፣ “እባብ አሳሳተኝና በላሁ” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔርም ሴቲቱን፦ “ይህ ያደረግሽው ምንድነው?” አላት። ሴቲቱም፥ “እባብ አሳተኝና በላሁ” አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን “ይህ ያደረግሽው ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቃት። እርስዋም “እባብ አታለለኝና በላሁ” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፦ ይህ ያደረግሽው ምንድር ነው? አላት። ሴቲቱም አለች፦ እባብ አሳተኝና በላሁ። |
ፈርዖንም አብራምን ጠርቶ አለው፥ “ይህ ያደረግህብኝ ምንድን ነው? እርስዋ ሚስትህ እንደ ሆነች ለምን አልገለጥህልኝም?
ኢዮአብም ወደ ንጉሥ ገብቶ፥ “ይህ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው? እነሆ፥ አበኔር መጥቶልህ ነበር፤ በደኅና እንዲሄድ ስለምን አሰናበትኸው?
እርሱም፥ “እኔ ደግሞ እንዳንተ ነቢይ ነኝ፤ መልአክም፦ እንጀራ ይበላ ዘንድ ውኃም ይጠጣ ዘንድ ከአንተ ጋር ወደ ቤትህ መልሰው ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተናገረኝ” አለው። ዋሽቶም ተናገረው።
ሴት ልጅም ብትወልድ እንደ ግዳጅዋ ወራት ሁለት ሳምንት ያህል የረከሰች ናት፤ ከደምዋም እስክትነጻ ድረስ ስድሳ ስድስት ቀን ትቈይ።
እነዚያም ሰዎች ከእግዚአብሔር ፊት እንደ ኰበለለ እርሱ ስለ ነገራቸው ዐውቀዋልና እጅግ ፈርተው፥ “ይህ ያደረግኸው ምንድን ነው?” አሉት።
ጲላጦስም መልሶ፥ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ለእኔ አሳልፈው የሰጡህ ወገኖችህና ሊቃነ ካህናት አይደሉምን? Aረ ምን አድርገሃል?” አለው።
ነገር ግን እባብ ሔዋንን በተንኰሉ እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ከክርስቶስ የዋህነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ።
ሳሙኤልም፥ “ያደረግኸው ምንድን ነው?” አለ። ሳኦልም፥ “ሕዝቡ ከእኔ ተለይተው እንደ ተበታተኑ፥ አንተም በነገርኸኝ መሠረት በቀጠሮው ቀን እንዳልመጣህ፥ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ማኪማስ እንደ ተሰበሰቡ አየሁ፤
ሳኦልም፦“ሕዝቡ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ይሠዉአቸው ዘንድ ከበጎችና ከላሞች መንጋዎች መልካም መልካሙን አድነዋቸዋልና ከአማሌቃውያን አመጣን፤ የቀሩትንም ፈጽሜ አጠፋሁ” አለው።